የወያኔ ስርሃት ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ዘገበ

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነቶችንና አመለካከቶችን በተገቢው ሁኔታ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው በሃገሪቱ ተቃውሞ ኣየተባበሱ መምጣቱን የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ አርብ ዘገበ።
በተለያዩ ክልሎች መጠኑን እያሰፋ የመጣው ይኸው ተቃዎሞ በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበርና በዴሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄዎች ላይ ጥያቄ አስነስቶ እንደሚገኝም ጋዜጣው አስነብቧል።
በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ በትንሹ 266 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ያወሳው ጋዜጣው አስተዳደራዊ ጥያቄን ባነሱ የኮንሶ ማህበረሰብ ዘንድም የሃይል እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።
የሃገሪቱን የብሄር ብሄረሰቦች መብት በመጠቀም በደቡብ ክልል የተነሳውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎ የኮንሶ ማህበረሰብ መሪ የሆኑን ካላ ገዛኸኝ በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበረም ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ በዘገባው አውስቷል።
በአማራ ክልል ከቅማት ማህበረሰብ የአስተዳደር ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለአመታት የቆየ ተቃውሞ ሲሰማ መቆየቱን የዘገበው ጋዜጣው በሃገሪቱ የፖለቲካ አመለካከቶችና ልዩነቶች በአግባቡ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው በመንግስት ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎች እየተባባሱ መምጣታቸውን አስነብቧል።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውንና ብሄርን ማዕከል ያደረገው የፌዴራሊዝም ስርዓትም የተጠበቀውን ያህል መረጋጋትና ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችልም በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ገልጸዋል።
የፌዴራል መንግስት በክልሎች ሊያካሄድ ባሰበው የኢኮኖሚና ተዛማች ጉዳዮች ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር ምክክሮችን ማካሄድ ቢጠበቀበትም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌዴራሊም ባለሙያ የሆኑት አቶ አሰፋ ፍሰሃ ለዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ አስረድተዋል።
የፌዴራል መንግስት ክልሎችን ሳያማክር ሰፋፊ የስኳር ፋብሪካዎችንና ሌሎች ፕሮጄክቶችንም በራሱ ስልጣን እያከናወነ እንደሚገኝ ጋዜጣው የተለያዩ መረጃዎች በምሳሌነት በማቅረብ ዘግቧል።
ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉን ያወሳው ጋዜጣው ውጤቱን ተከትሎ መቀስቀስ የጀመረው ተቃውሞ በፓርቲው የበላይነት ላይ ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ ማሳያ ነው ሲል ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል።
በሃገሪቱ ያለው የፌዴራል ስርዓትም ከተለያዩ አካላት ዘንድ ጥያቄ እየቀረበበት እንደሚገኝም ጋዜጣው አክሎ ዘግቧል።

12376295_1018502434888475_6231050438946837590_n

http://www.theguardian.com/global-development/2016/apr/08/ethiopia-clampdown-dissent-ethnic-federal-structure

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: