ኢትዮጵያ ዘንድሮም በእስረኛ ብዛት ከአፍሪካ በሁለተኛነት እየመራች ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ ዘንድሮም በእስረኛ ብዛት ከአፍሪካ በሁለተኛነት እየመራች ነዉ፡፡ ደቡብ አፍሪካን ተከትላ፡፡ ከ111 ሺህ በላይ እስረኞች አሏት፡፡ ይህ በይፋ የሚታወቀዉ ነዉ፡፡…
ጦላይና ሁርሶን በመሳሰሉ ትላልቅ የጦር ሠፈሮች(ካምፖች) ዉስጥ በ‹‹ተሐድሶ››ስም ያለፍርድ የታጎሩትን ፣ በፊንፍኔና ሌሎች ከተሞች ዉስጥ በሚገኙ የደህንነት እስር ቤቶች ታፍነዉ ያሉትን፣ በየቀበሌዉና በዞን እስር ቤቶች…በቤታቸዉ ታስረዉ ያሉትን መረራ ጉዲናንና በቀለ ነጋን…እንዲሁም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን አይጨምርም፡፡
World Prison Brief የተሰኘዉና የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለዉ ድርጅት ባለፈዉ ዓመት ባወጣዉ ዘገባ ኢትዮጵያ ያላት እስረኛ ብዛት 93000 ያህል ሲሆን በዚህ ዓመት 18000 ያህል ጭማሪ አስመዝግባለች፡፡ የአምስት ዓመቱ የልማት መርሀግብር አካል መሆኑ ነዉ፡፡
በምጣኔ ሀብት እድገት የዓለም ቁጥር አንድ የሆነችዉ አሜሪካ በእስረኞች ብዛትም ዓለምን ትመራለች፡፡ የ2.5 ሚሊዮን በላይ እስረኞች ሀገር ናት፡፡
ሁለት ዜጎቿን ብቻ ዘብጥ(ጢ)ያ በማስገባት የመጨረሻዉን ደረጃ የያዘችዉ ሀገር ሳን ማሪኖ ናት፡፡ ምስኪን…
ይኼ የጠባቡ እስር ቤት ዘገባ ነዉ፡

Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: