መሀመድ አላሙዲን 433 ሚሊዮን 571 ሺህ 241 ብር በጊዜ ገደብ እንዲከፍል ተፈረደበት

የወያኔው የንግድ ሸሪክ የሆነው መሀመድ አላሙዲን ቤት ከዓመታት በፊት ግዥ የፈጸመባቸውን የንግድና የእርሻ ድርጅቶች ክፍያን በወቅቱ ባለመፈጸሙ ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ብር እንዲከፍል በወያኔው ፍርድ ተፈርዶበታል። ወያኔ የመንግስትና የሕዝብ ሀብት የነበሩትን ጎጀብ እርሻ ልማትን፤ አዲስ ጎማን የሊሙና የበበቃ የቡና እርሻን ለመሀመድ አላሙዲ ሜድሮክ ኩባንያ መሸጡ ይታወሳል። መሀመድ አላሙዲ የልማት እርሻዎቹን ሆርዘን ፕላንቴሽን በማለት ስያሜ ሰጥቶ ክፍያ ግን ባለመፈጸሙ ጊዜ ቢሰጠውም በገንዘብ ቀውስ ሊከፍል አለመቻሉ ታውቋል። የወያኔው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ችሎት ጉዳዩን ለወራት መርምሮ የልማት እርሻዎቹ ባለንብረት መሀመድ አላሙዲን ድርጅቶቹ ያላቸውን አጠቃላይ ዕዳ 433 ሚሊዮን 571 ሺህ 241 ብር በጊዜ ገደብ እንዲከፍል ካልከፈለ ከነወለዱ እንዲከፍል ወስኗል። የፖሊካ ተመልካቾች የወያኔ የፖለቲካ ፍርድ ቤት በወያኔ የንግድ ሸሪካ ላይ ይህን ውሳኔ የጣለው በቱጃሩና በውያኔ መካከል ያለው ፍቅር አልቆ ነው ወይስ ስግብግብና አልለጠግብ ባይ የሆኑት የወያኔ መሪዎች ውትሮችም በዘዴና በስልት የሰጡትን የሀገርና የሕዝብ ንብረት በህግና በፍርድ ቤት ስም ሊቀበሉት በማሰብ ነው በማለት ይጠይቃሉ።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: