የወያኔ መንግስት አቶ ኦኬሎ አኳይ፣ ለማሳፈን ለደቡብ ሱዳን መንግስት 39.5 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉ ተነገረ

የቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የጋምቤላ ጭፍጨፋን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ ሰጡ። የጭፍጨፋውን ሂደት በማዛባት፣ የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ እንዲያቀርቡ በመገደዳቸውና ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ሰለነሳቸው ፕሬዚደንትነታቸውን ጥለው ድንበር አቋርጠው መሸሻቸውን በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።
ከሰኔ ወር 1978 ጀምሮ በነርስነት የመንግስት ስራ መጀመራቸው፣ በኋላም እስከ ክልል ፕሬዚደንትነት በዘለቀው አገልግሎት 18 ዓመታት መቆየታቸውን ያስረዱትና የ8 ልጆች አባት መሆናቸውን የገለጹት አቶ ኦኬሎ አኳይ የዛሬ 15 ዓመት በጋምቤላ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የተፈጸሙ ድርጊቶችን ለችሎቱ ዘርዝረዋል።
ታህሳት 5 ቀን 1996 ዓም በጋምቤላ የህወሃት ታጋይ በነበሩት ሻለቃ ጸጋዬ መሪነት የተንቀሳቀሰው የሃገር መከላከያ ሰራዊት 424 የአኝዋክ ወንዶችን ለይቶ መግደሉ በስም በዕድሜ በዖታና በአድራሻ ተለይቶ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ከመሰራጨቱ በፊት የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ዶ/ር ገብረዓብ ባርናባስ ዕለቱን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ግጭቱ የአኝዋክና ኑዌር ነው ማለታቸውን አቶ ኦኬሎ በጽሁፋቸው አስታውሰዋል።
በርሳቸው በኩል በማግስቱ ታህሳስ 6 ለጀርመን ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት ግጭቱ የአኝዋክና ኑዌር አይደለም በማለት ማስተባበላቸውን ገልጸዋል።
ሆኖም የወቅቱ ጠ/ሚኒስትር የነበሩት በአቶ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በጋምቤላ ም/ቤት ውስጥ በተደረገ ግምገማ ጭፍጨፋው የአኝዋክና የኑዌር ግጭት ተብሎ እንዲገለፅ ግፊት ሲደረግ አሻፈረኝ በማለታቸው፣ ስብሰባው እርሳቸው በሌሉበት በኢትዮጵያ ሆቴል መካሄዱን በጽሁፋቸው አስታውሰዋል።
በኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው ስብሰባ የሟቾቹ ቁጥር 60 ተብሎ እንዲጠቀስ ከጾታም አንጻር 59 ወንድና አንዲት ሴት መሆናቸውን እንዲገለጽ ስምምነት መደረሱን ዘርዝረዋል።
የወቅቱ የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር እና የህወሃት መስራች በነበሩት አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘጋጀውን ይህንን የውሳኔ ሃሳብ እንዲፈርሙ፣ ካልፈረሙ ከፕሬዚደንትንነት ወርደው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው በስብሰባው ላይ ከነበር የኑዌር ተወላጅ መረጃ ሲደርሳቸው፣ ሃገር ጥለው መጥፋታቸውን ዘርዝረዋል።
ግድያው በተፈጸመ በ24ኛው ቀን ታህሳስ 29 ይህ ውሳኔ ሲተላለፍባቸው፣ በማግስቱ ጠዋት ታህሳስ 30/1996 በድንበር አቋርጠው መውጣታቸውን ከጽሁፋቸው መረዳት ተችሏል።
ወደስደት ካመሩ በኋላ ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ስለነሳቸው በጋምቤላ ለሚፈጸመው በደል ስለተሰማቸው የመብት ትግል ለማድረግ መነሳታቸውን፣ ሆኖም የመገንጠል አላማ አለማራመዳቸውን ጠቅሰዋል። የደቡብ ሱዳን መንግስት በ23 ሚሊዮን ዶላር ጁባ ላይ ለኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይል እንደሸጣቸውም በጽሁፋቸው ዘርዝረዋል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት ዕርሳቸውን ለማሰርና ለመወንጀል 39.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን አብራርተዋል።
“የኢህአዴግ አባል እንዲሁም የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች አባል ሆኜ አላውቅም፣ እንደ አቶ መለስ ዜናዊም የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ አይደለሁም፣ የእነሱ ፕሬዚደንትነትም ሆነ ሚኒስትርነት አያጓጓኝም” ያሉት አቶ ኦኬሎ አኳይ፣ ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ይልቅ አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍ/ቤት እንደሚፈለጉ አብራርተዋል። ወንጀለኞቹ ያሉዋቸውም በስም ዘርዝረው አብረዋቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። “መለስ ዜናዊና ግብረ-አበሮቻቸው ኡምድ ኦባንግ፣ ጸጋዬ በየነ፣ ገብረዓብ ባርናባስ፣ አባይ ጸሃየ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ዮሃንስ ገ/መስቀል፣ አባዱላ ገመዳ፣ አልማው አላምረው እና ታደሰ ሃይለስላሴ” አለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍ/ቤት ሊቀርቡ እንደሚገባ ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓም ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
ከ10 ዓመታት በላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ማምራታቸውን ተከትሎ ከሁለት አመት በፊት በደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት አቶ ኦኬሎ አኳይ፣ የተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ውድቅ ቢሆንም፣ ጋምቤላን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ተንቀሳቅሰዋል በሚል በዚህ ሳምንት የ9 አመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ርሳቸው ለፍርድ ቤት በቀረቡት ጽሁፍ ኣንዲሁም፣ በማስረጃነት ባያያዙት ሰነድ በኢትዮጵያ አንድነት ከምያምኑ ድርጅቱ ጋር ትብብር ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከድርጅት አባልነት መባረራቸውን በመግለጽ፣ የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል።
ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ለቀረበላቸው ክስ ድርጊቱን አምነው ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ማድረግ ወንጀል

Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: