የሳምንቱ አበይት ዜናዎችንና ሌሎች ዳሰሳዎችን ከDceson ራዲዮ ይከታተሉ

 aseac

የአውሮፓ ህብረት እየጨመረ ከመጣው የስደተኞች ቁጥር አንጻር የስደተኞችን ፖሊሲ ለመቀየር ተስማሙ

የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕ/ት አቶ ኦኬሎ አኳይ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ

ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጠው

የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ የአቶ አንዳጋቸውን ፅጌ ጉዳይ መመርመር እንደሚጀምር አስታወቀ

 

የአውሮፓ ህብረት እየጨመረ ከመጣው የስደተኞች ቁጥር አንጻር የስደተኞችን ፖሊሲ ለመቀየር ተስማሙ

ህብረቱ አዲስ የሚቀይረው ህግ ከተለያዩ ሃገራት ወደ አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን አንድ ስደተኛ መጀመሪያ እግሩ ባረፈበት ሃገር ጥገኝነት የመጠየቅ መብት እንዳለው፥ አሁን ያለው የህብረቱ የስደተኞች ፖሊሲ ይደነግጋል። ይህ የደብሊኑ ስምምነት ግን እየጨመረ ከመጣው የስደተኞች ቁጥር አንጻር ማሻሻያ ያስፈልገዋል ተብሏል።

በዚህም ከ19 90ዎቹ ጀምሮ ስራ ላይ ያለውን ፖሊሲ መቀየርና ማሻሻል መፍትሄ መሆኑን ነው የህብረቱ መግለጫ የሚያሳየው።

የአሁኑን ደንብ ትንሽ ማሻሻል እና በብዛት ስደተኛ የሚቀበሉ ሃገራትን መደገፍና ማገዝ አንዱ አማራጭ ይሆናልም የተባለ ሲሆን አልያም ከፖሊሲ ማሻሻያ ጋር ስደተኞችን ለሃገራት እኩል ማከፋፈልም ህብረቱ ሊከተለው የሚችለው አማራጭ ነው እየተባለ ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የህብረቱ አባል ሃገራት የትኛውም አይነት አማራጭ እንደማይዋጥላቸው ገልጸዋል ምክንያቱም በቀደመው ደንብ መሰረት ስደተኞች ጥገኝነት የሚጠይቁት እግራቸው መጀመሪያ በረገጠበት ሃገር እንጅ ድንበር ተሻግረው ያረፉበት ሃገር አይደለምና።

በደብሊኑ ደንብ መሰረትም ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን ከሃገራቸው የማስወጣት እና ያለማስጠለል መብት አላቸው ።

የጥገኝነት ጥያቄው መጀመሪያ እግራቸው የረገጠበትን እንጅ የገቡበትን ሃገር አይመለከትምና ይህን ደግሞ ብሪታንያን ጨምሮ በርካታ ሃገሮች ይፈልጉታል።

እናም የትኛውም አይነት አማራጭ ቢቀርብ የቆየውን ህግ ብቻ መተግበር ምርጫቸው እንደሆነ ነው ሃገራቱ የገለጹት። በሳምንቱ መጀመሪያ ከመካከለኛው ምስራቅ ቱርክን ተጠቅመው ግሪክ የደረሱ ስደተኞችን ወደ ቱርክ የመመለሱ ስራ መጀመሩ ይታወሳል። 202 ስደተኞችም ከግሪኳ የሌዝቦስ ደሴት ቱርክ ዲኪሊ ደርሰዋል።

በርካታ የአውሮፓ ሃገራትም የስደተኞችን ፍልሰት ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ። ድንበራቸውን ከመዝጋት ጀምሮ የተጠናከረ ጥበቃ ማድረግና ለመግባት የሚሞክሩትን ባሉበት ማቆየት የሚጠቀሱ እርምጃዎች ናቸው።

የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕ/ት አቶ ኦኬሎ አኳይ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ

ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የኖርዌይ ዜግነት እንዳላቸው የሚነገረው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል::
በአኙዋክና ኑዌር ጎሳዎች መካከል ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ከሀገር የተሰደዱት አቶ ኦኬሎ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት የተቀናበረውና በግድያውም የተሳተፉት የመንግስት ወታደሮች እንደነበሩ ለተለያዩ የዜና አውታሮች መግለፃቸው ይታወሳል።
ከአቶ ኦኬሎ ጋር በአባሪነት የተከሰሱ ሌሎች 5 ግለሰቦችም ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን  ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ከ20 ቀናት በኋላ ቀጥሯቸዋል ተብሏል::
አቶ ኦኬሎ የጋቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ከ 400 በላይ ሰዎች በመንግስት ወታደሮች በግፍ ተገለው 60 ሰዎች ብቻ ናቸው እንድል ታዝዤ ፍቃደኛ ሳልሆን ቀርቻለው ማለታቸውን; ከ 10 አመት በፊት የተፍፀመውን ግድያ ዋነኛ ተዋናዮች አቶ መለስ ዜናዊ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ በረከት ስምዖን እንደሆኑና በዛን ግዜ የፌደራል ፖሊስ ጉዳዮች ሚንስትር ዴኤታ የነበሩት ዶክተር ገብረአብ ባላባራስ ወንጀሉን በቀዳሚነት አስፍፃሚ እንደነበሩ በፍርድ ቤት የክስ ክርክር ወቅት መናገራቸውን  አይዘነጋም:

ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጠው

የወያኔ መሪዎች የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንዲያስችላቸው በውጭ ሀገራት የማግባቢያ ሥራ  (የሎቢ ሥራ) ለሚሰሩላቸው ኩባንያዎች የአገሪቱን  ሀብት ማዕድኗን እንዲበዘብዙ  መንገዶችን ሲያመቻቹ መቆየታቸው ይታወቃል። ከአፋር ግዛት ከሰመራ የሚመጡ መረጃዎች  እንደሚያመለክቱት ከአስር ዓመት በፊት ለቀድሞ የወያኔ መሪና ጠቅላይ ሚኒስትር  ለመለሰ ዜናዊ ሽልማት የሰጠው ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ከኖርዌይ ያራ በተጨማሪ አንድ የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያም ይህንኑ የአፋር  ማዕድን እንያወጣ ተፈቅዶለታል። ኢትዮጵያ በከርሰ ምድሯ ያላትን ሃብት የወያኔ መሪዎች ከንግድ ሸሪኮቻቸውና ከባለውለታና አጋር ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በመሆን እየበዘበዙና በባዕድ ሀገርም ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብትና ንብረት እያከማቹ መሆናቸው ይታወቃል። የኖርዌይና የእንግሊዙ ማዕድን አውጭዎች በቅርብ ጊዜ ወደ ማዕድን ቁፋሮ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ የአቶ አንዳጋቸውን ፅጌ ጉዳይ መመርመር እንደሚጀምር አስታወቀ

የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በውጪ አገራት በእስር ላይ የሚገኙ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን (በኢትዮጵያ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ) እስረኞች ጉዳይ በማጥናት መንግስት በውጪ አገራት በሚገኙ እንግሊዛዊያን ላይ የሚፈጸምን የሰብዓዊ መብት ረገጣን ለማስቀረት የሚያሳየውን ቁርጠኝነት እመዝናለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ባለፈው ዓመት የነሐሴ ወር የወጣን ሪፖርት ኮሚቴው መመልከቱ የተገለጸ ሲሆን በሪፖርቱ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጽሙ አገራት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ለሰብዓዊ መብት መከበር ግድ የማይሰጠው መሆኑን ታዝበዋል ተብሏል፡፡
በፓርላማው የተዋቀረው የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በመንግስት የሰብዓዊ መብት አከባበር ስራ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግ በመግለጽ በውጪ አገራት የሚገኙ እንግሊዛዊያን እየደረሰባቸው የሚገኝን የመብት ጥሰት በዝርዝርና በጥልቀት በመመልከት የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር መንግስት የተጓዘውን ርቀት እንደሚቃኝ አውስቷል፡፡
በለንደን የአንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመርዳት ላይ የሚገኘው ሪፕራይቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው ከሆነም የፓርላማ ቡድኑ በዋናነት የአቶ አንዳጋቸውን ጉዳይ መመርመር ይጀምራል፡፡
አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጪ መያዛቸውን በመቃወም የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ፓርላማ አንዳርጋቸውን ኢትዮጵያ በነጻ እንድትለቅ ሲጠይቁ የእንግሊዝ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ሳያቀርብ በመቆየቱ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል፡፡ሪፕራይቭ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ዋነኛው ደጋፍ አድራጊ መሆኑን ማጋለጡ አይዘነጋም፡፡

Aseged Tamene

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: