በሱዳን የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሰቆቃ!

ቅዳሜ ፡ ማያዝያ ፩ ቀን 2008 ዓም ቅፅ 16 ቁጥር 847 በጫት መቃም ወንጀል እስከ 20 ዓመት የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን በሱዳን ይላል የውድ እህቴ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ዘገባ በአዲስ አድማስ እንዳነበብኩት። ግን እስረኞቹ 20 ሳይሆኑ ከ70 በላይ ናቸው በሱዳን ያሉ ከባድ ፍርደኛ ፡ከ10~20 ዓመት ፍርድ የተበየነባቸው ኢትዮጵያውያን። እኔ በኣካል እማውቃቸው እንኳን በካርቱም 51 በወህኒ ኣል ሁዳ ብቻ። በፖርትሱዳን  14 በከሰላ 1 በገዳሪፍና መደኒ ቁጥራቸው በተጨባጭ ኣላቀውም። እነዚህ ግን ከባድ ፍርደኛ ናቸው ኣስተውል 70ዎቹ ከባድ ፍርደኛ ብቻ ናቸው። በሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ 5 ወህኒ ቤት ኣሉ ኮበር፡ እምዱርማን፡ ሶባ፡ ደበክ እና “ኣል-ሁዳ” ይባላሉ። ወህኒ እምዱርማን የቀላል ፍርደኛ ከሁለት ዓመት በታችና ምን ይሁን ምን ፍርዳቸው ብቸኛው የሴቶች ወህኒ ነው። ኮበር፦ የፖለቲካና ከባድ ፍርደኛ እንዲሁም በሱዳን ኣራተኛው / ፖርትሱዳን፡ መደኒ፡ ኡበይድ / የሞት ፍርደኞች ማነቅያ መሳርያ ያለበት ግቢ ነው። ሶባ፦ ቀላል ፍርደኛ ከሶስት ዓመት በታችና የቼክ ማጭበርበር ወንጀል የተከሰሱ ይታሰሩበታል። ደበክ፦ ለጉልበት ስራ ሚያስፈልጉ ቀላል ፍርደኛ / ለባለ ስልጣኖች ቤት መገንብያ ” ጡብ ” ከዚሁ ነው ሚመረተው። ከከተማ ወጣ ብሎ ናይል ዳር ነው።/ ይታሰሩበታል። ወህኒ ኣል-ሁዳ ፦ በሱዳን ሃገር ውስጥ ግዙፍ ወህኒ ቤት ነው። ባለ 140 ማሰርያ ክፍሎች ያሉት……እያንድ ኣንዱ ክፍል 75 ሰው እንድይዝ 25 ኣልጋ ባለ 3 ደረጃ መላውን ክፍል የተማላለት………10500 / ኣስር ሺህ ኣምስት ሞቶ / እስረኞች እንድይዝ ተብሎ የተገነባ ነው። ይህ ወህኒ ከካርቱም ወደ ሰሜን ሱዳን ዱንጉላ መውጫ በስተ ግራ በኩል ” ሱግ ሊብያ ” ከሚባል ገበያ ማእከል ፡ እንደ መርካቶ፡ ኣለፍ ብሎ ይገኛል። በሰባት ንኡስ ግቢ እይንድ ኣንዱ በ20 ክፍል የሚገኝ ሲሆን……በተለያየ ወንጀል ከቀላል እስከ ከባድና በቼክ ማጭበርበር እንዲሁም የሞት ፍርደኞችም በውስጡ ኣቅፎ ይዘዋል። ከሱዳን በህገወጥ መንገድ ሃገሬ ገባቹ ተብሎ በሃገሪቱ ኢምግሬሽን ተከሰው ስደተኛ በመሆናቸው ብቻ ከ3000-5000 የሱዳን ፓወንድ እንዲቀጡ ኣልያም ክፍያው ከሌላቸው እስከ ስድስት ወር ታስሮ ወደ ኢትዮ፡ሱዳን ደምበር መተማ ዮሃንስ እንዲባረሩ ተወስኖባቸው ሚዳጎኑት ከዚሁ ወህኒ ነው። የሚደርሳቸው በደል ግፍ ፡ግርፍያና ዝርፍያ ከዚሁ ለመፃፍ ብሞክር ስቃያቸውን ማሳነስ ነው ሚሆነው። ምክንያቱ ተዘርዝሮ ኣያልቅም የመከራቸው ፅዋ። ባለፈው ዓመት ከተከሰተው በጣም ከባዶች ክስተት ብገልፅ እንኳን ዓርብ 3; 12; 2005 ዓም / 9; 8; 2015 እአኣ ነው። በህገወጥ መንገድ ሃገሬ ገባቹ ብሎ የከሰሳቸው ኢምግሬሽን ሱዳን የክፍያ ቅጣት ወይም የሶስት ወር ፍርድ ተበይኖባቸው ……የወርሃት ፍርዳቸው ጨርሰው ከ3 ቀን በፊት መተማ ዮሃንስ መግባት የነበረባቸው ዜጎች ……የሃገሪቱ ፓሊስ ፍርዳቸውን ከጨረሱ በሃላ እንዳይወስዳቸው የበዓል ምክንያት ኣድርጎ……ከበዓል ሳምንት በሃላ እንዲወስዳቸው ያለፍርድ መቀመጣቸው ሳይበቃ……በዚሁ ዕለት ሚያነጋ / ሓሙስ 2; 12; 2005/ 8; 8; 2013/ ለሊት መብራት ቆርጣ ስለነበር /በነገራችን ላይ ሱዳን ወህኒ መብራት መጥፋት ክልክል ነው። ካላቀረጠች በቀር……ግብረ ሶዶማውያን ስለሆኑ ነው / በእንቅልፍ እያሉ የለበሱትን ሱሪ ከስተ በሃላ በምላጭ ቀደው ለኣራት ሁኖ ሱዳኖች ደፍረዋቸው ኣደሩ። ኣንድ የኣ፡ኣ ልጅና ኣንድ የስሜን ጎንደር ናቸው።” ለክብራቸው ብየ እንጂ ስማቸው ከኔ ጋር ኣለይ ዲያሪ ውስጥ ስለምፅፈው። “” በወቅቱ ለኢትዮ፡ኣምባሳደር በካርቱም ኣቶ ኣባዲ ዞሞ ደውለን……ኢትዮጵያኖች በሁዳ ወህኒ ተደፍረዋል ስንለው………በትልቁም በትንሹም እየደወላቹ ኣትረብሹኝ ነበር መልሳቸው ……የኣምባሳደሩ። ወገን ክብሩን ተደፈረ ትንሽ ነገር ነው በሳቸው። … ሌላው፦……ሮቡዕ 13; 9; 2006 ዓም / 21; 05; 2014 እአኣ ነው……በካርቱም ህገወጥ ስደተኛ ተብለው ከ400 በላይ ኢትዮጵያኖችና ኤርትራኖች በዚሁ ወህኒ ውስጥ ታጉረዋል። ቢሆንም በወርሀ ጉንበት የሱዳን ሃገር ሙቀት ኣደለም ከወሃ ተለይተህ እንደ ኣሳ ባህር ውስጥ ብትጠልቅ ኣያረካም። መስኪኖች ሃበሻ ግን……ከሶስት ቀን በፊት ሰኞ 11; 9; 2006 / 19; 05; 2014 ለሊት ኣምጥተው በኣራት ክፍል ውስጥ / ከተሰራበት ዓቅም በላይ/ ኣጉሮው …እስከ ንጋት ሮቡዕ ያለውሃ ስለተዘጉ……ጥዋት ሮቡዕ ቆጣሪ ታረኛ መኮነን ክፍል ውስጥ ከ30 በላይ ሃበሻ / ኢትዮም፡ ኤርትራም/ ራሳቸው ስቶ ወደቆ ስላኣገኝዋቸው ………በሱዳኖች እስረኛና ኣቅማቸው ደህና የነበሩ ሃበሻ ኣሸክመው ወህኒ ግቢው ውስጥ ካለ ህክምና ለጤና እርዳታ ኣደረስዋቸው። ቢሆንም ግን………18 በቀላል እርዳታ ተሽላቸው ከግቢው ህክምና ሳይወጡ ወደ መታሰርያቸው ክፍል ሲመለሱ……3 ሃበሻ በግዜው ሂወታቸው ኣጡ። የቀሩት ወደ 12 ሚሆኑት ደግሞ ለተሻለ የጤና እርዳታ ወደ ካርቱም መሃል የሚገኘው ሆስፒታል “” መስተሽፋ ኣል-ሹርጣ “” / የፓሊስ ሆስፒታል ማለት ነው።/ በወህኒ ቤቱ ISUZ / ደፋር ትባላለች በሱዳንኛ/ ተጭነው ከተወሰዱ በሃላ …ዳግም ወደ ወህኒ ኣልተመለሱም። ተሽላቸው ወደ መተማ ዮሃንስ ይሸኙ ወይስ የሶስቱ ወገናቸው እጣ ፈንታ በነሱ ይድረስ …………… በወቅቱ ከጥዋቱ 4:00 ኣከባቢ ለኢትዮ፡ኤምባሲ ደውለን ብናስታውቅም ……የሃገራችን ኤምባሲ ሰራህተኛ በካርቱም ወገኑን ለመጠየቅ በጣም ፈጥኖ በእጁ ያለ ስራ ጥሎ……በሁለተኛው ቀን ሓሙስ 14; 9; 2006/ 22; 05; 2014 የደረሰላቸው። ይህ በየቀናትና ሳምንት ልዩነት እየተገፈፉ ከታጎሩ በሃላ የእጅ ጌጥ ካትም፡ቀለበት፡ብራስለት እንዱሁም ደህና የሆነ ጫማ ይሁን ልብስ፡ቀበቶ በዋናው ደግሞ ኪሳቸው ውስጥ ሚገኝ ጥሬ ገንዘብና ተንቀሳቃሽ ስልክ መዘረፍ ፡ መደብደብና ለሁለት ሰው በኣንድ ምላጭ መላጨት / ምላጭዋን ለሁለት ይሰጡና በኣንድዋ ገፅ ኣንተ ላጨው……ቀጥሎ የተላጨሀው ትነሳና በሁለተኛዋ ገፅ የለጨህን ወንድምህ ትላጫለህ/ ይህን ነው የሱዳን ግፍ……የኢትዮጵያ ሚድያና ውጭጉዳይ መስራቤት እህት ወንድም ሃገር የሚላት ሱዳንና ሱዳኖች። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ከባድ ፍርደኛ ወጣቶች ከዚሁ ወህኒ ውስጥ ናቸው። ከ10 እስከ 20 ዓመት ፍርደኛ በጫትና ሻሸመኔ / ገንጃ/ ወንጀል ተከሰው። እንዲሁም ኣንድ የሞት ፍርደኛ ጨቅላ የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዚሁ ወህኒ ይገኛል። እስረኞቹ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በካርቱም በተደጋጋሚ የሚደርስባቸው በደል ግፍ፡ ድብደባና የስነኣእምሮ ጫና፡ የባህልና ሃይማኖታዊ ተፅእኖ እንዲሁም ቤተሰብና ወገን ከምናገኝበት ሃገራችን ቢሆንም ዝውውር ተዶርጎልን በሃገራችን እንታሰር ቢሉ……ኤምባሲው እንደ መስቀል ወፍ በየዓመቱ ኣንዴ ብቅ እያለ ምንም መፍትሄ ሳያመጣ በተከታታይ ኣራት ዓመት / 2005 ዓም ጥር ወርህ ፤ 2006 ዓም መጋቢት ኣከባቢ ፤ 2007 ዓም ግንቦትና 2008 ታህሳስ ወርሃት ላይ እየተመላለሰ ኣንዲት ቁምነጋር ሳይሰራ ማይፈፅመውን ቃል እየገበ ይጠፋል። በዞንድሮ የእስረኛ ጉብኝታቸዉ ኣቶ መሓመድ ጡፋ ፤ ዲፕሎማት ኣቶ ኣረጋ ካሳና ኣምሳሉ እንዲሁም ከኢትዮጵያን ኮሚኒትዎች ሸኽ ዳውድ እና ሌሎች የኤምባሲው ስራ ባልደረባ ሲጎበኝዋቸው……ከተሰበሰቡት እስረኛ ከፍ ያለ ወቀሴታና መፍትሄ ቢስ ስለሆኑ እንድትመጡን ኣንፈልግም በጭራሽ፡ መፍትሄ ለማትሰጡን ጉዳይ በዓመት ኣንዴ ብቅ እያላቹ በስማችን ኣትነግዱ / ምክንያቱ ወደ ወህኒ በሄዱ ቁጥር ለእስረኛ ተብሎ መዋጮ ስለሚያደርጉ…የባህል ዝግጅት ኣድርገው ገቢ ያሰባስባሉ…ከኮምኒቲው ካዝናና ከኤምባሲው ካዝና ወጪ ያደርጋሉ……ለእስረኞች ግን የመጀመርያዋ በነበረች ጉብኝታቸው በ2005ጥር ወርህ የቦንዳ ልባሽ ጨርቅና የውስጥ ነጭ ትሸርት ኣዲሶች በስተቀር ኣንዲት ቅንጣት ነገር ይዞውላቸው ቀርቦ ኣያውቁም። / የግዳስ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በበለጠ በዓብይ ፆም ግዜ ስካር፡ የሚበጠበጥ ጁስ፡ የሃበሻ እንጀራ ከትንሳኤ በሃላ በግድፍት ወጥ፡ በብርድ ወቅት ብርድልብስና ቅያሪ ልብሶች፡ ትሸርትና የውስጥ ሱሪ ሳይሸከሙ እስረኛ ለመጠየቅ ኣይመጡም / የኢትዮ ኤምባሲና ስሙ ብቻ የኢትዮጵያውያን የሆነ ካርቱም 3 ያለው መድህነኣለም ቤተክርስትያን ኣንድም ቀን እስረኞች ጠይቆ ኣያውቅም። ኢትዮጵያኖቹ ወጣቶች እስከ 13 ዓመት ከዚሁ ወህኒ የቆዩ ኣሉ። ከኢትዮጵያ ልዓላዊ መሬት ዓብደራፊዕና ኣልመሃል ታፍነው 20 ዓመት የተፈረዱ ኣሉ። ሁሉም ንፁሃን ከወንጀል የፀዱ ባይሆኑም ያለወንጀል ተይዘው የፍርዳቸው ክትትል የህግ ጠበቃና የቋንቋ ኣስተርጋሚ ባለመኖሩ 20 ዓመት የተፈረዱ ኣሉ። ኡ …ኡ…ኡኡ ቢሉ ሰሚ ወገን ያጡ ከኤምባሲም ይሁን ከሚመለከተው ኣካል የውጭጉዳዮች ሚኒስተር እኒህ ኢትዮጵያን ወጣት ከኣማራ፡ትግራይ፡ኦሮሞ፡ዓፋርና ደቡብ ጉራጌ ሲሆኑ………ወገኔ ብሎ ሃገራቸው ገብቶም ፍርዳቸው እንዲጨርሱ ኣለኝታ ያጡ ናቸው። ከዚሁ የሚደርሳቸው የስነኣእምራዊ፡ ሞራላዊና ሃይማኖታዊ ተፅእኖ……… ለክርስትና እምነት ተከታዮች እምነታችሁን ከቀየራቹ ወደ እስልምና ገብታቹ ቁርዓን ኣጥንታቹ ካለፋቹ እንፈታቹ ኣለን ተብለው ሶስት ኢትዮጵያን ኣስልመዋል። እንዲሁም ሌላው እነሱን ተከትሎ እንድያ ኣሰልም ብለው በእስልምና ቦጎ ኣድራጊዎች የመንግስት ኣካል ኣንዱ የሆነው “” ዴዋን ኣል ዘካ “” ሙሉ ወጪ ተደርጎላቸው በወህኒ ውስጥ ከደጅ ያሉ ሻሂ ሚሸቅጡ ሃበሻ ኣምጥቶ ድሮውላቸው……ለባለ ቤታቸው ወርሃዊ ክፍያ ይሰጣሉ ………የቀረው እንዲከተል። …ሌላው የጉሙዝ ብሄር ተወላጅ የሆኑትን ወጣት ኢትዮጵያን ……ጉሙዝ በሙሉ ሙስሊም ነው። መስገድ ኣለባቹ፡ ኣረብኛ ተማሩ ቁርዓን ኣጥኑ እያሉ በልብስና ጥቅማጥቅም እየደለሉ መላው የጉሙዝ ብሄር ተወላጅ የነበረም ያልነበረውም ሰጋጅ ኣድርጎውታል። ……ከባዱ ነገር፦ በሱዳን ውስጥ ግብረ ሰዶም እንደባህል ነው። ኣባት ልጁን ኣምኖ ከኣጎቱ እቅፍ እንዲተኛ ኣይፈቅድለትም። ይህ ሠው ግብረሰዶማዊ ነዉ ሲባል እንደምንም ማይቆጥሩት ነው። በዚሁ ኣስነዋሪ ተግባር የሱዳኖች የቀን ተቀን መመልከቱ ሰቀቀን የሆነባቸው እነዚህ እስረኞች ጭሆታቸውን ማን ይስማ። በጣም ሚያሳዝነው በዚሁ ኣስፀያፊና ኣስነዋሪ ስነምግባር ኣንድ ወገን ተብከሎብናል። የሌሎች እጣ ፈንታ ነገስ……… ይህ ወጣትስ ፍርዱ ጨርሶ ሃገሩ ሲገባ ለሌላው ትውልድ ወገን ኣለማስተላለፉ ምን ዋስትና ይኖረናል። ……ከታሰሩት ወገን የእሳላም ስጋ ስለማይበሉ ሚቸገሩትስ። ለግብፆች ኮፕቲክ ቤተክርስትያን ነግረው በሁለት ወር ወይም 3_4 ወር ሲመጡ ሽሮ ይዘውላቸው ሲመጡ የመድህነኣለም ቤተክርስትያን ግን ሂዶ ቡራኬ ለመስጠት እንኳ ፊታቸው ኣላየም። ከእስረኞቹ ስጋ ስለማንበላ ወጥ ሰርተን ምንበላበት ለእህል ወጥ የሚሆን ኣደስ ወይ ደግሞ ሩዝ ነገር ይሰጠን ብሎ ለፖሊስ ሲያመለክቱ……ኣደሱም ሩዙም ሆነ ሽንጉርቱ በሙስሊም ብር ነው የተገዛ ……ካስፈለገህ ብላ…ኣልያም ወጪህን ራስክን ቻል ተብለው ከቤተሰብ ብር እየተላከላቸው ታስረው ራሳቸውን እየከፈሉ የሚቀለቡ ኢትዮጵያን ወጣቶች የመጀመርያ ሳይሆኑ ይቀራሉ በዓለም። ኤምባሲው ግን ይህን እያወቀ ሰባእዊ መብታቸዉ ሊያስከብርላቸው ቀርቶ……እስረኛ ኣደለህም እንዴ ስጋው ብትበላው ምንችግር ኣለው ነው ያሉት። ……ጓደኛ ዘመድ ለመጠየቅ ሲመጣ ……ከተጠያቂው እስረኛ ብር ካልሰጠሀን ኣንወስድም ወደ እስረኛ መጠየቅያ ቦታ። ……ከጠያቂው ደግሞ ብር ካልሰጠሀን…ብለው ኣንተ ከወንጀሉ ሽርካ ነበርክ ኣደል……የመኖርያ ፍቃድ ወረቀትህ ግዜው ኣልፎበታል ለኢሚግሬሽን እናስክብሃለን እያሉ ብር ይዘርፈሉ……ጠያቂው ዘመድ ጓደኛ እንዲጠይቅህ እየፈለገ ምንያድርግ???………… ከራስ በላይ ንፋስ ነው። ኣንተን ብሎ እሱ ይገባል ይንገላታል ኣ ሌላው በእስረኛው ሱዳኖችና ጠባቂ ፖሊሶች ከኣቅም በላይ ዘለፋና መድልዎ ይደርሳል። ኣሁንም የእስረኞቹ ጩሀት ኣንዲትና ኣንዲት ብቻ ናት ………እባካቹ ባይሆን ሃገራችን እንድንታሰር ዝውውር ይደረግልን ነው። እኛ ከዚሁ ቁጭ ብለን ትላንት እንደሃገር ነፃነትዋን ተጎናፅፋ ራስዋን የቻለች ደቡብ ሱዳን እንኳ ዜጎችዋን በድፕሎማስያዊ ግንኝነት ዝውውር ኣድርጋ ሃገራቸው ወስዳ ለቀቀች ። በመጋቢት 2005 ከ40 በላይ ኣብሮ የነበሩ ደቡብ ሱዳኖች ሲለቀቁ። ለኛስ ወገን ሃገር የለንም?????? …በዓርብ 14; 06; 2006 ዓም/ 21; 02; 2014 እአኣ/ የሱዳን የሆነው Blue Nile BN TV የረፋዱ ኤፍ ኤም ዝግጅቱ 4:00 ላይ እንደ ኢትዮጵያን ሰዓት ……በዜና ከኢትዮጵያ የነበሩ በተለያየ ወንጀል ከተለያየ ኣከባቢ ታስረው የቆዩ ሱዳኖች በዲፕሎማስያዊ ግንኝነት ኣስመለስኩ ብሎ ዜና ሰርተዋል / BN TV ኣርቺቭ ተመልከተው በገለፅኩት ቀን/ ታድያ ለኢትዮጵያውያን ዲፕሎማስያዊ ግንኝነት ተረዳድቶ ሃገራቸው ሚያስገባ መንግስት ወገን ይጥፋ…… በተቻላቹ ድምፃቹን ኣሰሙላቸው የሃገሬ ጋዜጠኞች የኣምድ ተሳታፊዎች። ለኣሁኑ ካርቱም ወህኒ ኣል ሁዳ ያሉት ኢትዮጵያውያን የፍርዳቸው ዝርዝር ይህን ይመስላል። ወህኒ ኣል ሁዳ ያሉት ብቻ ነው እነዚህ። ስም ዝርዝራቸው ሚፈልግ ሰው ለመስጠት ዝግጁ ነይ። በድብቅ ሞባይል ስልክም ይጠቀማሉ በቪድዮ ኮል ኢሞ መገናኘት ይቻላል። በሻሸመኔ / ጋንጃ / ተከሰው 20 ዓመት የተፈረዱት 31 ወጣት ሲሆኑ…10 የተፈረዱት ደግሞ 4 ወጣት ናቸው። በጫት ተከሰው 20 የተፈረዱት 7 ወጣት ሲሆኑ 10 ዓመት የተፈረደባቸው 4 ወጣትና የኣምስት ዓመት ፍርደኛ በጫት ደግሞ ሁለት ኢትዮጵያውያን ናቸው። በሻሽመኔ / ጋንጃ / ወንጀል የተፈረዱ ጠቅላላ 35 ወጣት ሲሆኑ። በጫት ወንጀል የተፈረዱት ጠቅላላ 13 ናቸው። በጠቅላላ ከባድ ፍርደኛ 48 ወጣት ኢትዮጵያውያን በሁዳ ወህኒ ኣሉ። ኣንድ ደግሞ የሚታነቅበትን ቀን የሚጠባበቅ የሞት ፍርደኛ……ኣዋጁ ኣቅናው ሙላት የተባለ የ22 ዓመት ጨቅላ ከዚሁ ኣል ሁዳ ወህኒ ኣለ። ካስፈለገ ፎቶ ጭምርት መላክ እችላለሁ የኣዋጁ። በነገራችን ላይ……ያለፍነው ወርህ መጋቢት መጀመርያው ኣከባቢ ኣንድ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ የሞት ፍርደኛ ኣንቀውታል። መልካሙ ታደሰ ወንድምነህ ይባላል የሱ ፎቶ ጭምርት ኣለ። ወገን ለወገን ነውና በተቻለው መጠን ጭሆታቸው እናሰማ። ባይሆን ሃገር ቤት ገብቶ ለመታሰር።

pen Ethiopia

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: