በደቡብ አፍሪካ ጆሓንስበርግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተነሳው ብጥብጥ አልበረደም/ቤተ ክርሲያኗ በዋነኛነትበሶስት ወገን ተከፋላ ጸብና ክርክርን ለማስተናገድ ተገዳለች

 

Aseged Tamene

አርብ ግንቦት 5 እረፋዱ ላይ ነበር አቡነ ያሬድ ጆሓንስበርግ የደረሱት ሶስት የተለያየ ግሩፕ በየግሉ ሊቀበላቸዉ ቢሄድም አቡኑ የመረጡት ቤተ ክርስቲያን የላከቻቸዉን ግለሰቦች ነበር። ኢትዮጵያ በሚገኘዉ ሲኖዶስ ዉስጥ ታላቅ ስፍራ የሚሰጣቸዉ አባት በጆሐንስበርግ ግን የጠበቃቸዉ ሌላ ነበር። ለቤተ ክርስቲያኗ መታመስ ምክንያት ናቸዉ የተባሉትን አስተዳደር አባ ጾመ ልሳንን እንዲተኩ በሲኖዶስ የተመረጡት አቡነ ያሬድ” የመጣሁት ለ10 ቀናት ብቻ ነዉ ዋናዉ አላማዬም እንደቤተክስቲያን ደንብ አባ ጾመ ልሳንን ወደ ሐገር ቤት ይዤ እንድሄድ ነዉ ” ቢሉም አባ ጾመ ልሳን በበኩላቸዉ አሻፈረኝ ብለዋል ” ምንጮች እንገለጹት አባ ጾመ ልሳን እንደ ዋና ህሳቤ አድርገዉ ያቀረቡት በቀድሞ የሰበካ ጉባኤ አባላቶች የተከፈተ የፍርድ ቤት  ክስ ገና አለመዘጋቱና ቀጠሮዉ ያለመድረሱን ተገን ያደረገ ሲሆን።

ቤተ ክርሲያኗ በዋነኛነት በወያኔ ክንፍ በሚመራዉ ቡድን . . .ሰበካ ኡባኤና መዘምራንን ባካተተ ቡድን እንዲሁም አባ ጾመ ልሳንን በሚደግፍ ቡድን በሶስት ወገን ተከፋላ ጸብና ክርክርን ለማስተናገድ መቻሏ በአብላጫ ምእመናንንን ኢጅግ እያሳዘነ ይገኛል።

በመሆኑም ኢነዚህ ተቃራኒዎች በናንትናዉ እለት ቤተ ክርስቲያንን በከፋ ሁኔታ አምሰዋታል። በተለይም አዲስ ተሹመዉ የመጡትን አቡነ ያሬድንም አንቀበልም የርሶም አመጣጥ ትክክል አይደለም በማለት በአንደኛዉ ቡድን በኩል አታካሮ የተነሳ ሲሆን አቡነ ያሬም የመጡበትን የሹመት ደብዳቤ አላሳይም በማለት ዝምታቸዉን አሰምተዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: