የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት በጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱት ህጻናት ጉዳይ አሳስቦኛል አለ

ከአምስት ቀን በፊት ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱት ወደ 100 አካባቢ የሚጠጉት ህጻናት ደህንነት አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።
በክልሉ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዘው የህጻናት መርጃ ድርጅቱ ከቀያቸው ታፍነው የተወሰዱ ህጻናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጥሪውን አቅርቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለመታደግ ዘመቻ መክፈቱን ቢገልጽም ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ታጣቂዎች የሚገኙበትን ስፍራ እንኳን ማወቅ እንዳልተቻለ የጋምቤላ ክልል ባለስልጣናት ማክሰኞ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ታጣቂዎቹ ያሉበት ስፍራ ከታወቀ በኋላ የኢትዮጵያ ወታደሮች የአጸፋ እርምጃን ለመወሰድ እንደሚጀምሩም የክልሉ ሃላፊዎች ገልጸዋል።
መንግስት ጥቃቱን ፈጽመዋል ባላቸው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ወታደራዊ እርምጃን ለመውሰድ ከደቡብ ሱዳን መንግስት ፈቃድን እየጠበቀች እንደሆነም ታውቋል።
የሙርሌ ጎሳ አባላት በደቡብ ሱዳን በወታደራዊ በትጥቅ ከተደራጁ ቡድኖች መካከል ዋነኛውና ጠንካራው መሆኑንም የደቡብ ሱዳን የፖለቲከ ተንታኞች በመግለጽ ላይ ናቸው።
ከአምስት ቀን በፊት በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ከ200 በላይ ሰዎች በተጨማሪ ከ100 የሚበጡ ህጻናት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን፣ ከ20ሺ በላይ ሰዎችም ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።
የተለያዩ ሃገራትን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውንና ድርጅቶች ይህንኑ ጥቃት በማውገዝ ግድያውን የፈጸሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪን እያቀረቡ ይገኛል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: