የጃዋር ስኬት እና የፖለቲካ ፈላሻዎች ( ሄኖክ የሺጥላ )

የብሄራዊ ፈተና ምስጢርን ለህዝቡ ቀድሞ በማሳወቅ ( « በማሰረቅ» የሚለው ስለማይጥም ነው ) ፥ ታቅዶ የነበረው የብሄራዊ ፈተና ክንውን ቢያንስ በታቀደለት እለት እንዳይከናወን ስለማድረጉ ብዙ እየተወራለት ነው ። ኦቦ ጃዋር

እርግጥ ጃዋር እጁ ረዝሞ ፥ ከሚኒሶታ አዲስ አበባ ተዘርግቶ ፥ ወያኔን ብስጭት እና ቁጭት ውስጥ የሚጥሉ ጉልህ ነገሮችን እያደረገ ሰለመሆኑ ተደረጉ የተባሉት ነገሮች ገላጭ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል ( መመርመር እንደሚኖርባቸው ባምንም)!! ። ባንፃሩ ግን ጃዋር እና ህቡዕ ድርጅቱ ፥ ፈጠሙ ከተባለው ጉዳይ ጀርባ ምናልባችም በበለጠ አንድ በረጋ እና በሰከነ ልቦና ልናጤን የሚገባው ጉዳይም አለ ። ይኽም ምንድን ነው ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ በትር ላለፉት 25 አመታት ሲሰቃይ የመኖሩን ያህል ወያኔን በዚህ ኣንድ እና ሁለት አመት ውስጥ ጃዋር እንዴት ሊፈትነው ቻለ? ፈተናውን ሰርቀው ለጃዋር የላኩት ግለሰቦችስ ፥ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ፥ ሃገርን ከወያኔ ክርን ለማውጣት በሚደረገው ትግል እና ትንቅንቅ ፥ ካሉት ተቃዋሚዎች መርጠው እና አወዳድረው ፥ ለጃዋር ሲገብሩ ለምን እና እንዴት ብሎ መጠየቁም አግባብነት አለው ባይ ነኝ ።

ከማየው እና ከምረዳው የ ኦቦ ጃዋር ፈተናውን ቀድሞ መለጠፍ እና የፈተናው መሰረዝ ፥ የብዙ ኢ ጃዋር ልቦናዎችን ያማለለ ነገርም መስሎ ተሰምቶኛል ። የጠላታችን ጠላት ፥ ጠላታችንን ስለፈተነው ፥ በአቅሙ ተማርከን ወዳጅ ልናደርገው የምንዳዳ ፥ ወይም ድል ስለራቀን ፥ ከገደሉን በላይ ጥላቻ በሰነቀ ፥ ሞት ባረገዘ ግለሰብ ርዮት ስር ለመውደቅ የምንደፍር ምስኪኖች ነን ብዬ ግን ገምቼ አላውቅም ።

መዘንጋት የሌለብን ጉዳይ ፥ ጃዋር ልክ እንደ ሌሎቹ እየታገለ ነው ። የሚታገልለት ህዝብ ወይም አካል ደሞ እንደ ማንኛውም ህዝብ የወያኔ በትር የደረሰበት ነው ። ከዛ ባለፈ ግን ፥ ወያኔን ከመጣል እና ከማሸነፍ በዘለለ ፥ የኦሮሞ ህዝቦችን መብትም ከማስከበር ባለፈ ፥ በጃዋርኛ ሌላ ጠላት ህዝብ አለ « ሚኒሊክ እና የሚኒሊክ ዘሮች » የሚባሉ ። ከዚህ አንጣር አይደለም ፈተና ወያኔን በሙሉ ሰርቆ ህርጣሌ እቶን ውስጥ የመክተት አቅሙን ቢያገኝ ፥ የመጨረሻ ግቡ የኔን ማንነት እንደ ወያኔ ማጥፋት ስለሆነ በዚህ ሰው ማንኛውም አይነት የፖለቲካ ድል አልደመምም!

ሌላ መማር ያለብን ጉዳይ ፥ በኢትዮጵያዊነት ሃገር ለማዳን ተደራጅተው የሚቧችሩት ያልተሳካላቸው ጃዋር ግን የተሳካለት ( የሚመስለው ) የመዋቅሩም ሆነ የግቡ መሰረት አንድን ብሄር ማዳን ብቻ ሳይሆን በድህረ ከድህነቱ መልስ ትናንት ጨቆኑን ብለው ዛሬ ለመሰባሰባቸው ምክንያት የሆኗቸውን ዘሮችም ማጥፋት ነው ።

ለዚህም ነው ቀልዱን ትተህ አማራ ተደራጅ የምለው። ለኔ የጃዋር ድል የወያኔን የመውደቂያ ቀን መቅረቡን ብቻ ሳይሆን ፥ የአማራንም ሙሉ በሙሉ የመጥፊያ ሰአት መዳረሻ ያሳየኛል ( ይነግረኛል)!
በህይወቴ በዚህኛው አውሬ ድል የምደሰት ፥ በዛኛው አውሬ ስልጣን የምናደድ ግብዝ መሆንን አልሻም ። ከጠላቶቻችን ጠላቶች ድል ይልቅ የወዳጆቻችንን ውድቀት ያንገበግበናል ። በምክንያት እና በትግሉ መሰረታዊ ማንነት ላይ ብዥታ የሌለው ሰው ( አካል ) ፥ በቅፅበታዊ ድሎች ሳይሆን ፥ በዘላቂ ሰላሞች ላይ ያለውን ኢ ረፋድ መድረሻ ያውቀዋልና ፥ ነገሩን ሁሉ በጥሞና ብናይስ ። የወያኔ መውደቅ አስፈላጊ ነው ። የትግሬ ወያኔ ወድቆ የኦሮሞ ወያኔ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ደሞ እጅግ አስፈላጊ ነው ።
ጃዋር ፈተና ሲሰርቅ ወይም እንዲሰረቅ ሲያስደርግ ፥ በፍጥነት የጃዋር አራጋቢ በመሆን የፖለቲካው ፍልሰት ፥ ሰው አቅም በማጣቱ አቋም ስለመምከኑ ማሳያ ነው ። ይህ ማለት ፥ ነገ ደሞ ግንቦት ሰባት አንድ ነገር ሲያደርግ ተገልብጦ ግንቦት ሰባት ለመሆን የሚጠይቀው ነገር ግፋ ቢል ተገለባባጭ ስብዕና ነው ፥ እኔ ግን እላለሁ ለምን እና ማንን እንደምትታገል እወቅ!

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

4 Responses to የጃዋር ስኬት እና የፖለቲካ ፈላሻዎች ( ሄኖክ የሺጥላ )

 1. HaileMichael says:

  ውድ ሄኖክ
  አሁን አንተ ልታፈርሰው እየሰራህ ያለህው ብዙ ተደክሞበት ሁለቱን ብሄሮች ማለትም አማራንና ኦሮሞን አግባብቶ ወያኔን መጣል እንዲቻልና ወያኔም ላለፉት 25 አመታት በከፋፍለህ ግዛ መርሁ በሁለቱ መካከል ሲያስነሳ የነበረውን ግጭት ለማብረድ ብዙ የተለፋበት፣የተደከመበትና የተሰራበት ነው፡፡ ምንም እንኳን አንተ ኦሮሞም እንደወያኔ ሁኔታዎች ቢመቻቹለት አማራን ለመጨቆን ብሎም ለማጥፋት ይንቀሳቀሳል የሚል ሀሳብ ቢኖርህም ይህ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ጁሃርም ሆነ ሌላ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ህዝብ አቋም እንዳልሆነ ልትገነዘብ ይገባል፡፡ ይልቅ ይህን በማድረግህ ወያኔን በጣም ያስደነገጠውን የሁለቱን ብሄረሰቦች ጥምረት( በወያኔዎች አገላለጽ የጠባቦችና ትምክህተኞች ጋብቻ) ወደ ኃላ መልሶ ትግሉን በማቀጨጭ ለወያኔ ሰርግና ምላሽ ያደርግለታል፡፡ የመከራ ጊዜያችንንም የትየለሌ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ስጋትህ ለትግሉ እንቅፋት ከመሆንና በብዙ ስራ የተፈጠረውን የጋራ መግባባት ጥርጣሬ ላይ ከመጣል ውጭ ልላ አንድምታ ሊኖረው አይችልም፡፡

  Like

 2. yidh says:

  durom lewere new yetefeterachut bita wera ayidenkenim, be goda mawurat man yibeltachuwar be adebabay yelachum inji amaru@gmail.com

  Like

 3. abe says:

  Congratulation to all Ethio terrorists in America.
  You have inflicted maximum damage on a few hundred thousand Ethiopian grade 12 teenagers. Well done , this is a leap forward for our democracy?

  Like

 4. ወያኔ እብድ ዉሻ says:

  Henok:

  What is wrong with you? How would come so naked with your jealously. Woyane is Ethiopian enemy, as any single Ethiopian elite who has well-grounded knowledge about Ethiopian politics. After woyane, Ethiopians could talk and craft a democratic government that accommodates the woyanes themselves. It seems that you lack any insight about Ethiopian politics and Ethiopian people. That is why you are instigating ethinic confrontation between Amhara and Oromo. That won’t help Ethiopia. Read a little bit and come out when mature enough not to be bloody jealous about hard-working and bright politician’s achievement and monger bloodshed while no one is interested in it. I should call you stupid!

  Jawar: Go Jawar! Oromo is asking its right, not wish to steal others’ interest like Henok and its click. Jawaar go Jawaar! Don’t listen to idiots!

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: