የኢህአዴግ ጉባኤ የፍትህ ሚንስትር የነበሩትን አቶ ጌታቸው አምባዬን ‹‹ዋና አቃቤ ህግ ››በማድረግ በዕጩነት አቀረበ

ፓርላማው (የኢህአዴግ ጉባኤ) በሙሉ ድምጽ በዛሬው ዕለት የፍትህ ሚንስትር የነበሩትን አቶ ጌታቸው አምባዬን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ‹‹ዋና አቃቤ ህግ ››በማድረግ በዕጩነት ማቅረባቸውን አጽድቋል፡፡ይህው ፓርላማ ጌታቸው ይመሩት የነበረውን ፍትህ ሚንስትርን ማፍረሱን ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡
የፌደራል አቃቤ ህግ በተቋም ደረጃ ራሱን ችሉ እንዲቋቋም አዋጅ ሲወጣለትም ዋና አቃቤ ህጉ ከፖለቲካ ሹመት ውጪ እንዲሆን ብዙዎች ቢወተውቱም ጌታቸው ቁጢጥ ብለውበታል፡፡
ቀድሞውኑ በፖለቲካ ወገንተኝነታቸውና በብአዴን /ኢህአዴግ አባልነታቸው ፍትህ ሚንስትርን እንዲመሩ በጠቅላይ ሚንስትሩ ዕጩ ተደርገው በፓርላማው ሹመታቸው የጸደቀላቸው የፖለቲካ ሹሙ ጌታቸው መለዩዋቸውን ሳይቀይሩ ስሙን ወደለወጠው አቃቤ ህግ ዝውውር እንዲያደርጉ ተደርገዋል፡፡ትናንት በፍትህ ሚንስትር ወንበር ተቀምጠው ፍርዱንም ክሱንም አንዴ ሲያቋርጡ ሌላ ጊዜ ሲያዝረዝሙ የከረሙት ጌታቸው ከዛሬ ጀምረው ደግሞ የፌደራል አቃቤ ህግ ተቋምን በመምራት ‹‹በከሳሽነት›› ለድርጅታቸው ያላቸውን ወገንተኝነት ያሳያሉ፡፡ከዚህ በላይ ምን ተጣጣፊ አክሮባቲስት መሆን ከወዴት ይገኛል?
አቃቤ ህግ ህገ መንግስቱን ጨምሮ አገሪቷ የተቀበለቻቸውን ህጎችና ሌሎች አዋጆችን በመንተራስ ህግ የተላለፈን አካል እንዲከስና ለተበደሉም በህግ ፊት እንዲቆም በሌሎች አገራት እምነት የሚጣልበት ቢሆንም ኢህአዴግ ዘንድሮም ‹‹ሰማይ አይታረስ መንግስት አይከሰስ››ከሚል ብሂል ባለመላቀቁ የድርጅቱን አባል ዋና ከሳሽ በማድረግ አስቀምጧል፡፡እናስ ኢህአዴግ በጌታቸው እንዲከሰስ ወይም የስርዓቱ ቁንጮዎች በዋና አቃቤ ህጉ እንዲከሰሱ ማን ሊጠብቅ ይችላል?

Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: