በኦሮሚያ እና አማራ ክልል በነበረው ረብሻና ሁከት ምክንያት ዘንድሮ ብሄራዊ ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች እንዳሉ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ…

በኦሮሚያ እና አማራ ክልል በነበረው ረብሻና ሁከት ምክንያት ዘንድሮ ብሄራዊ ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች እንዳሉ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ…
ችግሩ በርትቶ ትምህርት እስከ መዝጋት የደረሱ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ቀደም ሲል በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣው የፈተና ሰሌዳ መሰረት አያስፈትኑም ተብሏል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የህዝብ ተወካዮች ዛሬ ላነሱላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡
ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት እና ረብሻ ተማሪዎች ተሳታፊ ነበሩ፣ የስነ ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ለመሆኑ ምን ፈይደዋል ሲሉ ሚንስትሩን ጠይቀዋል፡፡
አንድ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ትምህርቱ መወቀስ የለበትም የሚል ምላሽ የሰጡት አቶ ሽፈራው ተማሪዎቻችን ጥያቄ ማንሳታቸው እና መሞገታቸው ስህተት የለበትም ብለዋል፡፡
በመላው ሀገሪቱ 40 ሺ ትምህርት ቤቶች አሉን የሚሉት አቶ ሽፈራው ሁከትና አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረው በኦሮሚያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ብቻ ነበር ብለዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ 13 ትምሀርት ቤቶች ትምህርት ለማቋረጥ ተገድደዋል ብለዋል፡፡
ተማሪዎቻችን መስታወት እንኳን አለሰበሩም፣ ድንጋይም አልወረወሩም፣ ጥያቄያቸውን በተገቢው መንገድ ነው ያቀረቡት ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ትምህርታቸውን ተረጋግተው ላልተማሩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የብሄራዊ ፈተና መውሰጃ ጊዜው ይራዘማል ተብሏል፡፡
ከክልሎቹ ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: