በወላይታ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ41 ሰዎች ህይወት ጠፋ

aseac

በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮሻ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት በትንሹ 41 ሰዎች ሞቱ።
በዞኑ በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች የጣለን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በደረሰው በዚሁ የመሬት መንሸራተት አደጋም ወላይታ ከተማን ከዳውሮ ዞን የሚያገናኝ መንገድ ከአገልግሎት ውጭ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
በደረሰው የመሬት መንሸራተት ቁጥራቸው ሊታወቅ ያልቻለ ሰዎች የተቀበሩ በመሆኑ የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና፣ በአደጋው መንገዶች ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው ምክንያት የነብስ አድን ስራው አስቸጋሪ እንዳደረገው የዞኑ ፖሊስ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጿል።
የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት መሆኑን ፖሊስ አክሎ አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ በባሌ ዞን የጣለን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የዞኑ ፖሊስ ማክሰኞ አስታውቋል።
በዞኑ ስር በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ ለሰዓታት የጣለው ይኸው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋም ከ1ሺ የሚበልጡ የቤት እንስሶች መሞታቸውም ተገልጿል።
በተመሳሳይ የጎርፍ አደጋም፣ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ጎርጎቱ ወረዳ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሁለት ታዳጊ ህጻናት ህይወት ማለፉን የዞኑ ሃላፊዎች ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
በዞኑ በደረሰ በዚሁ አደጋ ከ11ሺ የሚበልጡ ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ከሃገር ቤት ጉዳት እንደደረሰባቸውም ከሃገር ቤት ከተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

esat

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: