ዛሬ ጅጅጋችን የሃዘን ድባብ አጥልቶባት ውላለች !!!

ትላንት ምሽት በጎረቤታችን ጭናክሰን ከተማ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በሌሊት ሳይታሰብ በደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ በአዲሱ ታይዋን እና በኪዳነ ምህነት ሰፈሮች እስካሁን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የበርካታ ሰው ህይወት አለፈ::

ለዚህ ሁሉ ሰው ሞትና ቁጥር ስፍር ለሌለው ንብረት ውድመት ምክንያት የሆነው ይህ የጎርፍ አደጋ ጉዳቱ እንዲህ ሊሰፋ የቻለበት ምክንያት ከውሃው ሃይልና መጠን ባልተናነሰ :-

– በአዲሱ ታይዋን ሰፈር ያሉት መኖሪያ ቤቶች ወደ ጎርፍ መውረጃው መንገድ በጣም ተጠግተው የተሰሩ በመሆናቸው ፣

– በኪዳነ ምህረት ሠፈር ደግሞ በቅርቡ ለተጀመረው የመንገድ ግንባታ የፈራረሱ ቤቶች ፍራሽ እየተወሰደ የተደፋው በውሃው መውረጃ ቦታ ላይ በመሆኑ ፣
እንደሆነ በቦታው የነበሩ የዓይን እማኞች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል::

ከሁሉ ከሁሉ አንጀት የሚበላው ነገር ደግሞ በጎርፉ የተነጠቁትን የቤተሰብ አባል አስከሬን አጥተው ለመፈለግ እዚህም እዚያም የሚዳክሩ ወገኖችን ማየት ነበር::

ከአንድ ቤት ስድስት፣ ከአንድ ቤት ዘጠኝ እየተባለ የሰው ነፍስ እንደ እቃ በቁጥር ሲገለፅ መስማት ዛሬ ጅጅጋ ላይ የተለመደ ነገር ሆኖ ነበር የዋለው::

በዚህ ይብቃሽ ያልተባለችው ከተማችን በዚሁ በዛሬው እለት ምሳ ሰዓት ገደማ ደግሞ ተማሪዎችን የጫነ ባጃጅ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት እና 06 ቀበሌ ደግሞ አንድ የኤሌትሪክ ትራንስፈርመር ፈንድቶ እሳት ማስነሳቱ ሲሰማ “የዛሬውስ ጫን ያለው ነው”! እያለ ሁሉም በየእምነቱ “እግዚኦ” ማለት ጀምሮ ነበር::

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: