ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በዋልድባ ቁጥጥር ሲያደርጉ መሰንበታቸው ታወቀ

የገዳሙ አባቶች እንደገለጹት መጋቢት 27 የተከበረውን የመድሃኒአለም በአል ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በገዳሙ በመግባት ቁጥጥርና ክትትል ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ ሁሉም ደህንነቶች ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ የህወሃት ደህንነቶች መሆናቸውን የሚናገሩት አባቶች፣ ከወልቃይትና ከጎንደር ወደ ገዳሙ የሄዱ ምእመናን ከቤተሚናስ መነኮሳት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አላችሁ በማለት ሲያዋክቡዋቸው እና ሲከታሉዋቸው ሰንብተዋል፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ያሰጋቸው የህወሃት ደህንነቶች፣ ገዳሙን በተለዬ ሁኔታ ቁጥጥር እያደረጉበት ነው፡፡
ከወልቃይት ፣ ከጠገዴ ፣ ከዳንሻ፣ ሁመራ፣ አርማጭና ቆላ ወገራ በወልቃይት መዘጋ አድርገው ወደ ገዳሙ የሚሄዱ ቤተክርስያን ሳሚዎችን፣ ዛሬማ ወንዝ ላይ በማስቆም ከፍተኛ ፍተሻ ሲያደርባቸው ሰንብቶአል፡፡
በተለይ ማይበልጣ አፋፍ ወይም ውዳሴ ማርያም በተባለው ቦታ እና ሶስት ምእራፍ ላይ ከ200 ያላነሱ ምእመናን በሃወሃት የደህንነት አባላት ፍተሻ ተደርጎባቸው ንብረታቸው በሙሉ እንደተወሰደባቸው አባቶች ለኢሳት ተናግረዋል፡፡ በዚህ አካባቢ ፍተሻ ሲያካሂዱና ዝርፊያ ሲፈጽሙ የሰነበቱት የህወሃት ታጣቂዎች 4 ወንዶችና አንድ ሴት ሲሆኑ፣ ሴቶች የአንገት ሃብላቸው ሳይቀር እየተቆረጠ ተወስዶባቸዋል፡፡
ህወሃት የአካባቢው ህዝብ ተገናኝቶ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ እንዳይመክር የቀየሰው ስትራቴጂ መሆኑን የሚገልጹት የአይን እማኞች፣ ገዳሙ ከዚህ ቀደም ከደረሰበት ከፍተኛ ጥቃት በተጨማሪ ከወልቃይት ጥያቄ ጋር በተያያዘም ሌላው የጥቃት ማእከል ሆኖአል፡፡
በአሁኑ ሰአት ህወሃት መላው የትግራይ ህዝብ በወልቃይት ጥያቄ ጉዳይ ከህወሃት ጎን እንዲቆም ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን፣ ህዝቡን ለግጭት የሚያነሳሱና አንዱን ብሄር ጠላት አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ጥረት ህወሃት ከደርግ ጋር በነበረው ጦርነት ወቅት ያደርግ ከነበረው ቅስቀሳ ጋር ተመሳሳይ ነው በማለት ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ፡፡

ኢሳት ዜና

 በጎንደር ከተማ የነበሩትን ዋልድባ ገዳማውያን አስገድደው ወደ አዲርቃይ ለስብሰባ በሚል ተወስደዋል የገቡበትም አልታወቀም

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: