በእሥር የሚገኙት የኦፌኮ መሪዎች የረሃብ አድማውን አቆሙ

በተጨማሪም በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኦሮምያ የተለያዩ ክፍሎች ተይዘው የት እንደደረሱ እንማይታወቅ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር ገልፀዋል።

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ – ኦፌኮ መሪዎች የሚገኙበት የእሥር ሁኔታ በጥቂቱ መሻሻሉ ተነግሯል። ላለፉት አምስት ቀናት ያደረጉትን የረሃብ አድማ አቁመዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኦሮምያ የተለያዩ ክፍሎች ተይዘው የት እንደደረሱ እንማይታወቅ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር ገልፀዋል።

ስለሰዎቹ መያዝ ከኦሮምያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሣካም።

መለስካቸው አምሃ የኦፌኮን ምክትል ሊቀመንበር አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

http://m.amharic.voanews.com/a/imprisoned-ofc-leadership-stop-hunger-strike/3258412.html

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment