የደሴ ነጋዴዎች የሁለት ቀናት የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ኢሳት ዜና :- የከተማው ወኪላችን እንደገለጸው፣ ሚያዚያ 24 እና 25 ሙሉ በሙሉ፣ ዛሬ ደግሞ በከፊል የገበያ አዳራሾች ተዘግተዋል። በሰላም የገባ የአዳራሽ 624፣ በእድገት የገበያ አዳራሽ 638 ፣ በላኮመዛ የገባያ አዳራሽ 632 እንዲሁም በሚሊኒየም የገበያ አዳራሽ 562 ሱቆች የተዘጉ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ከፊሎቹ ዛሬ ስራ ጀምረዋል። የአድማው ምክንያት ከአቅም በላይ የተጣለባቸው ግብርና ካሽ ሬጅስትራር ማሽን እንዲገዙ መገደዳቸው ነው። ነጋዴዎቹ እንደሚሉት በቂ ስራ በሌለበት ሁኔታ፣ ከአቅማቸው ጋር የማይጣጣም ግብር እንዲከፍሉ መገደዳቸው ሳያንስ፣ ትናንሽ የንግድ ድርጅቶች ሳይቀሩ ካሽ ሬጂስትራር ማሽን እንዲገዙ መገደዳቸው አግባብ አይደለም።
ነጋዴዎቹ አድማውን ያደረጉት፣ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ፈቃድ ጠይቀው ከተከለከሉ በሁዋላ ነው። ከአድማው በሁዋላ የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ የሄዱ ነጋዴዎች “ የንግድ ፈቃዳችሁን መመለስ ከፈለጋችሁ 20 ሺ ብር ክፈሉ “ መባላቸውን ገልጸዋል። በድርጊቱ የተበሳጩት አንድ ነጋዴ “ከዚህ መንግስት ጋር መነጋገር ለሞተ ሰው መድሃኒት እንደማዘዝ ይቆጠራል” በማለት ብሶታቸውን ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የደሴ ከተማ ከንቲባን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በሌላ በኩል ከከተማዋ የተውጣጡ በርካታ የኢህአዴግ አባላት ና የመስተዳድሩ ሰራተኞች፣ የመግቢያ ፈተና ውጤት ሳይዙ በደቡብ ወሎ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ተደርጓል። የድርጅት አባሎቹ በትእዛዝ ገብተው እንዲማሩ ከተደረገ በሁዋላ፣ በተማሪዎቹ ላይ የስለላ ስራ እንደሚሰሩም ታውቋል። አባሎቹ በየቀኑ የተማሪዎችን ውሎ ለእለታዊ የመረጃ ልውውጥ አስተባባሪ ሪፖርት እንደሚያደርጉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: