በወልድያ ከተማ በተከሰተ የጎርፍና መሬት መንሸራተት ምክንያት 78 ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

ባሕር ዳር፡መጋቢት 25/2008 ዓ/ም(አብመድ) መጋቢት 22 ቀን2008 ዓ.ም በወልድያ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይሁለት ሰዓት ተኩል በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተከሰተ ጎርፍና የመሬትመንሸራተት በ78 ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

የወልድያ ከተማ አስተዳደር እና የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተጎጅዎችን ለማቋቋም እየሠሩእንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ጎርፉ ወንዝ ያቋርጥ የነበረ የአንድ ጎልማሳን ሕይወትም ቀጥፏል፤የአካል ጉዳት እንዲደርስም ምክንያት ሆኗል፡፡

በወልድያ አካባቢ ሰሞኑንም መለስተኛ ዝናብ ይጥል ስለነበረ ልዩጥንቃቄ እንዳላደረጉ የሚናገሩት በጎርፉ የተጠቁ ነዋሪዎች በ22ምሽት የጣለው ዝናብ ግን በእጅጉ የተለየና ከባድ ነበር፡፡

ከዝናቡ መክበድና ከቦታው አቀማመጥ የተነሳ ከባድኛ ጎርፍበመከሰቱና ያንኑ ጎርፍ የሚያስተናግድ በቂ ተፋሰስ አለመሠራቱለአደጋው የከፋ መሆን አስተዋፅ ማበርከቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በዚህም የተነሳ በበርካታ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ጎርፍ በመግባትየቤት ውስጥ ቁሳቁስ፣ አልባሳትና ቀለብ ጠራርጎ ወስዷል፡፡ለአካል ጉዳትም ምክንያት ሆኗል፤ ልጆቻቸው በውስጥ ሆነው ቤትቆልፈው መልሰው ለመክፈት የተቸገሩባቸውና ጎርፍ ቤቱንየሞላባቸው እናት ልጆቻቸውን ለማውጣት በእጃቸው የበርመስታውት በመስበራቸው መለስተኛ ጉዳት በእጃቸው ላይደርሶባቸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ፀሐይ መንገሻ እንደገለፁት በጎርፍየወደመው ንብረት ዘገባው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 4 ነጥብ 8ሚሊዮን ብር ተገምቷል፤ ጎርፍ የገባባቸው ቤቶችም 78 ደርሰዋል፤አሀዙ ግን ሊያሻቅብ እንደሚችልና ጥናቱ እንዳልተጠናቀቀምከንቲባው አስረድተዋል፡፡

በቦታው ተገኝተው የአደጋው ሰለባ የሆኑ ነዋሪዎችን የጎበኙት የአማራክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስለሽተመስገን በበኩላቸው አደጋውን ከዚህ ቀደም ለቅድመ ጥንቃቄበተሠሩ የተፋሰስ ሥራዎች መቀነስ የተቻለ ቢሆንም አሁንም ቀሪመሠራት ያለባቸው ሥራዎች እንዳሉ የተማርንበት ነው፤ ከዚህ በፊትየተሰሩ ተፋሰሶች የዲዛይንና የጥራት ችግር የነበረባቸው መሆኑጎርፉን ሙሉ በሙሉ መከላከል ሳያስችል ቀርቷል፡፡ አሁን ጉዳቱየደረሰባቸውን ዜጎች ለችግር እንዳይጋለጡ የምግብና መሰልአቅርቦቶችን በፍጥነት የማጓጓዝ ስራ ጀምረናል፤ አፋጣኝና ዘላቂመፍትሔም እንዲሰጥ ጠንክረን እንሠራለን ብለዋል፡፡

በወልድያ ከተማ ከሚገኙ ቀበሌዎች የጁገነት ቀበሌ አስተዳደርአካባቢ ያሉት ተክለሃይማኖት ኮንዶሚኒየም፣ ማረሚያ ቤትና ጎማጣቀጠናዎች በጎርፉ ክፉኛ የተጎዱ አካባቢዎች ናቸው፡፡ የጉዳት መጠኑየዚህን ያህል ባይሆንም ከአምስት ዓመታት በፊት በዚሁ ቀበሌተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ እንደነበርና ከዚያ በኋላ የተሠራየቅድመ ጥንቃቄ ሥራ አለመኖሩን የጎርፉ ተጠቂ ነዋሪዎችገልጸዋል፡፡

ከአንድ ወር በፊትም በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ አካባቢ ተመሳሳይ የጎርፍአደጋ ተከስቶ በመስኖ የለማ ሰብል አውድሟል፡፡ ዝናቡ ወቅቱንየጠበቀ የበልግ ዝናብ ቢሆንም የኤልኒኖ ታቃራኒ ውጤት ያለውላኒና ክስተት መጠኑን እንዲጨምር ምክንያት ሊሆንእንደሚችልም እየተገለፀነው፡፡

አብርሃም በዕውቀት

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: