ዐውደ ርእዩ እንዳይቀርብ የታገደው በመንግሥት አካል እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ባወጣው መግለጫ ገለፀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያÃÃÂ ማኅበረ ቅዱሳን ከመጋቢት 15 -21 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጁቱን አጠናቆ ዐውደ ርእዩን ለማቅረብ የሰዓታት እድሜ ሲቀረው መታገዱን አስመለክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ ሲሆኑ ዐውደ ርእዩን ለማዘጋጀት የተደረጉ ሒደቶችን አብራርተዋል፡፡ ዐወደ ርእዩን ለማዘጋጀት የተጠየቀው በ2007 ዓ.ም በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ እንደሆነና ከዚያ ቀደም ብሎ አንድ አካል በኤግዚቢሽን ማእከል ለማዘጋጀት ከአንድ ዓመት በፊት ማሳወቅ እንዳለበት የሚታወቅ በመሆኑ ይህንንም ተግባራዊ በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለሁለት ሳምንታት ኤግዚቢሽኑን ለማዘጋጀት በመስማማት ማኅበሩ ጥያቄውን ማቅረቡ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ኤግዚቢሽን ማእከሉ የመርሐ ግብር መደራረብ ስላጋጠመው ለአንድ ሳምንት እንድናዘጋጅ ተስማምተን የምናዘጋጅበት ጊዜ በጋዜጣ ላይ እንዲወጣ ተስማምተን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ፈቃድ እንዲሰጠን በመጠየቅ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፊርማ የተጻፈ ደብዳቤ በማቅረብ ከኤግዚቢሽን ማእከሉ ጋር ውል ተፈራርመን የመጀመሪያ ክፍያ ተከፍሏል ብለዋል፡፡

ከኤግዚቢሽን ማእከሉ ጋር የቀረበ ግንኙነትና ቀና ትብብር እንደነበራቸው የጠቀሱት ዋና ጸሐፊው ኤግዚቢሽኑን ለማዘጋጀት ወደ ሥራ በመግባት በተያዘው ጊዜ ለማቅረብ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አውስተዋል፡፡

በውላችን መሠረት መጋቢት 12 ቀን 2008 ዓ.ም የመጨረሻ ክፍያችንን ከፍለን አጠናቀናል ያሉት አቶ ተስፋዬ መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ.ም ጠዋት ግን ዐውደ ርእዩን የሚያዘጋጀው ዐቢይ ኮሚቴ ወደ ቦታው በማምራት ለኤግዚቢሽኑ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ለማስገባት የአዳራሾቹን ቁልፍ ሲጠይቅ ከኤግዚቢሽን ማእከሉ ችግር እንዳለና እቃ ማስገባት አትችሉም የሚል ያልተጠበቀ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከሚመለከታቸው የኤግዚቢሽን ማእከሉ ሓላፊዎች ጋር ውይይት ያደረግን ሲሆን እነሱም ጉዳዩ እንግዳ እንደሆነባቸው ገልጸውልናል፡፡

ኤግዚቢሽን ማእከሉ ሁለት ዓይነት አሠራር እንዳለው እናውቃለን፡፡ የመጀመሪያው ንግድ ፈቃድ ያላቸው አካላት ከንግድ ቢሮ ፈቃድ አስጽፈው በማምጣት ማዘጋጀት የሚችሉ ሲሆን ሁለተኛው የሃይማኖት ተቋማትና ግብረ ሠናይ ድርጅቶች ዕውቅና ከሰጣቸው አካል ፈቃድ ይዘው በመምጣት ዝግጅቶቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ ኤግዚቢሽን ማእከሉ ከእኛ ጋር በዚህ መሠረት ነው ውሉን የፈጸመው፡፡

በትናንትናው ዕለት እኛም ሆንን ሌሎች ሲያዘጋጁ በውሉ ያልተካተተና ተጠይቆ የማያውቅ ጥያቄ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ፈቃድ ካላመጣችሁ ማዘጋጀት አትችሉም በማለት ኤግዚቢሽን ማእከሉ ያልጠበቅነው ጥያቄ አቀረበልን፡፡ እኛም ከዚህ በፊት ይህ ጥያቄ ተጠይቀን አናውቅም ዛሬ ምን ተፈጠረ? ዐውድ ርእዩን ለማቅረብ አንድ ቀን ሲቀረን ነው ወይ የምትጠይቁን? በማለት ጥያቄያችንን መልሰን አቅርበናል፡፡

እነሱም ጥፋቱ የእኛ የኤግዚቢሽን ማእከሉ ነው ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን፣ ይህንንም በሚዲያ እናሳውቃለን በማለት መለሱልን፡፡ ጉዳዩን ይዘን ወደ አዲስ አበባ መስተዳደር ሔደን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ብናደርግም ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ መስተዳደር ከኤግዚቢሽን ማእከል እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ተጠይቆ እንደማያውቅና እንግዳ ነገር እንደሆነበት አሳወቀን ብለዋል፡፡

ዐውደ ርእዩ ለምን እንደታገደ አቶ ተስፋዬ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ዐወደ ርእዩ እንዳይቀርብ የታገደው በመንግሥት አካል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ በምን መነሻነት ሊታገድ እንደቻለም ለቀረበላቸው ጥያቄ ወደፊት ይህን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል በመወያየት ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ዐውደ ርእዩንም የት እና መቼ እንደሚቀርብ የማኅበሩ አመራር ወደፊት እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል፡፡

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ዐውደ ርእዩ እንዳይቀርብ የታገደው በመንግሥት አካል እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ባወጣው መግለጫ ገለፀ

  1. Pingback: ዐውደ ርእዩ እንዳይቀርብ የታገደው በመንግሥት አካል እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ባወጣው መግለጫ ገለፀ - EthioExplorer.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: