የሳምንቱ አበይት ዜናዎች

1796634_222183061305326_875283870_n99994-430426_159963350831423_915461233_n

ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጠው

የኖርዌይ መንግሥት 800 ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለሁ ማለቱ 

የወያኔ መንግሥት ድረ ገጾችን ሰብሮ የመግባት ጥቃት መፈጸሙን፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ለፓርላማው ገለጹ፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ በድርቅ በተጎዱ ቦታዎች በተላላፊ በሽታዎች እየተጠቁ ነው ተባለ

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች፤ ከእስር ከተለቀቁም በኋላ አገር ውስጥ በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ እንዲሁም ለሽልማት፣ለትምሕርትና ለሥልጠና ላገኟቸው ዕድሎች ከአገር መውጣት እንደተከለከሉ ገለጹ፡፡

የኖርዌይ መንግሥት 800 ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለሁ ማለቱ 

ባለፉት ሳምንታት ኖርዌይ ተግባራዊ ለማድረግ ያሰበችውን የስደተኞች አዲስ እቅድ ምክንያት በማድረግ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከ800 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ያለፍላጎታቸው ወደሃገራቸው ለመመለስ መወሰናቸውን የኖርዌይ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸውን ተከትሎ። የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር Erna Solberg ስደተኞችን በአግባቡ ለመለየት በሚደረገው አካሄድ ወደሃገራቸው የሚመለሱ ሰዎች እንዳሉ በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና፣ ስደተኞችን ያለ-ፍላጎታቸው ወደሃገራቸው እንዲመለሱ ማስገደዱ ተገቢ አይደለም በሚል የተለያዩ አካላት በኖርዌይ መንግስት ላይ ቅሬታን እያቀረቡ የሚገኙ ሲሆን ውሳኔውም ማሻሻያ እንዲደረግበት አሳስበዋል።

ኖርዌይ ጥብቅ የተገን አሰጣጥ ፖሊሲ ያጸደቀችው ባለፈው አመት ሲሆን በርካታ ስደተኞችን በግዳጅ ወደ መጡበት ለመመለስ የምታደርገው ጥረት የ.ተ.መ.ድ. ጨምሮ ከበርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ነቀፋ ገጥሞታል።

ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጠው

የወያኔ መሪዎች የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንዲያስችላቸው በውጭ ሀገራት የማግባቢያ ሥራ  (የሎቢ ሥራ) ለሚሰሩላቸው ኩባንያዎች የአገሪቱን  ሀብት ማዕድኗን እንዲበዘብዙ  መንገዶችን ሲያመቻቹ መቆየታቸው ይታወቃል። ከአፋር ግዛት ከሰመራ የሚመጡ መረጃዎች  እንደሚያመለክቱት ከአስር ዓመት በፊት ለቀድሞ የወያኔ መሪና ጠቅላይ ሚኒስትር  ለመለሰ ዜናዊ ሽልማት የሰጠው ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ከኖርዌይ ያራ በተጨማሪ አንድ የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያም ይህንኑ የአፋር  ማዕድን እንያወጣ ተፈቅዶለታል። ኢትዮጵያ በከርሰ ምድሯ ያላትን ሃብት የወያኔ መሪዎች ከንግድ ሸሪኮቻቸውና ከባለውለታና አጋር ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በመሆን እየበዘበዙና በባዕድ ሀገርም ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብትና ንብረት እያከማቹ መሆናቸው ይታወቃል። የኖርዌይና የእንግሊዙ ማዕድን አውጭዎች በቅርብ ጊዜ ወደ ማዕድን ቁፋሮ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የወያኔ መንግሥት ድረ ገጾችን ሰብሮ የመግባት ጥቃት መፈጸሙን፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ለፓርላማው ገለጹ፡፡

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ ወቅት የመንግሥት ድረ ገጾችን ሰብሮ የመግባት ጥቃት መፈጸሙን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ለፓርላማው ገለጹ፡፡
የተሰነዘሩት ጥቃቶች በአብዛኛው ያተኮሩት በወረዳ ኔት ድረ ገጽ ላይ መሆኑን፣ ለሚመለከታቸው ተቋማትና ለመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የማሳወቅ ሥራ በማከናወን የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት ጥረት መደረጉን፣ ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸማቸውን ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ አሁን ግን ችግር የገጠማቸው ድረ ገጾች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
የወረዳ ኔት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ሁሉንም የአገሪቱ ወረዳዎች በአንድ የሚያገናኝ ሲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚገኘው የብሔራዊ የዳታ ማዕከል ውስጥ የተካተተ መሆኑ ይታወቃል፡፡
‹‹ግርግር ሲጀመር ነው የወረዳ ኔት ድረ ገጽ ላይ ጥቃት የተሰነዘረው፡፡ ከየትኛው አገር እንደተሰነዘረም አውቀነዋል፡፡ ልዩ ትኩረትም እንሰጠዋለን፤›› በማለት ሚኒስትሩ ለፓርላማው አሳውቀዋል፡፡
 በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋትና መቆራረጥ በቴሌ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መምጣቱን ገልጾ  አሁን ግን ቴሌ የራሱ የኃይል አማራጭ ይኖረዋል ይበል እንጅ በኢትዮጵያ መፍተኄው ስለጠፋለት የኤሌክትሪክ መቋረጥና መጥፋት የተነፈሰው ነገር የለም።  

ይህ በንዲ እንዳለ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የማህበራዊ ሚዲያዎች Block መደረጋቸውን ነዋሪዎች ገለፁ በዚህም ፌስቡክ ቫይበር ቲውተር ና የመሳሰሉትን ለመጠቀም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ተናግርዋል

በሀገራችን ኢትዮጵያ በድርቅ በተጎዱ ቦታዎች በተላላፊ በሽታዎች እየተጠቁ ነው ተባለ

የየአካባቢዉ ነዋሪዎችና አንዳድ የዜና ምንጮች «ኮሌራ» የሚሉት በሽታ አንዳድ አካባቢዎች በርካታ ሰዉ ገድሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለበሽታዉ አጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት የሚለዉን ሥም ነዉ የመረጠዉ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በደቡብ፤ በኦሮሚያ እና በሶማሌ መስተዳድር የተዛመተዉ የተቅማጥና ትዉከት በሽታ የሰዉ ሕይወት ማጥፋቱ ተዘገበ። የየአካባቢዉ ነዋሪዎችና አንዳድ የዜና ምንጮች «ኮሌራ» የሚሉት በሽታ አንዳድ አካባቢዎች በርካታ ሰዉ ገድሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለበሽታዉ አጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት (አተት) የሚለዉን ሥም ነዉ የመረጠዉ። የጤና ጥበቃ ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ በድርቁ እና በንፅሕና ጉድለት ምክንያት ከተቅማጥና ትዉከቱ በተጨማሪ የማጅራት ግትር (ሜኔን ጃይትስ) በሽታም በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል። በበሽታዉ ሥለሞቱ ወይም ሥለታመሙ ሰዎች ብዛት ግን በግልፅ የተነገረ ነገር የለም።

  የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች፤ ከእስር ከተለቀቁም በኋላ አገር ውስጥ በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ እንዲሁም ለሽልማት፣ለትምሕርትና ለሥልጠና ላገኟቸው ዕድሎች ከአገር መውጣት እንደተከለከሉ ገለጹ፡፡

ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ከእሥር ከተለቀቀ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ሲናገር፤ ከመታሠሩ በፊት ይሠራበት የነበረው መጽሔት በመዘጋቱ ምክኒያትሥራ እንደሌለው ገልፆ ነገር ግን ጀርመን አገር በሚገኘው ዜድ.ኤ.ፍ ZDF) ለሥልጠና ተጋብዞ ደርሶ ሲመለስ፤ “መጀመሪያ እንዴት ወጣህ?፣የሚጣራ ነገር አለ” በሚል የጉዞ ሰነዱን ወይም ፓስፖርቱን እንደተቀማ ተናግሯል፡፡

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምሕር የነበረው ጦማሪ ዘላለም ክብረት በበኩሉ ገና እሥር ቤት እያለ ከሥራ መሰናበቱን ተናግሯል። ከተፈታም በኋላ ሽልማት ለመቀበል ለተደረገለት ጥሪ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክር ፓስፖርቱን እንደተቀማ ተናግሯል፡፡

ለአምስት ወራት ያሕል ፓስፖርቱን ለማግኘት በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም ማግኘት እንዳልቻለም ይገልፃል፡፡ እንዲሁም ለዚህ ዓመት አሜሪካ ውስጥ ለሚሰጠው የወጣት አፍሪካውያን መሪዎች ፌሎሽፕ (Young African Leaders Initiative (YALI) ቢያሸንፍም እስካሁን የጉዞ ሰነዱን ማግኘት ባለመቻሉ ዕድሉ ያልፈኛል የሚል ስጋት እንዳለው ይናገራል፡፡

መከላከል ሳይገባቸው በነፃ የተለቀቁት ጦማርያኖቹ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር ተሰኝቻለሁ› በማለት ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በታህሳስ 04/2008 የተፃፈ ይግባኝ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ይግባኝ ማቅረቡ ይታወቃል

AsegedTamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: