ሰበር መረጃ . . የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ወታደራዊ መኮንን ኮበለሉ.

በምእራብና በምስራቁ እዝ ዉስጥ ከ1991 አመተ ምህረት አንስቶ ሲያገለግሉ የነበሩ የወያኔ ወታደራዊ አመራር ሻምበል መላኩ የትግራይ ነጻ አዉጪዉን ቡድን የመከላከያ ሰራዊት ከድተዉና ዉድ ሐገራችዉን ጥለዉ ከወጡ ሰንበትበት ብለዋል አዎ በአንድ ዘር የበላይነት ላይ የተመሰረተዉን ሰራዊት ከማገልገል መነጠል ይሻለናል ብለዋል ወጣቱ መኮንን ።
ሻምበል መላኩ በሶማሌያና በጎንደር እንዲሁም በምስራቁ እዝ ላይ ያገለገሉ የነበረ ሲሆን በተለይም ከሶማሌያ የተመለሰዉንና አዘዞ ላይ የፈረሰዉን የ 43ተኛ ክ/ጦር ሰራዊት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት
” እጅግ አሳዛኝ ሲሉ ይገልጹታል ” አዎ እጅግ በጣም ዘግናኝና አሰቃቂ በደል ተፈጽሞብናል! እንደ ከንቱ ሸቀጥ ነበር ሙት ወታደሮች በከባድ መኪና ሸራ ለብሰዉ ተጭነዉ የሚወሰዱት! ወታደሮቻችን ሲሞቱ ለቤተሰቦቻቸዉ እንክዋን በቅጡ መሰዋታቸዉ አይነገራቸዉም! ካሳም ሆነ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘውት የዘር ሀረግ ይመዘዝ ነበር! በሶማሌያ ላይ የተደረገዉ ወንጀል ህዝብ ቅነሳ ካልሆነ በስተቀር አንድ እራሱን እንደ መንግስት የሚመለከት አካል ሊሸከመዉ የማይችል ጉዳይ ነዉ “።
” በተለይም ከአዘዞ ወደ ቀብሪ ደሐር ተላልፈን ሁለተኛ ሜካናይዝን ካቋቋምን ወዲህ የብረት ለበሱ የመከላከያ መሳሪያዎች ወደ ሶማሌያ ተወስደዋል።
ባጠቃልይ ከወያኔ ጋር የሚደረግ አብሮነት እጅግ አደገኛ ነዉ! ህዝብንና ሐገርን ከመጉዳቱም በላይ ለተጠያቂነት ይዳርጋል ነገ የወያኔ መንግስት መዉደቁ አይቀርም እዉነት ግን እዉነት ነች ሁሉም በሰራዉ ወንጀል ይጠየቃል በመሆኑም ለመላዉ የመከላከያ ሰራዊት የማስተላልፈዉ መልእክት ቢኖር ከወያኔ ጋር ያለዉን ማለትም የተሳሰረበትን ገመድ በመበጠስ ለህዝብ ከቆሙና ከሚታገሉ ጋር አብሮ እንዲቅም ነዉ ” ።
ፎቶ የሙሉ መቶ አለቃ በነበሩበት ወቅት የተነሳ ሲሆን ሻምበል መላኩ የህዝብ ልጅነታቸዉን በማስመስከር ኢትዮጵያዊነታቸዉን አንጸባርቀዋል!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: