የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅት ታንዛኒያ 74 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸዉ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠየቀ

የታንዛኒያ ኢሚግሬሽን ጉዳይ በኪሊማንጃሮ ግዛት በቁጥጥር ስር የሚገኙ 74 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸዉ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻች የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅት (IOM )ጥሪ አቅርቧል።
ፍልሰተኞቹ በታንዛኒያ ዉስጥ በህገ-ወጥ ዝዉዉር ታስረዉ የእስር ጊዜያቸዉን የጨረሱ ሲሆኑ፤ የታንዛኒያ መንግስት ከ3 ሳምንታት በፊት በኬንያ ድምበር በኩል ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ ቢሞክርም የኬንያ የድመበር ጠባቂዎች ኢትዮጵያዉያኑን ወደ ኬንያ ድምበር እንዳይገቡ ከልክሏቸዋል።
ፍልሰተኞቹ ወደ ኬንያ እንዲሻገሩ ታቅዶ የነበረዉ በኬንያ – ታንዛኒያ ድምበር በምትገኘዉ ታቬታ ግዛት ነበር። በግዛቱ አንድ የመንግስት ኃላፊ፣ “እነዚህ ኢትዮጵያዉያን መመለስ ያለባቸዉ ወደ ሃገራቸዉ ኢትዮጵያ እንጂ ወደ ኬንያ አይደለም፣ የታንዛኒያ መንግስት ያንን ማድረግ ሲገባዉ ወደ ኬንያ መንግስት ፍለሰተኞቹን መጣሉ ተገቢ አልነበረም” ሲሉ ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።
በታንዛኒያ የኪሊማንጃሮ ክልል የኢሚግሬሽን ኃላፊ የሆኑት ማንኩጉ እንዳሉት ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሃገራቸዉ ለመለስ የታንዛኒያ መንግስት በቂ ባጀት ስለሌለዉ በዳረ ሰላም የሚገኘዉ ዋና ቢሮዋችን የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅትን (IOM) እርዳታ ጠይቀዋል በማለት ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።
የፍልሰተኞቹ ጉዳይ የሚመለከተዉ በኬንያ ናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በበኩሉ ስለፍልሰተኞች ሰምቻለሁ በእርግጥ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን በማጣራት ላይ ነን ብለዋል አቶ አንዳርጉ በርሄ በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሁለተኛ ጸሃፊ።
አክለውም፣ መረጃዉ አለን ከሞሽ ኪሊማንጃሮ አካባቢ ለነበሩት 74 ልጆች እሥራቸዉን ጨርሰዉ ወደ ኬንያ ድንበር ነዉ ዲፖርት ያደረጓቸዉ ብለዋል።
የታንዛኒያ መንግስት አሁን ምንድነዉ ግን እዝያ ችግር የነበረዉ፣ ሰዎቹ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ የላቸዉም፣ ሰነድ ስለሌላቸዉ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ አይደሉም የሚል ነገርም ስለ ነበረዉ፣ ሊሰፓሲ መያዝ አለበት አንድ ሰዉ ኢምባሲዉ መነገር አለበት፣ ስለዚህ ጉዳዩን እየተከታተልነዉ ነዉ አሁን ሞሽ ነዉ የሚገኙት ልጆቹ እኛጋ ፕሮሰስ ለማድረግ ደብዳቤ እንጽፋለን ሊስታቸዉን እንልካለን ብለዉ ነበረ፣ እሱን በመጠባበቅ ላይ ነዉ ያለነዉ ይላሉ አቶ አንዳርጉ በርሄ።
እንዴት ነዉ የምትለይዋቸዉ? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄም፣
“ኢትዮጵያዊ ነህ አይደለህም እንደ መንግስት የምናደርገዉ የራሳችን አሰራር አለን። ይሄ የኤምባሲዉና የመንግስት ሥራ ነዉ። ወደዝያ ሄደን ነዉ የሚናጣራዉ፣ አሁን ከእነሱ ጋር ተነጋግረናል፣ በስልክም ተደዋዉለናል። ኦፊሴላዊ የሆነ ደብዳቤ እና ሊስታቸዉን ላኩልን ባስቸኳይ ብለናቸዋል፣ እነሱም እንልካለን ብለዋል። እንግዲህ ያዉ በእነሱ አንዳንድ ነገር እየጣሩ ይሆናል የሚልኩት ከዚያም በአስቸኳይ እኛ ለመንግስታችን እናሳዉቃለን መንግስት በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት ከዝያ ጉዳዩን እንፈጽማለን።” ብለዋል አቶ አንዳርጉ በርሄ።
የነገሩን ቅድመ ሁኔታ ምን ያክል ጊዜ ይፈጃል? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ እንግዲህ እኛ በመጣልን ሰዓት ነዉ እርምጃ የምንወስደው ብለዋል።
Voa
TPLF በአሜሪካ እሥር ቤት ላሉት ኢትዮጵያውያን ከ አሜሪካ ለማስባረር ዜግነት አይጣራም ቀጥታ የጉዞ ሰነድ ያዘጋጃል በሥቃይ ለሚገኙት ግን ዜግነት እያጣራን ነው
በኴንያ የህውሀት ጽ/ ቤት ሀላፊው አቶ በርሄ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: