ወደ አውሮፓ የሚፈልሱትን የአፍሪካ ስደተኞች ለማስቆም የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ አምባገነን መሪዎች የገንዘብ ስጦታ መደበ

ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ የሚጎርፉ ሰደተኞችን ለመግታት የአውሮፓ ህብረት ስደተኞቹ ለሚመነጩባቸው ሃገራት መሪዎች ከፍተኛ ገንዘብ ለመስጠት በሚስጥር እየመከረ መሆኑ ተገለጸ።
በዚህም የሱዳኑን አልበሽርን ጨምሮ ማንነታቸው ላልተገለጸ ስምንት የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች 46 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ከ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሰጥ ሲወያዩ እንደነበር ዴይሊ ሜይል የተባለ በእንግሊዝ የሚታተመው ጋዜጣ የጀርመንን መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ በማድረግ በዛሬው ሃሙስ ኣጋልጧል።
46 ሚሊዮን ዩሮ የሚሰጣቸው ስምንቱ አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ወደ አውሮፓ የሚሻገሩትን ስደተኛ እንዲያስቆሙላቸው በስጦታ እንደሆነ ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል። ጀርመንን ጨምሮ በ28 የአውሮፓ አምባሳደሮችን ውይይት የተካሄደበት ይህ እቅድ፣ በምንም መልኩ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆንና መታወቅ እንደሌለበትም ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ከፍተኛ ረዳት የሆኑት ፈደሪካ ሞግኸሪኒ ይህ ውሳኔ በመገናኛ ብዙሃን እጅ ገብቶ በህዝብ ዘንድ ከደረሰ የአውሮፓ ህብረትን ክብር ያጎድፋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
እንደ እቅዱ ከሆነ በሶስት አመት ጊዜ የድንበር ጠባቂዎች ለማሰልጠን እና የስደተኛ ማጎሪያ ካምፖችን ለመገንባት በቂ ገንዘብ እንዲመደብ ስምምነት ተደርሷል። ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያና፣ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚጎርፉ ስደተኞችን ለመቆጣጠር አብዛኛው ግንባታ በሱዳን እንዲከናወን ስምምነት ላይ መደረሱን ተነግሯል። በተጨማሪም የውጭ ስደተኞችን ለመቆጣጠር በተለያዩ ቦታዎች ካሜራ እንዲተከል፣ ሰርቨሮች ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በተለይም በሱዳን እንዲገነቡ የሚዘረዝር ሰነድ እንደተገኘ ደር ሽፒገል (der Spiegel) የተባለውን የጀርመንት ጋዜጣ ጠቅሶ ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና እድገት ሚኒስቴር እቅዱ ትክክል እንደሆነ አምኖ፣ ነገር ግን ፕላኑ እስካሁን ድረስ ተግባራዊ እንዳልተደረገ ገልጿል። የጀርመንት ተራድዖ ድርጅት ጂ አይ ዜድ (GIZ) ጉዳዩን በበላይነት እንዲይዘውና እንዲያስፈጽም ሃላፊነት ተሰጥቶታል ተብሏል።
የአፍሪካ ስደተኞችን ለማስቆም የቀረበው ይህ የሚስጥር እቅድ ተቃውሞ ገጥሞታል። በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደሉ የአፍርካ አምባገነን መሪዎች ለህዝቦች እንቅስቃሴና ዝውውር ቁጥጥር እንዲያደርጉ በአውሮፓ ህብረት መታሰቡ እጅግ የሚሳዝን ነው በማለት ተቃዋሚዎች እቅዱን ኮንነዋል። በጀርመን እርዳታ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ኤክስፐርት የሆኑት ማሪና ፒተር በአካባቢው የጸጥታ ስጋት የሆነና መቶ ሺዎችን ያፈናቀለ አገዛዝ አሁን አካባቢውን እንዲያረጋጋ በአውሮፓ ህብረት መታሰቡ እንዳስገረማቸው ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ኡመር ሃሰን አልበሽርን ጨምሮ እነዚህ መሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በህዝቦቻቸው ላይ በፈጸሟቸው ወንጀሎች ተጠያቂ መሆናቸውን የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መክሰሳቸው ይታወሳል። በተለይም ፕሬዚደንት አልበሽር በሄግ በሚገኘው በአለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዳርፉር በተፈጸመ ዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈለጉ ናቸው። ፕሬዚደንት ኡመር ሃሰን አልበሽር በበላይነት መርተውታል በተባለው በዳርፉር ጥቃት ከ200 ሺ ሰዎች በላይ መገደላቸውንና 2.7 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወቃል።
አፈትልከው የወጡት የስብሰባው ቃለጉባዔና ሌሎች የምስጢር ሰነዶች በጀርመን ሃገር በሚታተመው ደር ሽፒገል ጋዜጣና እርዴ (ARD) በተባለው የህዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ እጅ ገብቷል።

posted by Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: