የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በጋቤላ የደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ምንም አዲስ ነገር አይደም አለ::

የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በጋምቤላ የደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ አዲስ ነገር አይደለም ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት በዘገባው አስፍሯል። አርቡ እለት የደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባዎች በአብዛኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የኑዌር ጎሳ አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ በዘገባው የጠቀሰው ዋሽንግተን ፖስት፣ በዚህ አመት በኑዌርና በአኝዋክ ጎሳዎች መካከል ደም ያፋሰሰ ግጭት ተከስቶ እንደነበር ዘግቧል። “የምናውቀው ድርጊቱን የፈጸሙት እስከ ፍንጫቸው የታጠቁ፣ የተደራጁና የሚሰሩትን የሚያውቁ ናቸው። የመንግስት ቃል አቀባይ በምስራቅ አፍሪካ ጥቃቱ ያን ያክል የሚያስገርም ነገር አይደለም” ማለቱን ዋሽንግተን ፖስት በዘግባው አስነብቧል። የኢትዮጵያ መንግስትም በቅርቡ ጊዜ የክልሉን ፖሊስ ትጥቅ ማስፈታቱ አሁን ለተፈጸመው የጅምላ ዕልቂት የራሱን አስተዋጽዖ አበርክቶ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን በዘገባው አመልክቷል።
አቶ ጌታቸው ረዳ መንግስታቸው ከኢትዮ- ደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በጥቃት አድራሾቹ ላይ የጋራ ጥቃት ለመክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ጋዜጣው ኢትዮጵያውያን ሃዘናቸውን ለመግለፅና ለተጨፈጨፉት ወገኖች መንግስት መግለጫ ለቀናት ባለማውጣቱ የተሰማቸውን ንዴት በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሲገልጹ መዋላቸውን አስነብቧል።
የጋምቤላ ዕልቂት የተከሰተው በወሳኝ ሰዓት መሆኑን የዘገበው ዋሽንተን ፖስት፣ ጭፍጨፋው የተከሰተው በሀገሪቱ በተከሰተው ከ10.2 ሚሊዮን ህዝብ ለርሀብ በተጋለጠበት ፣ በኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ በነበረው ህዝባዊ እምቢተኝነት ከ200 ሰዎች በላይ በተገደሉበት እና ከ5ሺህ በላይ ለእስር በተዳረጉበት ወቅት መሆኑ የጅምላ ጭፍጨፋው ጥያቄዎችን የሚያጭር ነው በማለት በዘገባው አመልክቷል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: