በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በሙስና ተጠርጥረው የተያዙት አቶ ዘላለም ጀማነህ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሠማ…

ሸገር ከኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች እንደሰማው የፀረ ሙስና ኮሚሽኑ በተጠርጣሪው ላይ የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁን ነው፡፡

አቶ ዘላለም ጀማነህ የክልሉ መንግሥትና ድርጅት ኃላፊ በነበሩበት ጊዜ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ህዝባዊ አደራ በመተው የተሰጣቸውን ሥልጣን ያለአግባብ ለግል ጥቅም አውለዋል በሚል ያለመከሰስ መብታቸው ወርዶ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፓርቲያቸው ኦህዴድ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሸገር ዛሬ እንደሰማው በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማዕረግ የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ በመሆን ይሰሩ የነበሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ ዛሬ አቃቂ ወረዳ ፍርድ ቤት ለምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ቀርበዋል፡፡

ከአቶ ዘላለም ጀማነህ በተጨማሪ የሱሉልታ ከተማ ምክትል ከንቲባ በመሆን ይሰሩ የነበሩት አቶ ዲሮ ደሜ በህግ ከተፈቀደላቸው በላይ በራሣቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም መሬት በመውሰዳቸው ተጠርጥረው መያዛቸውን ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡

የሱሉልታ ከተማ ምክትል ከንቲባ የነበሩት አቶ ዲሮ ደሜ ከ1 ሺህ 300 ለሚበልጡ ሰዎች ህገ-ወጥ መሬት በመስጠት ወንጀል መከሰሣቸውንም ሰምተናል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት የአቶ ዘላለም ጀማነህንና የአቶ ዲሮ ደሜን ያለመከሰስ መብት ገፎ ለፍርድ እንዲቀርቡ ከቀናት በፊት የወሰነ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ዛሬ ከቀረቡት ከአቶ ዘላለም ጀማነህ በተጨማሪ በአቶ ዲሮ ደሜ ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው በቅርቡም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ሲል ኮሚሽኑ ነግሮናል፡፡

Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: