የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት ዛሬም ቀጥሏል፣ ሁለቱም ሀገሮች ተጨማሪ ጦር እያንቀሳቀሱ ነው

by Aseged Tamene

በተጨማሪም  የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት ዛሬም ቀጥሏል፣ ሁለቱም ሀገሮች ተጨማሪ ጦር እያንቀሳቀሱ ነው

መንግስት ግጭት አይሎ ከሚታይባት ፆረና አካባቢ በተጨማሪ በተለያዩ የድንበር አካባቢዎች ጦሩን በተጠንቀቅ እንዲቆም አድርጓል። “ኢትዮጵያ ወረራ ልትፈፅምብኝ ነው” ያለችው ኤርትራ ከጦር ሰራዊቷ ከፍተኛ ልምድ ያለውን ዕዝ በሶስት አካባቢዎች እንዲስፍር አድርጋለች። የኤርትራ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ክተት ሊያውጁ እንደሚችሉ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ ሁሉም የክፍለ ጦር አዛዦችን ወደ ግንባር እንዲንቀሳቀሱ የደረገች ሲሆን በእረፍት ላይ የነበሩ ሁለት ከፍተኛ አዛዦችም በአስቸኳይ ወደ ምድባቸው እንዲመለሱ ታዘዋል።

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለሁለት አስርት አመታት በቀኝ ግዝት ይዞ የቆየዉ ይህዉ የወያኔ ቡድን በተለያየ የሐገሪቷ ክፍሎች ከገባበት የጦር አጣብቂኝ ዉጥረት የተነሳ ሲሸሸዉና ሲሸሽገዉ የነበረዉን ጦርነት ሳይወደዉ በግዱ እየተጋፈጠዉ ይገኛል።

በዚህ ጦርነት ወያኔ ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበት የተረጋገጠ ሲሆን የ 25ኛ ክፍለ ጦር የደጀን ጦርን ለማጠናከር በሚል ወደ አዉድማዉ ተጠግቷል።
በጦርነቱ የደረሰዉ የጉዳት መጠን ያልተረጋገጠ ከመሆኑ ባሻገር ከትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን መከላከያ ዘመቻ ስምሪት መምሪያ አካሎች የተገኘዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ በወያኔ በኩል የተሞከረዉ ትንኮሳ በተዘዋዋሪ መንገድ በኤርትራ ከሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ጋር እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ድንበር ዘለልነቱ የኤርትራ ወታደሮችንም ተሳታፊ እንዳደረጋቸዉ እንዲሁም እንደሚያደርጋቸዉ በጉልህ ያሳየ ነዉ።

በአፍሪካ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ልዩ ሬንጀር ኮርስና የበረሃና የከተማ ልምምድ ስልጡን ሐይል የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የጦርነት ትንኮሳ ወደ ፈጸመባቸዉ አካባቢዎች መንቀሳቀሱን ምንጮች እየጠቀሱ ይገኛሉ!
በተልይም የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ወታደራዊ ምንጮች ከዉስጥ እንደጠቆሙት በህወሃት ወታደሮች ክንፍ አጥብቆ የሚፈራዉ በሜጀር ጄነራል ዳዊት አብረሃ የሚመራዉ ብዛት ያለዉ የኤርትራ ሰራዊት መንቀሳቀሱን ሲሆን….
ህወሃት ኢትዮጵያዊነት የሚሰማቸዉ በወያኔ ሰራዊት ዉስጥ የሚገኙ ወታደሮችን ጥያቄ ለማስተናገድ ወታደራዊ ፖለቲካ ክፍሉ እንደተሳነዉ እየተገለጸ ይገኛል።
ሰራዊቱ ለወራቶች ዉጊያዉን በተመለከተ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ቢደረግለትም በትንኮሳዉ ጦርነት ላይ ያለ አግባብ የሚደረግ ደም መፋሰስ መሆኑን እየገለጸ እንደሚገኝ ያሳወቁት ወታደራዊ ምንጮች ህወሃት በዚህ ከቀጠለች ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ህዝብ ጋር በምታደርገዉ ግብ ግብ ወታደሩ የሚያደርገዉ እገዛ እጅግ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ ከወዲሁ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብታል ተብላል

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: