የቀድሞ መንግስት ባለሥልጣናትን ያካተተ የመረዳጃ እድር አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

የደርግ አባላትና መስራች የነበሩትንና በኋላም የስርዓት ለውጥ ሲፈጠር በእስር ላይ ቆይተው በቅርቡ የተፈቱት የቀድሞ መንግስት አባላት ያቋቋሙት የመረዳጃ እድር አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ባሳለፍነው ሳምንት በአገር ፍቅር ቲአትር ቤት አከበረ።

በአሁኑ ወቅት ወደ 280 አባላትን የያዘው ሰው ለሰው የመረዳጃ እድር የተቋቋመው በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም መሆኑን የገለጹት የእድሩ ሊቀመንበር ኮሎኔል አሸብር አማረ የእድሩ ካፒታልም ከ200 ሺህ ብር በላይ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሎኔል አሸብር የእድሩን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ስለ አመሰራረቱ ሲገልጹ “አብዛኞቹ የእድሩ አባላት ችግርና መከራን ያለፉ ናቸው። በነበራቸው የመንግስት ኃላፊነት ምክንያት እስር ቤት ገብተው ከተፈቱ በኋላ የተቸገሩ የታመሙ እና ማረፊያ በማጣት የተጎዱ ነበሩ” ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አያይዘውም ሁለት የቀድሞ መንግስት አመራር አባላት ከእስር ከተፈቱ በኋላ መጠጊያ በማጣታቸው ጎዳና ላይ ወድቀው ሞተው ከተገኙ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እንደቀበራቸው ገልጸዋል። ለእድሩ መመስረትም ምክንያት የሆነው ያ ክስተት እንደሆነ የገለጹት ኮሎኔል አሸብር “ከዚህ በሀላ ለአራት እና አምስት ወራት እየተገናኘን ከተወያየን በኋላ ይህን እድር ለመመስረት ቻልን። ለእድሩ መመስረት ወንድማችን ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የተጫወቱት ሚናም ከፍተኛ ነው” ብለዋል።

በሁለት ዓመታት ውስጥ አራተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው ሰው ለሰው የመረዳጃ እድር ”በእድር” ስያሜ ከመጠራቱ በፊት “ማህበር” የሚል እንዲሆን ታስቦ ለአራዳ ክፍለ ከተማ ማህበራዊ ጽ/ቤት አቅርበው እንደነበረ የገለጹት ኮሎኔል አሸብር “ሆኖም ጽ/ቤቱ ማህበር ሳይሆን እድር መመስረት ትችላላችሁ ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገውን ፎርማሊቲ አሟልታችሁ ኑ ባለን መሰረት መተዳዳሪያ ደንብ፣ የአባላት ብዛት እና በአባላት የተመረጠ አመራር ይዘን ቀርበን ከሚያዝያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ህጋዊ እውቅና ተሰጠን” ብለዋል።

እድሩ ከምስረታው ጀምሮ አሁን እስካለበት ደረጃ እስኪደርስ ድረጅ በርካታ ውጣ ውረዶችን እንዳለፈ የገለጹት የእድሩ አመራሮች በተለይ የመሰብሰቢያ ቢሮ ችግር ከፍተኛውን ችግር እንደያዘ ገልጸዋል። ኮሎኔል አሸብር “ይህን ችግራችንን የተመለከቱት ወንድማችን አቶ ጸጋዬ ወልደገብርኤል (የዩኒቨርሳል ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባለቤት) በኮሌጃቸው እንድንሰባሰብና እንድንጠቀም ፈቀዱልን። አቶ ጸጋዬ ከዚህም በተረፈ ለ25 የእድሩ አባላት ልጆች ነጻ የትምህርት እድል ሰጥተውናል” ሲሉ ተናግረዋል። ከአቶ ጸጋዬ ወልደገብርኤል በተጨማሪ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለ16 የእድሩ አባላት ህክምና እንደሰጠች የገለጹት ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደግሞ 50 ሺህ ብር ድጋፍ እንዳደረገችላቸው ተናግረዋል። የእድሩ አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በተከበረበትበት ወቅት የደርጉ ምክትል ሊቀመንበር ሌፍቴናንት ኮሎኔል ፍሰሃ ደስታ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ተገኝተዋል።

የሰው ለሰው መረዳጃ እድር በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በቁጥር አ/ክ/ከ/ሰ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት 930/2006 ተመዝግቦ ህጋዊ እውቅና ያለው ሲሆን 279 ኣባላት አሉት። ወቅታዊ ካፒታሉም ከ200 ኚህ ብር በላይ ደርሷል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: