ጎንደር በወያኔና በሕዝቡ መካከል ውጥረቱ አሁንም ቀጥሏል፥

ደቡብ ጎንደር ደብረታቦርና ጋይንት ጉና ዓካባቢ የሰነበተው ጦርነት መሰል ሁኔታ እንዳለ ሆኖ፥
ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ግንቦት 30 2008, በላይ አርማጭሆ ወረዳ ፈረስ መግሪያ ቀበሌ፤ ቤቱ ተከቦ በወያኔ ደፈጣ የተጣለበት ወጣት ከወያኔ መከላከያ ኃይል ጋር ተታኩሶ ዓንድ የመከላከያ ባልደረባ መግደሉንና መሳሪያውን ማርኮ ወደ ጫካ መግባቱ ተሰምቷል፥
በወያኔ መከላከያ ሠራዊት የተደረገበትን ከበባ በከፍተኛ ተኩስ መክቶ፥ አንድ የመከላከያ አባል ገድሎ ጠመንጃውን ማርኮ ወደ ጫካ የገባው ግለሰብ አልብሰው ወልዴ የተባለ ወጣት ሲሆን፥ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ትሰራለህ በሚል ታስሮ እንደነበርና በቅርቡ የተፈታ መሆኑም ታውቋል፥
ለዛሬው ነገር መነሻ የሆነው፥ ንብረትነቱ የትግራይ ነጻዓውጭ ድርጅት መሆኑ የሚታወቀው የዳሸን ቢራ በአካባቢው እንዳይከፋፈል ሰዎችን በማሳደምና ሰሞኑን ዳሸን ቢራ የሚያከፋፍል ሁለት የመከላከያ መኪና ላይ ጥቃት አድርሰሃል በሚል ጥርጣሬ መሆኑን ዓክለው ጠቁመዋል፥
በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቹ መያዛቸውንና አካባቢው በወያኔ እየታወከ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል፥
ፈረስ መግሪያ ፥ በሁመራ መንገንድ ከጎንደር ከተማ ወደ 35 ኪሎሜትር ርቀት ላይ፥ በትክልድንጋይና በሙሴባም ከተማ መካከል ያለች፥ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት በቋሚነት የሰፈረባት በላይ ዓርማጭሆ ወረዳ የምትገኝ ትንሽ ቀበሌ ነች፥

gonder

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: