በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ስደተኞችን ከሰሰ!

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ የሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ ከፍተኛ የሆነ ስህተት በመስራት ላይ ይገኛል! ይህዉም በዚያ በደቡብ አፍሪካ በስደት የሚገኙ በተለይም የወያኔን ስርአት በመቃወም የሚኖሩ ወገኖች በህጋዊ መንገድ በሐገሪቷ የስደተኞች ቢሮ ( DAPARTMENT OF HOME AFFAIR ) የመታወቂያ ወረቀት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ የተሰጣቸዉ ግለሰቦች ለንግድና ለተለያየ የአገልግሎት ጥቅም ወደ ሌሎች ሐገር ሊያሸጋግር የሚችል የጉዞ ሰነድ ( PASPORT ) እንዳያገኙ ፈጽሞም ኢንዳይሰጣቸዉ የወያኔዉ ተላላኪ የሆነዉ የኢትዮጵያ እንባሲ ክስ አቅርቧል!
በመሆኑም አንድ ስደተኛ ወረቀት ሊያሰጠዉ ከሚችለዉ መስፈርት አንዱ የወያኔን ስርአት በመቃወሙ ምክንያት መሰደዱን ማረጋገጥ ከመፋሉ የተነሳ በመሆኑ ማንኛዉም ስደተኛ በስደተኝነት እያለ የጉዞ ሰነድ ( Pasport ) የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
የህጉ አንክዋር እንዲህ ይላል “አንድ ስደተኛ ግለሰብ ለደህንነቱ ሲባል ከኢትዮጵያ ዉጭ በጉዞ ሰነዱ የትም ሐገር የመጓዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ”
ነገር ግን የኢትዮጵያ ኢንባሲ በክሱ ላይ እንዳስቀመጠዉ መረጃ አለኝ እያለ ሙግት ጀምሯል! ይህዉም በተባበሩት መንግስታት ዉል መሰረት የደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ቢሮ የጉዞ ሰነድ ( passport ) የሚሰጣቸዉ ኢትዮጵያዊያኖች ፓስፖርቱን የሚፈልጉት ወደ ኤርትራ በመጓዝ አርበኞች ግንቦት 7 የተባለ የሽብር ቡድንn ለመቀላቀል ነዉ! ። የሚል ተልካሻ መነሻ ሐሳብ ሲሆን ክሱ በጥንቃቄ እንዲታይለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
ይህን መሰል ክህደት በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚፈጽመዉ ተላላኪዉ የወያኔ ኢንባሲ በሰሞኑ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የደቡብ ተወላጆች በተለይም የከንባታና ሐዲያ ልጆችን ሰብስቦ አስገራሚ የሆነ የዉንብድና የሐሰት ስራ በገዛ ወገኖቹ ላይ ሊፈጽም ተዘጋጅቷል!
አምባሳደር ሙሉጌታ የተገኙበት የደቡብ ህዝቦች ስብሰባ ላይ የተገለጸዉ ተንኮል… በስደተኝነት ህጋዊ ወረቀት አግኝታችሁ ከኢትዮጵያ ዉጭ የትም መሄድ የሚያስችል የጉዞ ሰነድ ( Pasport ) ያላችሁ የደቡብ ተወላጆች ሐገራችሁ ገብታችሁ ገንዘባችሁን ተጠቀሙ ወረቀታችሁ እንዳይበላሽ ከዚህ ወደ ሱዳን ወይም ኬንያ ወይም ደግሞ ጅቡቲ ትሄዱና ከዚያ ደግሞ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ ሐገራችሁ መግባት ትችላላችሁ በማለት ስደተኞችን ለከሰሱት የኤርትራ ጉዞ መረጃ መሰብሰቢያ በማድረግ ለመጠቀም እያመቻችሁ ይገኛሉ።
በመሆኑም በዚህ እኩይ ተግባር የተበሳጩ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ኢንባሲ ያደረጋቸዉን ገለጻዎች በሙሉ በድምጽና በምስል በመያዝ ለሚመለከተዉ አካል አስተላልፈዉ ጉዳዩ በተለየ መልኩ እየታየ እንደሚገኝ መረጃ የደረሰዉ የወያኔ ኢንባሲ ወደ ሐገር ቤት የላከዉን ሪፖርት የዉስጥ ምንጮች አሳልፈዉ ሰጥተዋል።
ማሳሰቢያ….. በደቡብ አፍሪካ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ ይህን የወያኔ ተንኮል ግምት ዉስጥ በማስገባት ከተጠነሰሰባችሁ ሴራ እንድትጠነቀቁ እና እራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

poster-with-pic-a-ማይ-14-

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: