ሰበር መረጃ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን መከላከያ አባላት እየከዱ ነዉ።

sirag-fergesa-and-samora-300x200

በምእራብና ደቡብ ምስራቅ እዝ ዉስጥ ባልደረባ የነበረዉና በሶማሌያ እንዲሁም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እየተዘዋወረ ለረጅም አመታት ያገለገለ በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር ስልጠና ዋና መምሪያ የሜጀር ጄኔራል ኋየሎም አራአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዉስጥ የስድስት ወር ብቻ የለብለብ የመኮንነት ስልጠና አጠናቆ የተመረቀዉ ም/መቶ አለቃ መላኩ አበበ ነጋሽ የህወሃትን ሰራዊት ተነጥሎ የሸሸ ሲሆን ብዛት ያላቸዉ የሰራዊቱ አባላት ህወሃትን የማገልገል ፍላጎት እንደሌላቸዉና አጋጣሚዎችን እየተጠባበቁ እነደሆነ ለመረዳት ችለናል።
በአንኳርነት የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን አካዳሚዎች አንድ መኮንን አሰልጥኖ ለመመረቅ የሚወስዱትን እጅግ አጭር ወቅት ከመመልከት አንጻር ምን ያህል የወያኔ መኮንኖች በብቃት እንደሚያገለግሉ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናቱ በምን ያህል ግዜ የጄኔራልነት ቆቡን እንደሚጭኑት ለመገመት አመላካች መረጃ ሆኖ ከማግኘታችን በላይ የሰራዊቱን መማረርና መንቃት ለመረዳት ችለናል።
በመሆኑም በሐገር መከላከያ ሰራዊት ስም የህወሃት ጥቅም አስጠባቂ አንሆንም! ያሉ በርካታ የመከላከያ ሹሞች መብቱን በሚጠይቀዉ ጭቁኑ ህዝባችን ላይ አፈ ሙዝ አንመዝም ሲሉ በመነጠል ላይ ሲሆኑ።
በተጨማሪ የአንድ ዘር የበላይነት የነገሰበት የሐገር መከላከያ አባል መሆን አያሻንም! የወያኔ ባለስልጣናትን ኪስ ለማደለብ በሶማሌያ በከንቱ አንታረድም! ከሐገራችን ምድረ እርስት ላይ ተቆርሶ ለሱዳን መሬታችን ሲሰጥ ዝም ብለን አንመለከትም! ዝርፊያና ግፍ የነገሰበት ስርአት ጥቅም አስጠባቂ አንሆንም! በማለት ሰራዊቱ እየፈራረሰ መሆኑን እማኞች የገለጹሲሆን።
በተለይም ሌላዉን የመጨፍለቅ እራይ ያለዉን የወያኔን ወታደራዊ ስልት ከመዋጋት አንጻር ሁሉም የመከላከያ አባልት የሚቻላቸዉን እርምጃ እንዲወስዱ እያሳሰብን !!!!!!!
በስብሶ በመደርመስ ላይ ከሚገኘዉ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን የግፍ ቤት ፍርስራሽ ሌሎች አባላት እራሳቸዉን እንዲያድኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: