ሰበር መረጃ በኢቲዮ_ኤርትራ ድንበር ከፍተኛ ጦርነት በነፃነት ዓሎችና በወያኔ ወታደሮች ተካሄደ

74 ከአ/አ ከጎንደር ከሀረር ደቡብ ወዘተ የተሰባሰቡ ነፃነት የጠማቸዉ በምህንድስናና በጤና ድግሪ ያላቸዉ ወጣቶች በኢቲዮ_ኤርትራ ድንበር ከተማ ከትመዋል ወጣቶቹ ከመላዉ ኢ/ያ የተሰባሰቡት ቀጭን ቀጠሮ ይዘዉ ነዉ:: ማእከላዊነት ፈጥረዉ ሁሉም ሌሎች የተቀጣጠሯቸዉን ይጠባበቃሉ:: ከወጣቶች መሀል አንደኛዉ ስልኩ ቢዚ ሆኗል:: ቶሎ ቶሎ ያናግራል:: የሚያወራዉ ስልክ Unknown number ይላል:: ስልኩ ከኢትዮጵያ ዉጭ ነዉ::

”ሃሎ ሃሎ” ይላል ልጁም ተመሳሳይ መልስ ይመልሳል::

”ከርቀት እየተጠባበቃችሁ ተንቀሳቀሱ መንገድ ጀምሩ ስላችሁ ብቻ ወደተከዜ ሰሜን አቅጣጫ ኑ:: የሚመራችሁ ከጀርባዉ የኢትዮጵያ ባንዲራ የተለጠፈበት ወጣት ይመጣል:: እሱ ወደሚሄድበት ተከፋፍላችሁ ከ7 በማይበልጥ ስብስብ ተከተሉት:: አሁን ልጁ ይታያችሁዋል አደል? ጀምሩ!”

አለ የማይታወቀዉ ስልክ ይመጣል የተባለዉ መጣ:: 7 ሰባት እየሆኑ መከተል ጀመሩ:: ጫፍ ላይ ደርሰዋል:: በአካባቢዉ ዝር የሚል የለም:: የሚመራዉ ጠንከር ፈርጠም ያለዉ ወጣት ጃኬቱ ስር ታጥቋል:: ከመቅፅበት ቁም የሚል ከሁለት አቅጣጫ ከአንድ ጥይት ጋር ተሰማ:: የኢ/ያ መከላከያ 24ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አባል ነበር:: ወዲያዉ ቁም ያለዉ ወታደር ተመቶ ወደቀ:: ማን እንደመታዉ አልታወቀም:: ወጣቶቹ ግራ ገባቸዉ:: ተኩስ ከየአቅጣጫዉ ይፈነዳል:: የኢ/ያ ወታደሮች በየቦታዉ ሲወዳድቁ ይታያል:: ጥይት ወደወጣቶቹ አልተተኮሰም::

”ማን ከማን ጋር ነዉ?” ሲል ከፊት የሚመራዉን ፈርጣማ ወጣት ከወጣቶቹ ሲደዋወል የነበረዉ ጠየቀ::

”አይዟችሁ ደርሰዋል:: እኛን የሚመሩን የነፃነት ሀይላችን ሰራዊት ሊያጠቁን ከመጣ ከወያኔ ወታደር ጋር ነዉ የገጠሙ:: ደርሰናል:: ቅርብ ናት የ5 ደቂቃ መንገድ ነዉ የቀረን ጀግኖቹ እየተፋለሙ ነዉ:: እኛ ሰላም ነን… ”…
(የቀጠለ) በርቱ ደርሰናል:: አሀን ያለንበት የኤርትራ ምድር ነዉ:: ቅድም ወንዙን ከመሻገራችን በፊት ያለዉ መሬት ነዉ የኢትዮጵያ:: ዉጊያዉ ያለዉ ከኢትዮጵያ መሬት ነዉ:: አንዱን ሻለቃ የ24ኛ ክፍለ ጦር እያርበደበዱት ያሉት ከ30 የማይበልጡ የነፃነት ጉዋዶቻችን ናቸዉ:: የዉስጥ አርበኞችም እያገዟቸዉ ነዉ:: ገዥ መሬት ስለያዙ ለማጥቃት አይቸገሩም:: ትርርርር ያለ ተኩስ የሚተኩሱት ወያኔወች ናቸዉ እዉር ድንብሱን ተስፋ በቆረጠ መልኩና እየተብከነከኑ ስለሚተኩሱ ድምፁ እንደዛ ነዉ በአንድ ቃታ ነዉ 30 ጥይት የሚጨርሱት:: በፍርሀት ሳያስቡት እኛን ለመብላት ብቻ ስለመጡ ሳያስቡት በገጠማቸዉ ጠንካራ ጡጫ ተደናብረዋል:: ብዙዉን ማጥቃትም መከላከልም አያደርጉም በተለይ እንደዛሬዉ ካላሰቡት:: ወደሀዋላ ነፋስ እየደበደቡ እየተኮሱ ነዉ እግሬ አዉጭኝ የሚሮጡት:: በመትረየስ ሽፋን ጣ….ጣ…ጣ…ጣጣጣ…ጣጣ የሚለዉ ተኩስ ድምፅ ደሞ የኛወቹ የነፃነት ሀይሎች ናቸዉ:: እያዩ ነዉ የሚሮጠዉን የሚቀልሙት:: የወያኔ ወታደር ነፃነት ሀይሎች መጡ ከተባለ ላብ በላብ ነዉ የሚሆኑ:: በፍርሀት ነዉ ቀድመዉ ነዉ የሚሞቱት:: የተማረኩ ወታደሮች የሚሉትም ይሄኑ ነዉ:: በነፃነት ሀይል ባህል ተኩሶ አደለም መሳት ያሰቡት ነጥብ ላይ አለማሳረፍ ያሳፍራል:: ታያላችሁ ማንም ሳይሰዋ ነዉ የሚመለሱት… ለማንኛዉም እኛ ወደካምፕ ተጠግተናል:: በሁለት ተሰለፉ 27 ሀያ ሰባት ሁኑ::” አለ መሪያቸዉ:: የነፃነት ታጋይ አባል:: ወዲያዉኑ የነፃነት ሀይሎች ከርቀት በተረጋጋ መንፈስ ሲመጡ ይታያሉ:: ፈርጣማዉ የነፃነት ሀይሎች አባል አጨበጨበ:: ”ይሄዉ ታጋዮቻችን ሁለት ሶስት ክላሽና መትረየስ እየተሸከሙ ከሄዱት 30 ተራብተዉ 55 ሆነዉ እየመጡ ነዉ:: የነፃነት ሀይል መሸነፍ አያዉቅም:: በተለይ እጅ መስጠት
ጠት አይታሰብም:: (የቀጠለ)…ብም:: ሁሉም በድል ተመልሰዋል:: እዛዉ ስለምንገናኝ እንድረስና አረፍ እንበል:: እንግዲህ ሀያ አምስቱ ተጨማሪወቹ የወያኔ የተማረኩትና የዉስጥ አርበኞች ናቸዉ ማለት ነዉ:: ቃኘዎችና የዉስጥ አርበኞቻችን ነበሩ:: የመሩት እነሱዉ ናቸዉ:: የዉጊያዉን ሁኔታ እስቲ ልጠይቅ…” ብሎ መገናኛዉን አወጣና ነካ:: ”ሀሎ ኦ7 ሃሎ ይሰማል ኦ7 ይሰማል:: ኦ74 ነኝ!” አለ:: ”ከዛኛዉ ማዶም ሀሎ ኦ74 ይሰማል ኦ7 ነኝ በሰላም ገባችሁ? እያየናችሁ
ነዉ:: እኛ በሰላም ተመልሰናል:: የተወሰነ ማርከናል ከ171 በላይ ሙትና ቁስለኛ ተመዝግቧል ከኛ 2 ጉዋዶች በመጠኑ ቆስለዋል:: ሁላችንም ጠመንጃወችና
ትጥቆችን ማርከናል:: የዛሬዉ በተለይ ከንጋጋቱ ያገኘነዉ ድል ልክ የለዉም:: ከባድ ጉዳት ነዉ ያደረስነዉ:: የዉስጥ አርበኞቻችንም ይዘናል:: የተሳካ ነዉ:: በቀን
16/09/2008 ቀንቶናል::” በሉ እዛዉ እንገናኝ ቻዉ ኦ74 ቻዉ ሞርኮ የሚቀበለን ደጀን ሀይል ደርሶልናል:: ሰላም ግቡ ደርሰናል::” ብለዉ ተሰነባበቱ::
በ16/09/2008 ሌሊት ጀምሮ ከመላዉ ኢትዮጵያ ተጠራርተዉ የመጡ ወጣቶችን ወደ ነፃነት ሀይሎች ለመቀላቀል የተደረገ ፍልሚያ በነፃነት ሀይሎች አሸናፊነት ከ171 በላይ የወያኔ ወታደር በመግደልና በማቁሰል የጦር መሳሪያም በመማረክ ነፃነት የጠማቸዉን ወጣቶች በሰላም እንዲቀላቀሉ በማስቻል ተጠናቀቀ::
ህሊና ፀረወያኔዋ

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ሰበር መረጃ በኢቲዮ_ኤርትራ ድንበር ከፍተኛ ጦርነት በነፃነት ዓሎችና በወያኔ ወታደሮች ተካሄደ

  1. abe says:

    Harif Dirset new.
    You should develop it into a book. Yimechih.

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: