በአፋርና በኢሳ ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በአፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ በአፋርና በኢሳ ሶማሊ ጎሳዎች መካከ ግጭት ተቀስቅሶ በግንሹ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ሰዎችም ለጉዳት መዳረጋቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሰኞ ገለጠ።
በወረዳው አስጊታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት አንድ የአፋር ተወላጅ ወጣት በኢሳ ሶማሊ ጎሳ መገደሉ ተከትሎ እንደሆነ የድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ገሃስ መሃመድ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።
በአካባቢው ሰኞ ምሽት ድረስ የተኩስ ልውውጥ በመካሄድ ላይ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሎ ስጋት መኖሩን ሃላፊው አስታውቋል።
በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ለዘመናት ሲቀርቡ የነበሩ አስተዳደራዊ ጥያቄዎች እልባት ባለማግኘታቸው ምክንያት በወረዳው ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝም የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃጎስ መሃመድ ተናግረዋል።
ሁለቱ ጎሳዎች እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከግጦሽ መሬት ጋር በተገናኘ በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ይገቡ እንደነበር ያወሱት ሃላፊው በአካባቢው መነሳት የጀመሩ አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ጉዳዩ በሚመለከታቸው የመንግስት ሃላፊዎች በኩል ችላ መባላቸው ሳቢያ ግጭቱ በአዲስ መልክ መቀጠሉን አስረድተዋል።
በዚሁ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ውጥረት አፋጣኝ እልባትን ካላገኘም ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰታቸው እንደማይቀር የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አክሎ አመልክቷል

11329989_1062444910449995_7995307124947863635_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: