የትግራይ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ በአሰፈራቸው ካድሬዎቹ በኩል አዲስ ጥቃት መፈጽም ጀምሯል።

719e1-tigray-after-1991_011012

በመጥሪያ ወረቀት እየጠሩ 90 በመቶው ሴት እንዲሰበሰቡ ካደረጉ ብሗላ ተወላጅ ሴቶቹ ለባሎቻቸውና ልጆቻቸው እንዲሁም ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸው እንዲመክሩ በታላቅ ማስፈራሪያ በስብሰባው ሲናገሩ ሰንብተዋል። በትላንትና ከስአት ብሗላ በተደረገው ስብሰባም በመጨረሻው የሴቶቹ ስነ-ልቦና ያናደዳቸው የመቀሌው ወያኔ “አማራ ነን ብላችሁ ከምትሞቱ የወያኔ ዱላ እየተገረፋችሁ በህይወት ብትኖሩ ይሻላችሗል፤ አማራ ከሆናችሁ ብሗላም ከሞት አታመልጡም” በማለት በማን አለብኝነትና በትዕቢት እብሪተኛ ንግግራቸውን በይፋ አሰምተዋል። ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን ሆይ የእነዚህ ጥጋብ እኮ በጣም የሚገርም ነው!!

ሌላኛው አስገራሚ ክስተት በዳንሻ ከተማ ላይ ወያኔ ሰፋሪዎችና ካድሬዎቹ አሰባስቦ የሙዚቃ ባንድ አስደግሶ እየጨፈረ የዳንሻ ህዝብን በስድብና ዛቻ ለማሸማቀቅ እየሞከረ ነው። ከሳምንቱ የትንኮሳ ዘመቻ ግን የዛሬውና የትላንት ውሎ በጣም የተለየ ነው። በእነዚህ ሁለት ቀናት አዳራሽ ዘግተው እየጨፈሩ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የፈልጉትን ነገር ማድረግ እንዲችሉ ፊርማ አሰባስበው ከመቀሌ ለመጡት ወያኔዎች በመጠየቃቸው ምክንያት ወያኔም በህዝቡ ላይ የፈለጉትን ማድረግ እንዲችሉ ፈቃዴና ደስታዬ ነው በማለት በይፋ አረጋግጦላቸው በፉከራ ከአዳራሻቸው ወጥተዋል። ለምሳሌ ትላንት እና ዛሬ በጠገዴ ወረዳ በዳንሻ ከተማ በሚገኙ የትግራይ ሰፋሪዎች በኩል በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጥቃት ለመፈጸም ብር እያዋጡ ነው።

ወ/ሮ የሻረግ ሙጬ ትባላለች የጎንደር እብናት ተወላጅ ናት፡፡ ትዳር መስርታ ዳንሻ ከተማ የምትኖር ሲሆን ለመተዳደሪያዋም ሆቴል ከፍታ በሥራ ላይ ብዙ ዓመታትን አስቆጥራለች፤ የሆቴሏ ስም ደግሞ “ጣና ሆቴል” ይባላል፡፡ ወ/ሮ የሻረግ ባለቤቷ የትግራይ ተወላጅ ሲሆን ጎይትኦም ጣና እየተባለ በሆቴሉ ስም ነው የሚታወቀው፡፡

ታዲያ ከሰሞኑ ከወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ጉዳይ ጋር በተያያዘ አቶ ጎይቶም ጣና እና ሌሎች የትግራይ ተወላጅ ወዳጆቹ በሚስጥር ተሰባስበው “ወልቃይቴዎች ጠግበዋል ብር አዋጥተን እናስገድላቸው” የሚል አጀንዳ ነድፈው ለጉዳዩ ማስፈፀሚያም የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ ከወሰኑ ብሗላ

1ኛ. ጎይትኦም ጣና 50,000 ብር

2ኛ. ተላ ካሳሁን 50,000 ብር

3ኛ. ተክላይ ሃበሽ 60,000 ብር

4ኛ. ሲሳይ ገ/መድህን 60,000 ብር

5ኛ. አወጣሃኝ አያልነህ 50,000 ብር

6ኛ. ገ/ክርስቶስ ሰሊጥ ነጋዴ 60,000 ብር

7ኛ. ጉዕሽ ገ/ስላሴ 60 ካሳ ቢራ(ራያ ቢራ ማከፋፈያ)

8ኛ. ቴዲ ማደያ 100,000 ብር

9ኛ. ግሩም ቡቲክ 60,000 ብር

10ኛ. ቁንጬ ባለ ሲኖትራኩ 50,000 ብር እንዲሁም ሌሎችም እንዳቅማቸው አዋጥተው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ይህን ሚስጥር ያወቀች የአቶ ጎይቶም ባለቤት ወ/ሮ የሻረግ ሙጬ በጣም ስለተናደደች ባለቤቷን “አንተ ለወልቃይቴዎች ማስገደያ 50,000 ብር ስትከፍል እኔ ደግሞ ለወልቃይቴ ወገኖቼ ራሳቸውን የሚከላከሉበት 100,000 ብር ልክፈልና ሂሳብ አድርገን እንለያይ” ስትለው ይሄማ አይሆንም ወልቃይቴዎች እኮ ጠላቶቻችን ናቸው ብሎ ይመልስላታል፡፡ ጉዳዩ የከነከናት ወ/ሮ የሻረግ የባሏን ሀሳብ ባለመቀበል “አሁኑኑ መለያየት እፈልጋለሁ” በማለት እቀጩነን በመናገር ወዲያውኑ ከባለቤቷ ጋር ተለያይታ ዕቃዎቿን ጭና ጎንደር ከተማ ገብታለች፡፡

በተጨማሪም ትግሬ ባል ያሉዋቸው ሌሎች የአማራ ተወላጅ ሴቶችም ካድሬ ባሎቻቸውን በወልቃይት ህዝብ ላይ ባሴሩት ምስጢራዊ ሴራ ምክንያት ትዳራቸውን እየፈቱ ይግኛሉ፤ አንዷ የወልቃይት ተወላጅም የባለቤቷን እኩይ ተግባር በመቃወም “መከራዬን አይቼ ለፍቼ ባመጣሁት ገንዘብ በወገኖቼ ላይ ይህንን ነገር ብታደርግ እኔ እራሴ እንደማጠፋህ እወቅ” በማለት ድምጿን ከፍ አድረጋ ሁለት የወልቃይት ጠገዴ ሰዎች ባሉበት በንዴት በዛሬው ቀን በግልጽ ተናግራዋለች፡፡

በስብሰባውም ልታውቁት የሚገባችሁ ነገር ካሉን ብሗላ “ሁሉም ትግሬ ወያኔ ነው፤ ወያኔን የሚጠላ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው” ካሉ ብሗላ ነገሩን የእብደት የሚያደርገው ደግሞ ለእያንዳንዱ ትግሬና እና “ነፍሱን ማትረፍ” የሚፈልግ የአካባቢው ተወላጅ የክተት አስቸኳይ ጥሪ በማቅረብ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እንዲሁም በአማራውና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከዛሬ ጀምሮ “ጥቃት” እንዲፈጽሙ ጠይቋል። ስለሆነ “የወያኔ ጠላት ሁሉ አንገቱ እንቆርጠዋለን” ትላንትና እያሉ በመዛት ሲያስፈራሩን ውለዋል ።

በመጨረሻም እኛ የወልቃይት ጠገዴ አማራ የጎንደር ህዝቦች ዘራችንን ለማትረፍና ትውልዳችንን ለማስቀጠል በምናደርገው ህጋዊ እንቅስቃሴ የአለም ህዝብ ከጎናችን እንዲቆምና ወያኔ እያደረሰብን ያለውን የዘር ማጥፋት ስራ በቃ እንዲልልን በትህትና እንጠይቃለን። መላው የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናችን በመቆም ወንበዴው የእኛ የወገኖቹን መገፋት አይቶ የወያኔን ምትሰራው ግፍ ይብቃህ እንዲልልን ይሔው አስቸኳይ ጥሪ አቅርበልንሃል።

ከወልቃይት ጠገዴ ጎንደር ኢትዮጵያ

መጋቢት 28 /2008 አ/ም

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: