በመተማ እና አካባቢዋ ባለፈው ሁለት ቀን በተካሄደው ከባድ ውጌያ ከተማረኩት የህወሃት ወታደሮች መካከል አንዱ የጦር መኮነን የሰጠው ቃል

ይህ የጦር መኮነን ይህን ያለብት ትልቅ ጉዳይ አለ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የአንድ ብሄርን ብቻ ጥቅም በማሰጠበቁ ብሎም፡የኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ህልውና አደጋ ላይ በመጣሉ ወታደር ሃይሉ አሁን ይህ ነው የማይባል ሃገራዊ ጥያቄወችን ቢያነሳም ጥያቄውን በተገቢ መልኩ ከመመለሰ ይልቅ ጥያቄያችንን ወደ ጎን በመተው የነበሩትን ነባር መኮነኖች የጦር አዛዦች በተለይም በሁለት ብሄር ተወላጆች ላይ ከቦታቸው በማንሳት በሰብሰባ ስም ያደረሰበት ቦታ ሳይታወቅ በነሱ ቦታ ታማኝ ያላቸውን የጦር ልምድ የሌላቸውን የራሱን ሰወች ብቻ እየሾመ ጦሩን ትልቅ አደጋ ውሰጥ ጥሎታል፡፡ ከወታደሩ የሚነሱ አበይት ጥያቄወች
1- ከባለፉት 6 ወራት ጀምሮ በሃገራችን ልዩልዩ ቦታወች የተነሳው ህዝባዊ አመች በሰላም ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ለምን ወታደራዊ እርምጃ ትወሰዳላቹህ ለምንሰ ንጹሃንን ዜጋ ትገድላላቹህ ወታድሩ ብዙ መረጃወች እየደረሱት ነው እኛ ለሃገራችን ብለን ቤት ንብረት ሳንል ሁሉን ጥለን ወተን እናንተ ግን ሰልጣናቹሁን ለማርዘም ሰትሉ የእኛን እናት አባት እህት ወንድም ባደባባይ በጥይት ትጨፈጭፋላቹህ ለምን የህዝብን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ አትፈቱም?
2- ወልቃይት ላይ ያለው ጉዳይ ለምን ለህዝቦች አትተውትም ህዝቦች ህገመንግሰቱ በሚፈቅደው መንገድ የጠየቁትን መልሰ እናንተ ለምን ባሃይል ለመመለሰ ትሞክራላቹህ ለምን ለህገመንግሰቱ ቦታውን ዳኝነቱን አትለቁም?
2- ኦሮሚያ ላይ ያን ሁሉ የጨፈጨፉት ለህግ መቅረብ ሲገባቸው እናንተ ግን ሰላማዊ ሰወችን በግፍ አሰራቹህ፡ በእናንተ ጦር የሞቱትን ሰወች አሰከሪን ኣንኳን እንዳይቀብሩ ገንዘብ ጠየቃቹህ ይህ ምን ማለት ነው ለእናንተ?
3፥ በተለይም እኛ ደንበር ላይ የተቀመጥነው ቁጭ ብለን ልንበላ ልንጠጣ አልያም የእኛን ሰወች ለመጨፍጨፍ ሳይሆን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማሰከበር ነበር ነገር ግን በሚሰጥር እና በድብቅ የተደረገው ለሱዳን በሸህ ኪሎሜትር የሚቆጠር መሪታችን እንደቀላል ነገር ተቆርሶ ሊሰጥ መሆኑንም ሁላችንም አውቀናል ይህ ድጋሜ የማይሆን ትልቅ ሰህተት እና ድፍረትም ጭምር ነው በኤርትራ በተደረገው እልህ አሰጨራሽ ውጊያ ላይ ብዙ ጓዶቻችን ካጣን በኋላ ወደ ኋላ ተመለሱ ተብለን እንደቀላል ነገር በማግስቱም የጓዶቻችን እንባ ሳይደርቅ ባድመን በአንድ ሰው ፊርማ ብቻ አሳልፈው መሰጠታቸውን ሰማን ይህ እልህ በውሰጣችን ቁጭ ብሎ ቁጭታችን ሳያልቅ ዛሪ ደግሞ ጭራሸ ለባእዳን ሃገር ለም መሪታችን መሰጠት ምን ማለት ነው ይህ ለእናንተ? በእርግጥ የኢትዮጵያ መሪ ናቹህን?
ይህን እና መሰል ጥያቄወችን ከመላው አብዛኛው መከላከያ አባላት ተውጣጥተን ጥያቄን በተደጋጋሚ አቅርበን ነበር ቢሆንም ምንም፡መልሰ ሳይሰጠን ብዙ ጓዶቻችን አሰበላን የት እንደገቡ እንኳን አይታወቅም ሰንጠይቅም የሚሰጡን መልሰ ተቀይረዋል እድገት አግተዋል፡መሰል የህጻን ጫወታ ይጫወቱብናል ይህ በእንዲህ እንድለ ባለፈው በደቡብ ሱዳን እና ሰሜን ሱዳን አዋሳኝ ያለን መከላከያወች በአንድ ቀን ውሰጥ በሰአታ ልዩነት በመጣልን ሪድዮ መልእክት ሁላችንም ቦታውን ለቀን ወደ መሃል ሀገር ወደ ጎንደር እንድንዘምት ተደረገ ልብ አድርጉ ይህ የሆነበት ምክንያት የደቡብ ሱዳን አማጺን መሪ ኢትዪጵያ የገንዘብም የመሳሪያም ድጋፍ ታደርጋለች ይህንም የሚያደርጉበት ሚሰጥር አማጺ ቡድኑ ካሸነፈ ለሰሜን ሱዳን ወዳጅነት የበለጠ ይጠነክራል ሰሜን ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በአብዩ በተባለ አካባቢ ታላቅ ፍጥጫ ውሰጥ በመግባታቸው ዝግ ነው አሁን ይህ ብድን ካሸነፈ ሰሜን ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በጋራ ይሰራሉ ይጠቀማሉ ይህ እኛን አልከፋንም እኛን ያበሳጨን ወያኔ ይህን አካባቢ የግሉ ለማድረግ ይዞ ታላቋብ ትገራይ ለመመሰረት ባወጣው ካርታ መሰረት ጋንቤላን ያካትታል ይህም፡ማለት ሱዳን እሰከ ደቡብ ሱዳን ከትግራይ ጋር ትዋሰናለች አባይም፡የኢትዮጵያውያን መሆኑ ቀርቶ የሱዳናውያን እና ትግራውያን ይሆናል፡፡ ይህን ለማሰፈጸም እዝህ አካባቢ ያሉትን ህዝቦች ማስለቀቅ አልያም መጨፍጨፍ አልያም የትግራይን፡ማንነት መቀበል የትግራይን ማንነት መቀበል ደግሞ፡ለጋንቤላ ህዝቦች ሞት ነው ጋንቤላ በኢትዮጵያውያንነት የሚያምኑ ታላቅ ህዝቦች ናቸው ይህን ባደረጉ፡ማግሰት እኛ በወጣን ባንደኛው ቀን የደቡብ ሱዳን አማጽያን ገብተው ህዝባችን ጨፈጨፉ፡ በግፍ ተገድርሉ ይህን ትእዛዝ ደግሞ ከወያኔ እንደወረደ የተላለፈ ትእዛዝ ነበር። ይህ በእርግጥ ለኢትዮጵያውያን ያማል እጅጉን ያማል። እዚህ ላይ ይህን ሲለኝ መኮነኑ በእምባ ታጠበ አንድ እውነት ልንገትህ ባድመ ላይ ባለቁት ጓዶቼ እንኳን እንዳሁኑ አይነት የሃዘን ስሜት አልተሰማኝም፡ለምን?
አንድን ሃገር ለማፈራረሰ ህዝቦችን በነጭ ወረቅት ፈርሞ መጨረሰ ለምን አሰፈለገ? በእርጥ ወያኔ እና አመራሮቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው? ትግራይሰ ቢሆኑ፡ለኢትዮጵያ አልተጋደሉም ታዳ ዛሪ ትልቅ ክህደት ለምን አሰፈለገ?
አሁን ሁሉም ወታደር መሳሪያውም ለወያኔ ያዞራል አትጠራጠር አሁንም እንባ የእልህ እንባ ያለቅሳል።
ለምን ድጋሜ ሰሜን ዘመታቹህ?
ወያኔሰ፡ለምን አሁን ወደ ጋንቤላ ጦር ያዘምታል?
የሚለውን በቀጣይ ክፍል ይዘን እንቀርባለን፡

የእናንተው ገብርየ ከሰሜን አርበኞች ግንቦት ሰባት

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: