የሳምንቱን አበይት ዜናዎችና ሌሎች መጣጥፎች /Aseged Tamene/

የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ሀገራችንን አልወረረችም ሲሉ ማስተባበያ ሰጡ፡፡

በድሬዳዋ ሮብ ሌሊት በጣለው ከባድ ዝናብ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አራት የኦሮሞ ድርጅቶች ለመተባበር ተስማሙ

በጎነደር ቋራ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት የተደረገዉ አሰሳ አደጋ እንደገጠመዉ ተነገረ

በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት መክመሪ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር ስላልተቻል ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው  በመጠለያዎች መግባታቸው ተነገረ።

የ7 አመቷ ታዳጊ ግማሽ ሊትር አረቄ ጠጥታ ህይወቷ አለፈ!

aseac

የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ሀገራችንን አልወረረችም ሲሉ ማስተባበያ ሰጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ሀገራችንን አልወረረችም ሲሉ ማስተባበያ ሰጡ፡፡ በጋምቤላ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ በኋላ የኢትዮጵያ ጦር በሁለቱ ሀገሮች ድንበር አካባቢ መስፈሩን የተናገሩት፤ እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት የታገቱትን ህጻናት ለማስፈታት የጋራ ዘመቻ ለመክፈት ማቀዳቸውን የገለጹት የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ምንጮች ከዚህ ውጪ ግን የኢትዮጵያ ጦር ወደ ደቡብ ሱዳን ገብቷል የሚሉ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች መሆናቸውን አስተባብለዋል ይለናል ተከታዩ ዘገባ፡፡ ደቡብ ሱዳን በማንኛውም አይነት ሁኔታ በኢትዮጵያ ድንበሯና ሉአላዊነቷ እንዲጣስ እንደማትፈቅድ ባለስልጣናቱ መናገራቸውንም ዘገባው ጨምሮ ይገልጻል፡፡

በድሬዳዋ ሮብ ሌሊት በጣለው ከባድ ዝናብ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ባለፈው ሳምንት በደረሰው ጎርፍ ጉዳት ደርሶበት የነበረው  ድሬዳዋን ከመልካጀብዱ የሚያገናኘው ድልድይ በሮቡ ጎርፍ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ የሆነ ሲሆን፡፡

የ3 ሰዎች ሕይወት ሲአልፍ በ3 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን ተነግራል

12ዐ ሜትር ርዝመት ያለው የጎርፍ መከላከያ ግድብም ሲፈርስ የቤት እንስሳትና አንድ ተሽከርካሪም በጎርፉ መወስዱን 1 መስኪድ መፍረሱንም ተነግራል፡፡፡

ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የድሬዳዋ ዋና የገበያ አካባቢ የንግድ እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥም የተደረገ ሲሆን፡፡

ሕብረተሰቡ የውኃው መጠን ሲጨምር ለማስጠንቀቂያነት የሚለቀቀውን ሳይረንና የመሣሪያ ድምፅ ሲሰማ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መነገሩም ታውቃል፡፡

አራት የኦሮሞ ድርጅቶች ለመተባበር ተስማሙ
አራት ተቃዋሚ የኦሮሞ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰሞኑን ባወጡት የጋራ የፕሬስ መግለጫ አስታውቀዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፤ የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፤ የኦሮምያ ነፃ አውጭ ግንባር እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዓላማ አድርገው የተነሡት የኢሕአዴግን አስተዳደር መታገልና መጣል መሆኑን አራቱንም ድርጅቶች አስታውቀዋል

በጎነደር ቋራ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት የተደረገዉ አሰሳ አደጋ እንደገጠመዉ ተነገረ

የወያኔ ባለስልጣናቱ ሽፍታ ያሉት የጎንደር ጀግናና አርበኛ መሽጎበታል የተባለዉን ከቋራ ባሻገር የሚገኝ ስፍራ ለማሰስ ከሱዳንና ከኢትዮጵያ አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ አሳሽ ቡድን አርበኞች አሉበት የተባለዉ ስፍራ ሲደርሱ ምንም በማጣታቸዉ ፊት ተለፊት ተገናኝተዉ ተስፋቸዉ በተመናመነበት ወቅት ድንገተኛ የመትረየስ ጥቃት ከየአቅጣጫዉ በመሰንዘሩ እርስ በእርስ እስከ መሞሻለቅ እንደደረሱ ምንጮች ከመካላከያ አሳዉቀዋል።
ከ15 ቀናት በፊት ይህን ሁኔታ ለመበቀል በንፋስ ገበያ በኩል የገቡ የሰሜን ሱዳን ወታደሮች አራት ገበሬዎችን ጠልፈዉ የወሰዱ ቢሆንም ገበሬዉ ከየአቅጣጫዉ በመነጋገር በመተናነቁ ተመልሰዉ ወደ መጡበት ፈርጥጠዋል።
የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን የጎንደርን ገበሬ ለማሸማቀቅ እና ለማስፈራራት ከባድ መሳሪያ የጫኑ ካሚዮኖች በየመንደሩ በማንቀሳቀስ ላይ ሲገኝ አፈናዉና ድንገተኛ የቤት ለቤት አሰሳዉ ቀጥሏል።

በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት መክመሪ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር ስላልተቻል ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው  በመጠለያዎች መግባታቸው ተነገረ።

በካናዳ በነዳጅ ሃብቷ በምትታወቀው አልበርታ ፎርት መክመሪ በተባለ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት የሸሹ 100 ሺህ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው።

በሰደድ እሳቱ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ እየወደመች መሆኑ እየተነገረ ነው።

100 ሺህ የሚሆኑት የፎርት ማክመሪ ነዋሪዎች እንዲወጡ የታዘዙት አካባቢውን እያጋየ ያለውን ሰደድ እሳት ማቆም ወይም መቆጣጠር ባለመቻሉ እንደሆነ ተገልጿል።

በእሳቱ ምክንያት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እስካሁን እንደሌለ ታውቋል። በዚህ አካባቢ አስራ አምስት ሺሕ የሚደርስ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በዚህ አካባቢ የሚኖረውና በኢትዮጵያ ጋዜጠኛ የነበረው ሰይፈ መኮንን እሳቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ይላል።

ሰደዱን ለማስቆም እየተረባረቡ ካሉት ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት ቻድ ሞሪሰን የእሳቱ መንስኤ መብረቅ ይሁን ወይም ሰው የጫረው ገና እንደማያውቁና እያጣሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የ7 አመቷ ታዳጊ ግማሽ ሊትር አረቄ ጠጥታ ህይወቷ አለፈ!
——-
ከመዲናችን አዲስአበባ በ130 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረብርሃን ከተማ ጎሽኬ ቀበሌ አንዲት የ7 አመት ታደጊ ከትላንት በስቲያ ከቀኑ 10 ገዳማ ወላጆቾ ለእረኝነት በተሰማሩበት ወቅት እቤትውሥጥ በጠርሙስ ተቀምጦ የነበረ ግማሽ ሊትር አረቄ ጠጥታ መሞቷን የጎሽኪቀበሌ ፓሊስ ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀ::

በእለቱ ታዳጊዋ ወደ ደብረብርሃን ሆስፒታል ለህክምና አምርታ የነበረ ቢሆንም የጠጣችው አረቄ ከመጠን በላይ በመሆኑ ህይወቷ ሊያልፍ እንደቻለ የደብረብርሃን ሆስፒታል ገልፆል!
የታዳጊዋ የቀብር ስነስርዓት በትላንትናው ዕለት ተፈፅሟል::

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: