ኢትዮጵያዊያኑ በርሀብ ሊያልቁ ነው በቀን አንድ ዳቦ ብቻ በግሩም ተ/ሀይማኖት

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ካምፕ ውስጥ በርሀብ ሊያልቁ ነው። የመን በአየር ድብደባ ቁም ስቅሏን ማየት ከጀመረች አመት አለፈ። በዚህን ጊዜ በሙሉ ከመቶ ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ የመን እየገቡ ነው።
መንገድ የቀረው ቀርቶ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚገባውም ብዙ ነው። ሁዴዳ ያለው የIOM ካምፕ በየጊዜው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን ያስተናግዳል። በአሁኑ ሰዓት ግን የባጀት እጥረት አለብኝ በማለት የምግብ አቅርቦቱ በቀን አንድ ዳቦ ብቻ ነው።
በከፍተኛ የርሀብ እና ችግር ውስጥ ናቸው። ከየቦታው ተለቅመው በእስር ቤት ያሉት እና በካምፕ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በአሳዛኝ ሁኔታ ለስድስት ወር በርሀብ ተጠብሰው ያሉበት ሁኔታ ይሄን ይመስላል።
ምንም አይነት የምግብ ድጋፍ ለማድረግ አቅም የለንም ያለው IOM በሚቀጥለው ሳምንት ስደተኞቹን ወደ ሀገር ለመመለስ በመሰናዶ ላይ ነው። ሊሴ ፓሴ ለማዘጋጀት ኤምባሲ ወክሎ ያስቀመጣቸውን ሁለት ሰዎች ወደ ሁዴዳ እንዲሄዱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ቅዳሜ ወይ እሁድ ሄደው የተለመደውን ትብብር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ሌሴ ፓሴው ቢዘጋጅም ጉዞው ግን በታቀደለት ጊዜ እንዳይካሄድ ንፋስ ስለተነሳ ባህሩን ማቋረጥ አስቸጋሪ ይሆናል ተብሎ ተፈርቷል። ጉዞው የሚዘገይ ከሆነ በዚሁ የርሀብ ሁኔታ እንዴት ሊቆዩ ይችላሉ? የአካባቢው ሰው ተርበው የሚለምኑትን ኢትዮጵያን ያለውን እያካፈለ በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል። በርሀብም በበሽታም የሚሞቱትን ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።
መርዳት የምትችሉ ወገኖቻችንም ሆናችሁ ከዚህ በፊት የመን ላለ ስደተኛ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሞከራችሁ። አሁን IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ በርሀብ እያለቀ ነውና አሁን ተረባረቡ.

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: