በአመት 44 ሺህ ኢትዮጵያውያን በካንሰር ይሞታሉ
April 11, 2016 Leave a comment
በኢትዮጵያ በቀን 120 በዓመት 44 ሺህ ኢትዮጵያውያን በካንሰር ይሞታሉ” አዲስ አድማስ ጋዜጣ ሚያዝያ 1/2008 ዓም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የካንሰር መከላከልና ቁጥጥር ፕሮግራም የቴክኒክ አማካሪ ዶክተር ኩኑዝ አብደላን ጠቅሶ እንደዘገበው።
ለምን? የኬሚካል ማዳበርያ? ጤንነታቸው ያልተረገጋገጠ የምግብ ዘይቶች? ወይንስ ሌላ? ነጋዴው መንግስት ገንዘብ እስካወጡለት ድረስ ከውጭ የሚያስገባቸው ምግቦች ለሕዝቡ ጤነኛ መሆናቸው ላይ ማን ይጨነቃል?
ካንሰር እያደገ የመጣ የጤና ችግር መሆኑንና በአገሪቱ በየአመቱ 44 ያህል ሺህ ሰዎች በካንሰር ሳቢያ ለሞት እንደሚዳረጉ፤ 77 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችም በካንሰር እንደሚጠቁ “አናዶሉ ኤጀንሲ” ዘገበ፡፡በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የካንሰር መከላከልና ቁጥጥር ፕሮግራም የቴክኒክ አማካሪ ዶክተር ኩኑዝ አብደላን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ የካንሰር ችግር በመስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚከሰተው የሞት መጠን 5.8 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍነውም በካንሰር በሽታ ሳቢያ የሚከሰት ሞት ነው፡፡ በአገሪቱ ለካንሰር ተጋላጭ በመሆን ረገድ ሴቶች ቅድሚያውን እንደሚይዙና ይህም እጅግ አሳሳቢእንደሆነ ለ“አናዶሉ ኤጀንሲ” የተናገሩት ዶክተር ኩኑዝ አብደላ፣ በካንሰር ሳቢያ ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል በሚል ሪፖርት ከተደረጉት መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡ በአገሪቱ በአዋቂ ሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር አይነቶች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የጡት ካንሰር እንደሆነም አስረድተዋል፡፡መንግስት ካንሰርን ለመከላከልና ለማከም ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ የጠቆመው ዘገባው፤ በተመረጡ 118 ሆስፒታሎች የማህጸን በር ካንሰር ምርመራና ህክምናን ለማስፋፋት እየተሰራ እንደሚገኝ፤ የመድሃኒት አቅርቦትና ለካንሰር ህክምና የሰው ሃይል ማሟላትም ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙበት ገልጿል፡፡