በወልቃይት ቃብትያ አካባቢ አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ

aseac

ሰሞኑን በትግራይ ክልል ስር በሚገኘው የቃብትያ አካባቢ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች በክልሉ ላለመተዳደር የወሰዱትን የቃለ መሃላ ውሳኔ ተከትሎ በአካባቢው አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ።
ትላንት እሁድ የወልቃይት ተወላጆች በውሳኔያቸው ዙሪያ ለመምከር በተሰባሰቡ ጊዘ የአካባቢው የጸጥታ ሃይሎች የማስፈራሪያ የተኩስ እርምጃ መውሰዳቸውን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
የጸጥታ ሃይሎች በነዋሪዎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎም በአካባቢው ትምህርትና የሌሎች የመሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጡን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
በአካባቢው ባሉ የወልቃይት ተወላጆች ላይ የተከፈተውን የተኩስ እርምጃ በመስማት ሌሎች ነዋሪዎች ከአጎራባች ስፍራዎች ቢመጡም የጸጥታ ሃይሎች ወደ ቃብቲያ እንዳይገቡ ማድረጋቸውን እማኞች አስረድተዋል።
ባለፈው ሳምንት በቃብቲያ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች በትግራይ ክልል ስር አንተዳደርም ሲሉ አዲስ ውሳኔ ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
ወደ 4 ሺ ሰዎች በተገኙበት በዚህ የቃለ-መሃላ ስነ-ስርዓት ተወላጆች ባህላቸውንና ታሪካቸውን ጠብቀው በአማራ ክልል ስር ለመተዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ለዞኑ አስተዳደር ማስታወቃቸውን ነዋሪዎቹ ለኢሳት አስረድተዋል።
ይሁንና የቃብቲያ አስተዳዳሪዎች በነዋሪዎቹ የተካሄደን ውሳኔ ተከትሎ በወልቃይት ተወላጆች ላይ የቅርብ ክትትልንና ቁጥጥርን እያደረጉ እንደሚገኝ ከነዋሪዎቹ ለመረዳት ተችሏል።
ልዩ ሃይል በአካባቢው ሰፍሮ መሰንበቱን የገለጹት ነዋሪዎች ጉዳዩ የሚመለከተው የፌዴራል መንግስት ችግሩን በድጋሚ እንዲመለከትላቸው ጠይቀዋል።
ሰሞኑን ቃለ-መሃላ ውሳኔን ያስተላለፉት የቃብቲያ ተወላጆች በአሁኑ ወቅት የራሳቸው ኮሚቴ በማቋቋም ራሳቸውን ለማስተዳደርና ከትግራይ ክልል ስር የሚመጣን መመሪያ ላለመቀበል መወሰናቸውም ታውቋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: