ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት

e6165-bemjdn4cmaamqwj

‹የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ›
ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅስያ የአንዲት ክርስቲያን ምእመንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው ነው፡፡ እንዳለው አልቀረም አውዶቅስያ ባደረሰችበት መከራ ተግዞ በዚያው ሞትን ተቀብሏል፡፡ እውነተኛ አባት ስለ በጎቹ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል እንጂ በጎቹን ለራሱ ክብርና ጥቅም ሲል አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ፓትርያርክ ማለት በግሪክ ‹ታላቅ አባት› ማለት ነው፡፡ የታላቅ አባት ተግባር የልጆቹን ሥራ ማፍረስ አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን መክሰስ አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን እንጂ አባት አያስፈልግም፡፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ጠርቶ መውቀስ እንጂ በር መዝጋት አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፡፡ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ማቀፍ እንጂ ማባረር አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን አለ፡፡
ፓትርያርኩ እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደዋዛ በአንድ ሙሰኛ ሲነጠቅ ተኝተዋል፤ በመሐል ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሠሩ ሕንጻዎች በጎጆ ቤት ዋጋ በሙስና ለዐሠርት ዓመታት ሲከራዩ ተኝተዋል፤ ከመንበረ ፕትርክናቸው ሥር ባለች አጥቢያ የቤተ ክርስቲንን ገንዘብ አናስበላም ያሉ ካህናትና ምእመናን ሲባረሩ ተኝተዋል፡፡ በሕዝብ ጥያቄ ሽፋን ጽንፈኛ አቋምን በሚያራምዱ ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ይተኛሉ፤ የስልጤ ዞን ምእመናን በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ እየተቀበልን ነው ሲሉ ይተኛሉ፤ ቤተ ክህነቱ የኑፋቄ ማኅደር ሲሆን ይተኛሉ፤ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሲዘጉ፣ ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች ሲበተኑ ይተኛሉ፤ በመሥዋዕትነት የተመሠረቱት የደቡብ አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት በሙሰኛ አመራሮች አደጋ ላይ ሲወድቁ ይተኛሉ፣ ይሄ ሁሉ ዘለፋና ኑፋቄ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲዘንብ ይተኛሉ፡፡
መናፍቃንን የሚተች ጽሑፍ በኦርቶዶሳውያን ተጻፈ ሲሏቸው፤ ምእመናንን የሚያጸና ጉባኤ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ ሕዝቡ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ ነው ሲሏቸው፤ ወጣቱ ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል እየተጋ ነው ሲሏቸው፤ ዲያስጶራው ሕዝብ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነ ሲሏቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጥ ዐውደ ርእይ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሊቀርብ ነው ሲሏቸው ያን ጊዜ ብዕራቸውን ይዘው ለማገድና ለመክሰስ ይነቃሉ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ‹ድንግል ሆይ የአንቺን ምስጋና ለመጻፍ ምንጊዜም ብእሬ ቀለም እንደያዘ ነው› ነበር ያለው፡፡ የፓትርያርኩ ብእር ግን ምእመናንን የሚያጽናና ጦማር ለመጻፍ ወይም ድንግልን የሚያመሰግን ድርሳን ለመድረስ የሚጨበጥ አይደለም፡፡ እንደ ጠንቋይ ብዕር ለማፍዘዝና ለማደንገዝ እንጂ፡፡
የፓትርያርክ ዋናው ሥራው የሀገር ደኅንነት እንዲጠበቅ ‹ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ› እያለ መጸለይ፤ የምእመናን ድኅነት እንዲረጋገጥም ሃይማኖት ማስተማር፣ በጎችን መሠማራትና ቀኖናን መጠበቅ ነበረ፡፡ ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹በጎቼን ጠብቅ፣ አሠማራ› ነበር የተባለው፡፡ መጠበቅ- ከክህደት፣ ከኑፋቄ፣ ከኃጢአት ከበደል፤ ማሠማራት – በትምህርት፣ በምግባር፣ በትሩፋት፣ በአገልግሎት፣ በጽድቅ መስክ ላይ፡፡
‹ባለሞያ ሴት የሠፋችውን ወራንታ፣ ጅል ትተረትረዋለች› እንደተባለው በደኅና ጊዜ ትጉኃን አበው የሰበሰቧቸውን ወጣቶች ካልበተንኩ ብሎ እንዴት አንድ ፓትርያርክ ይነሣል፡፡ ወጣቶቹ ሊሳሳቱ፣ ሊያጠፉም ይችላሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ለዚህም መንገድ ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሳይቀሩ የገዛ ልጆችዎን ያወያዩ ሲሏቸው በራቸውን ጠርቅመው የሚዘጉ ፓትርያርክ በታሪክ የሚጀመሪያው መሆን አለባቸው፡፡ በሱራፊ ነበልባል የተዘጋች ገነት ስትከፈት በፓትርያርክ የተዘጋች የቤተ ክህነት በር ልትከፈት አልቻለችም፡፡ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማነጋገር የደከሙ እነ ክርስቶስ ሠምራን የመሰሉ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን እረኛው ከመንጋው ጋር መነጋገር አቃተው፡፡ ኢየሱሳውያንን በዐደባባይ ሳናነጋግራቸው መሄድ የለባቸውም ብለው የተሟገቱ እነ እጨጌ በትረ ጊዮርጊስ በነበሩባት ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቹን ለማነጋገር በር የሚዘጋ እጨጌ ተፈጠረ፡፡ የመካ ቁራይሾችን አሳልፈን ለጠላቶቻቸው አንሰጥም የሚሉ አበው በነበሩባት ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቹን አሳልፎ የሚሰጥ አባት መጣ፡፡
የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት በ1972 እኤአ ካይሮ ላይ ባደረጉት ጉባኤ ከተስማሙባቸው ነገሮች አንዱ የኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳት ተልዕኮ ነበረ፡፡ እንዲህ ይላል ‹ኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳት አምስት ተልዕኮ አላቸው፡፡ እነዚህም
1. ወንጌልን መስበክ(Preach the Gospel)
2. ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን መፈጸም(Administer the Sacraments of the Gospel.)
3. የቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ አንድነትና ቀኖና መጠበቅ(Guard the faith, unity, and discipline of the church.)
4. ለካህናትና ለምእመናን የቅድስና ምሳሌ መሆን(Be a moral example of holiness and wholesomeness.)
5. በእረኛውና በበጎች መካከል ያለውን ክፍተት ማጠበብ(Diminish the distance between bishops and their flock.)
ለመሆኑ የእኛ አባት የቱን ነው እየፈጸሙ ያሉት? ወይስ ከኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ማኅበር ውጭ ሆነናል?
ዐውደ ርእዩ የማይደረግበት በቂ ምክንያት ከነበረ ቢያንስ ከሳምንት በፊት መግለጥ ይቻል ነበር፡፡ ዓላማው ግን ማበሳጨት፣ ዐመጽ ማስነሣት፣ ተሥፋ ማስቆረጥና ምእመናንን ወደማይፈልጉት መሥመር መውሰድ ነው፡፡ ለዚህ ነው ፈያታዊ ዘየማን ገነት በገባባት ሰዓት ዐውደ ርእዩ እንዲዘጋ የተደረገው፡፡ የዚህች ሀገር ሰላም አይፈለገም? ምእመናን ሀገር እንደሌላቸውና መብት እንደሌላቸው ራሳቸውን እንዲቆጥሩ ይፈለጋል? ‹ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል› እንዲል ሀገሪቱ ያለባት ችግር አይበቃትም? ተጨማሪ ችግር ማምረት ይፈለጋል?
ችግሩ ሁሉ እየተፈጠረ ያለው በመንግሥት ስም ነው፡፡ ‹መንግሥት አዞናል፤ እገሌ የተባለ ባለ ሥልጣን ብሎናል፤ ፖሊስ እንጠራለን፤ ደኅንነት እናዛለን› ነው በቤተ ክህነቱ ዘንድ የሚባለው፡፡ እውነት መንግሥት በስሙ የሚሠራውን ያውቀዋል፤ ካወቀውስ ዝም ይላል? ቤተ ክህነቱ በሚያመጣው ዳፋ መከራ ለመቀበልስ ዝግጁ ነው? ይህ አካሄድስ ለሀገሪቱ ደኅንነት የሚበጅ ነው? ዐውደ ርእዩ እንዲዘጋ ያዘዘውስ የትኛው መንግሥት ነው? አንዱ የሚፈቅድ ሌላው የሚዘጋ ስንት መንግሥት ነው ያለው? ወይስ ‹ደብዳቤ መጻፉ አላዋጣምና ዝጋልኝ› ተብሎ እጅ የተሰነዘረለት አካል ያደረገው ነው? መጽሐፉ እንደሚል ‹የማይገለጥ የተሠወረ› አይኖርምና ዐውቀነዋልም፣ እናውቀዋለንም፡፡
የገዛ ፓትርያርካችን ለእኛ ለምእመናን ድኅነትን እንዳናገኝ ሥጋት ሆነውብናል፡፡ የታገሡትን ሁሉ ለክፋት በማነሣሣት ደግሞ ለሀገሪቱ ደኅንነት ሥጋት እየሆኑ ነው፡፡ የምእመናኑን ሥጋት ሲኖዶሱ፤ የሀገሪቱንም ሥጋት መንግሥቱ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ከቤተ መቅደስ የተነሣ ችግር መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው አይታወቅምና፡፡ እንዲህ ያሉ ነገሮች የምእመኑን የአስተሳሰብ ቅርጽ ይቀይራሉ፡፡ የሐበሻን ሥነ ልቡና ለሚረዳ ደግሞ ሲረገጥ እንደሚጠክር ጭቃ ያጠነክራሉ፡፡ ሲሞረድ እንደሚሳል ቢላዋ፣ ሲቀረጽ እንደሚሾል እርሳስ ያደርጋሉ፡፡
በዐውደ ርእዩ የሚማሩት የሚያዩት ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን ግን ያላዩትም እንዲማሩ አድርገዋል፡፡ ሐሳብና ርእዮት ሊያስተባብረው የማይችለውን ተጠቂነት ያስተባብረዋል፡፡ ተጠቂነት ክርክርና ውይይት፣ ማስረጃና መረጃ አይጠይቅም፡፡ መጠቃቱን ያወቀ ሁሉ ራሱ ገብቶት ይተባበራልና፡፡ ምናልባትም ምእመናንን ከገድል ተራኪነት ወደ ገድል ሠሪነት ያሻግራቸው ይሆናል፡፡ ‹እዚያም ቤት እሳት አለ› አሉ አለቃ፡፡
እንደ ሶምሶን ከአንበሳ ሬሳ ማር ለማውጣት ግን በሳል አመራር ይጠይቃል፡፡ የማኅበሩ አመራርም ቢሆን ጊዜውን አይቶ የሚሣለጥ አመራር እንጂ የተቸከለ አመራር መሆን የለበትም፡፡ የፓትርያርክ ማትያስ ዘመን እንደ ፓትርያርክ ጳውሎስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምም ዘመን እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አይደለም፡፡ አሁን የሆነው ነገር ሊሆን እንደሚችል ቀድሞ እየታወቀ ከግንቡ ጋር እስኪጋጩ ድረስ ቆሞ መጠበቅ ብልህነት አይደለም፡፡ አሁንም ‹እገሌ የተባለ ባለሥልጣንን አናግረናል፤ እገሌ የተባሉ አባት አይዟችሁ ብለውናል› እያሉ መጓዝ የሚያዋጣ አይደለም፡፡ ለጉባኤ ተሰብስቦ ‹ ለፓትርያርኩ የተጻፈው ደብዳቤ አንጀት አርስ ነው› ብሎ አጨብጭቦ የሚበተን አመራር ጊዜው ሊያልፍበት ይገባል፡፡ ከዲሚትሪ ሆቴል እስከ ፌዴራል ጉዳዮች የተደረጉትን ውይይቶች ገምግሞ አዲስ አቅጣጫ መያዝ ይገባ ነበር፡፡ የሚሰበሰብ ብቻ ሳይሆን የሚተነብይ አመራርም ያስፈልጋል፤ ካልሆነ ግን
‹ከክምር ድንጋይ ላይ ይበቅላል ደደኾ
የፈራሁት ነገር መጣ ድኾ ድኾ› የተባለው ይደርሳል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

3 Responses to ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት

 1. “ተጨማሪ አስታየት””
  “”የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ፡ ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር በምን ምክንያት ቢሉ፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅሲያ የአንዲት ክርስቲያን መእምንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው ነበር”””ዳንኤል ክበብረት በማን አለብኝነት በእጨጌ መንበሩ ላይ የተቀመጡትን ፖትርያርክ እና ሌሎቹንም አባቶች በመተቸት በህብረተሰብ ድህረ ገጽ ላይ ካወጣው ጹኡፉ የተወሰደ ነው፡፡ ፍየል ወደዚህ ቅምዝምዝ ወደዛ የሚሉት አባባል ሆነብኝ ፡ጥቅሱ ትክክል ነው ወቅታዊም ነበር ልብ ያለው ወቃሺ ቢገኝ እውነትም የዘበናችን ዮሐንስ አፈወርቅ ባልንህ ነበር፡ በዚህ ወቅት ያገሬቷ ገበሬ መሬታችንን ተቀማን በማለት ብሶቱን በአደባባይ እያሰማ እየተደበደበ,እየታሰረ, እየተገደለ ባለበት ወቅት በዚህ ጥቅስ መንግሥትን መገሠጽ ነበረብህ…!!! ይህ ሕዝቡ ክርስትያን አይደለም ወይ? ባይሆንስ ኢትዮጵያዊ አይደለም ወይ? በዚህ ሕዝብ እና በመንግሥት መሃል በመሆን አሰታራቂ ሃሳብ በማምጣት ሕዝብና መንግሥትን እንደማቻቻል ፋንታ ያለቦታው ጠንካራ የእምነት አርበኞች የሰሩትን ጀግንነት የሚያመለክተውን ጥቅስ በመጥቀስ ብቻ እንደነሱ ታዋቂ ለመሆን መሞከር ፈሪነትም, ተንኮለኝነትን የተላበሰ ትዝብት ላይ የሚጥል አጉል ስልት ነው፡፡ይህንን ጥቅስ ለትክክለኛ ቦታ በትጠቀምበት ኖሮ ለዚህች እምነት እና ያላግብ ለተበደሉ ሕዝቦች ሕይወትህን አሳልፈህ እንደሰጠህ ይቆጠር ነበር ይህ ነው ተጋድሎ ማለት ዳሩ ይህንን የላደረክበት በመፍራት መንገሥት ያስረኛል ከፈለገም ይገለኛል በማለት ያለቦታው ባሌለህ የእውቀትም ሆነ የሹመት ደረጃ የእምነት አባቶችን መናገር “”አወኩሺ ደፈርኩሺ አሳልፌም ለደፋሬ ሰጠውሽ ነው” ይህንን እኩይ ሥራህን ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ፍንትው አድርጎ ለመምእኑ እና ለእምነቱ አላፌዎች ማሳየት ለአስፈላጊው እርምጃ የሚመለከተው አካል ድርሻ ይሆናል፡ኢላማውን የሳተ ብልጥነት የተላበሰ የስድብ አባዜ በየጊዜው ከአንተ መሰንዘሩ ከተራ ተሳዳቢነት ውጭ ዮሐንስ አፈወርቅ መሆንን አያስገኝም ለመሆኑ ይህንን የስድብ ሰርተፍኬት የተቀበልከው ከማን ይሆን? ዳንኤል ክብረት ለመሆኑ አንተ ማነህ? ከየትኛውስ ነህ? ሰው ለመሾም ጥሩ ሥራ ሠራ ለመባል አነድ ነገር ላይ በቋሚ በሃሪው፡በመቀሳቀስ ለውጤት የደክማል ማንነቱም ይለካበታል አንተ ግን በዚህ ሁሉ ዘበንህ ሰዎችን ከመወንጀል አልፈህ ትላንት ከተላንት ወዲያ ማህበረ ቅዱሳንን ይህው ዛሬ ለነሱ የተቆረቆርክ መስለህ አባቶችን ማብጠልጠል ምን የሚሉት እርግማን እንደሆነ እ/ር ይወቀው፡፡ ነግ ተነጎድያ ደግሞ ዛሬ ጥሩ ናቸው እያልክ እያሞካሸህ አባቶቼ ወንድሞቼ የምትላቸውን ከእኔ በላይ አዋቂ ላሳር ነው በማለት እንደምታዋርዳቸው እርግጠኛ ሆኜ እናገራለው፡፡ ጹኡፍህ እና ድርጊትህ እጂግ የተለያዮ የመሰሪነት,የንቀት, እኔን ከነኩኝ ጉድጏድ ቆፊሬ እቀብራቸዋለው የሚል ስለሆነ ዳንኤል ክብረት ያንተ የተንኮለኚነት አካሄድ ያበቃ መሰለኝ
  መህበረ ቅዱሳንም አንተ እንደ ወነጀልካቸው እንደከሰስካቸው ሳይሆን ባላቸው የአመራር አባላት ብርታት እና ጸሎት ከእናት ቤ/ክ ጋር ያላቸውን ልዮነት አሶግደው እንደልጂነታቸው ከእምነት አባቶቻቸው እግር ስር በመሆን ባይመቻቸው እንኴን የክርስትና ሕይወት አልጋባልጋ እንዳይደለ ስለሚያውቁ አብረው ለበለጠ ሥራ ይተጋሉ በውይይት በይቅርባይነት ከአባቶች ጋር ያለመግባባት እንኳን ቢከሰት በውስጥ አሰራር ነገሩን በመፍታት ጠንካራና ትኡት ወጣቶችን ለዚች ቤ/ክ ያስገኛሉ እስካሁን ነገራቸውን በመጠላለፍ አንዱን ከሌላው ጋር ተጠራጣሪ በማድረግ ስውር አመራረ አላቸው በማለት የሕዝብም ሆነ ያባላቱን ታማኝነት እንድያጡ በማሰብ የእባብ መርዝህን ለመላው ዓለም የረጨህው የትላነት ሥራህ ነው፡፡ በዚህ አድራጎትህ ዮሐንስ አፈወርቅነትም, ዝናም,የእምነት ጀግንነትም አይገኝም ከዚህ ድፍረትህ በኋላ ማንነትህን መላው ኢትዮጵያዊ ያወቀህ ይመስለኛልና በቃህ ከስድብህ ከውርደትህ ጋር ከማእከላቸው ውጣ፡፡

  Like

 2. Bizuneh Simei says:

  “””የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ፡ ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር በምን ምክንያት ቢሉ፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅሲያ የአንዲት ክርስቲያን መእምንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው ነበር”””ዳንኤል ክበብረት በማን አለብኝነት በእጨጌ መንበሩ ላይ የተቀመጡትን ፖትርያርክ እና ሌሎቹንም አባቶች በመተቸት በህብረተሰብ ድህረ ገጽ ላይ ካወጣው ጹኡፉ የተወሰደ ነው፡፡ ፍየል ወደዚህ ቅምዝምዝ ወደዛ የሚሉት አባባል ሆነብኝ ፡ጥቅሱ ትክክል ነው ወቅታዊም ነበር ልብ ያለው ወቃሺ ቢገኝ እውነትም የዘበናችን ዮሐንስ አፈወርቅ ባልንህ ነበር፡ በዚህ ወቅት ያገሬቷ ገበሬ መሬታችንን ተቀማን በማለት ብሶቱን በአደባባይ እያሰማ እየተደበደበ,እየታሰረ, እየተገደለ ባለበት ወቅት በዚህ ጥቅስ መንግሥትን መገሠጽ ነበረብህ…!!! ይህ ሕዝቡ ክርስትያን አይደለም ወይ? ባይሆንስ ኢትዮጵያዊ አይደለም ወይ? በዚህ ሕዝብ እና በመንግሥት መሃል በመሆን አሰታራቂ ሃሳብ በማምጣት ሕዝብና መንግሥትን እንደማቻቻል ፋንታ ያለቦታው ጠንካራ የእምነት አርበኞች የሰሩትን ጀግንነት የሚያመለክተውን ጥቅስ በመጥቀስ ብቻ እንደነሱ ታዋቂ ለመሆን መሞከር ፈሪነትም, ተንኮለኝነትን የተላበሰ ትዝብት ላይ የሚጥል አጉል ስልት ነው፡፡ይህንን ጥቅስ ለትክክለኛ ቦታ በትጠቀምበት ኖሮ ለዚህች እምነት እና ያላግብ ለተበደሉ ሕዝቦች ሕይወትህን አሳልፈህ እንደሰጠህ ይቆጠር ነበር ይህ ነው ተጋድሎ ማለት ዳሩ ይህንን የላደረክበት በመፍራት መንገሥት ያስረኛል ከፈለገም ይገለኛል በማለት ያለቦታው ባሌለህ የእውቀትም ሆነ የሹመት ደረጃ የእምነት አባቶችን መናገር “”አወኩሺ ደፈርኩሺ አሳልፌም ለደፋሬ ሰጠውሽ ነው” ይህንን እኩይ ሥራህን ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ፍንትው አድርጎ ለመምእኑ እና ለእምነቱ አላፌዎች ማሳየት ለአስፈላጊው እርምጃ የሚመለከተው አካል ድርሻ ይሆናል፡ኢላማውን የሳተ ብልጥነት የተላበሰ የስድብ አባዜ በየጊዜው ከአንተ መሰንዘሩ ከተራ ተሳዳቢነት ውጭ ዮሐንስ አፈወርቅ መሆንን አያስገኝም ለመሆኑ ይህንን የስድብ ሰርተፍኬት የተቀበልከው ከማን ይሆን? ዳንኤል ክብረት ለመሆኑ አንተ ማነህ? ከየትኛውስ ነህ? ሰው ለመሾም ጥሩ ሥራ ሠራ ለመባል አነድ ነገር ላይ በቋሚ በሃሪው፡በመቀሳቀስ ለውጤት የደክማል ማንነቱም ይለካበታል አንተ ግን በዚህ ሁሉ ዘበንህ ሰዎችን ከመወንጀል አልፈህ ትላንት ከተላንት ወዲያ ማህበረ ቅዱሳንን ይህው ዛሬ ለነሱ የተቆረቆርክ መስለህ አባቶችን ማብጠልጠል ምን የሚሉት እርግማን እንደሆነ እ/ር ይወቀው፡፡ ነግ ተነጎድያ ደግሞ ዛሬ ጥሩ ናቸው እያልክ እያሞካሸህ አባቶቼ ወንድሞቼ የምትላቸውን ከእኔ በላይ አዋቂ ላሳር ነው በማለት እንደምታዋርዳቸው እርግጠኛ ሆኜ እናገራለው፡፡ ጹኡፍህ እና ድርጊትህ እጂግ የተለያዮ የመሰሪነት,የንቀት, እኔን ከነኩኝ ጉድጏድ ቆፊሬ እቀብራቸዋለው የሚል ስለሆነ ዳንኤል ክብረት ያንተ የተንኮለኚነት አካሄድ ያበቃ መሰለኝ
  መህበረ ቅዱሳንም አንተ እንደ ወነጀልካቸው እንደከሰስካቸው ሳይሆን ባላቸው የአመራር አባላት ብርታት እና ጸሎት ከእናት ቤ/ክ ጋር ያላቸውን ልዮነት አሶግደው እንደልጂነታቸው ከእምነት አባቶቻቸው እግር ስር በመሆን ባይመቻቸው እንኴን የክርስትና ሕይወት አልጋባልጋ እንዳይደለ ስለሚያውቁ አብረው ለበለጠ ሥራ ይተጋሉ በውይይት በይቅርባይነት ከአባቶች ጋር ያለመግባባት እንኳን ቢከሰት በውስጥ አሰራር ነገሩን በመፍታት ጠንካራና ትኡት ወጣቶችን ለዚች ቤ/ክ ያስገኛሉ እስካሁን ነገራቸውን በመጠላለፍ አንዱን ከሌላው ጋር ተጠራጣሪ በማድረግ ስውር አመራረ አላቸው በማለት የሕዝብም ሆነ ያባላቱን ታማኝነት እንድያጡ በማሰብ የእባብ መርዝህን ለመላው ዓለም የረጨህው የትላነት ሥራህ ነው፡፡ በዚህ አድራጎትህ ዮሐንስ አፈወርቅነትም, ዝናም,የእምነት ጀግንነትም አይገኝም ከዚህ ድፍረትህ በኋላ ማንነትህን መላው ኢትዮጵያዊ ያወቀህ ይመስለኛልና በቃህ ከስድብህ ከውርደትህ ጋር ከማእከላቸው ውጣ፡፡

  Like

 3. Bizuneh Sime says:

  እብዛም የጠለቀ የነገረ መለኮት ትምህርት የለኝም ነገር ግን ማንም ኤትዮጵያዊ አስተዳደጉ አኗኗሩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርሃቱ በማንኛውም ደረጃ ያለውን ስህተትና እውነት መለየት አያዳግተውም
  እውነት የዳንኤል ክብረት ወቀሣ,ሥርሃቱን,ደረጃውን እና ወቅቱን የጠበቀ ነው ወይ ? ይህስ አሰራር ከነገረ መለኮት ሚስጤራዌ አፈጻፀም ጋር አብሮ የሚጓዝ ይመስላል ወይ? ችግሮዎች የሉም አልተፈጠሩም ማለቴም አይደለም ነገር ግን በዚህ ሰው እና በእንደዚህ ያለ ሥርሃቱን ባጣ ደረጃውን ባልጠበቀ ኢ -ኦርቶዶሳዊነት በሆነ አሰራር ችግሩ ሊቀረፈ ይቻል ይመሰላችዋልን? አገሬቷ በከፋ ችግር ላይ በወደቀችበት ወቅት የኤትዮጵያዊያን ደም እየፈሰሰ ሕይወት እየተቀጠፈ ባለበት አስከፌ ጊዜ ሕዝቡ የሰው ዳኛ አጥቶ በየእምነቱ ጎራ አምላኩን በሚማጸንበት ወቅት የአገሬቷን ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሕዝበ መእምን ይዛ የምታስተዳድረዋን ቀዳሚት እምነት በእነ ዳንኤል ክብረት የስደብ ውርጂብኝ እና ጦርነት እየታወጀባት ነው ፡፡ ካሃናቱ,መነኰሳቱ,ጳጳሣቱ,እነደ ዳንኤል ማን አለብኝ በሚል ድፍረት ሳይሆን ፓትርያርኩም,, ሰዎች ናቸው ፡ግን የተሾሙት ሹመት, የያዙት መሥቀል,የተሾሙበት እጬጌ መንበሩ እንኳን በተራው ዳንኤል በሚመለከታቸው አባቶች አይተችም ፓትራርክን ከሴጣን ጋር ከአፍዝ አደንግዝ ጋር እያገናዘበ ሰድቦ ለሰዳቤ መስጠት የጊዜያቺን እጂግ ቅጥያጣ ድፍረት መሆኑን ያመለክታል፡፡ ለዚህ አጉል ድፈረትህ ቅጣቱን የሚሰጠህ አይቸኩልምም ደግሞም አይዘገይምም፡ ዳንኤል ሳታውቀው ጣራ ደረሥክ ጣትህና ድፉረትህ የስማይ አምላክን ዓይን ሌያወጣ መድረሱን አላወክምና ቆም ብለህ አሰተውል ፡፡
  ወገኖቼ, አንድ ገበሬ ብርቱከኳን ለማምረት ተከለና ምርቱን ሲጠብቅ የብርትኳኑ ዛፍ እጂግ የሚያጔጔ ብርትከኳን አፈራ የብርትኳን ዛፍ በተፈጥሮው እሾካማ ነው ያ ገበሬ እሾሁን ፈርቶ ብርትኳኑን ሳይሰበስብ ይቀራል ወይ? እርግጠኛ ነኝ እንደምንም ብሎ ተጠግቶ እሾሁን አልፎ በርቱኳኑን ይቀጥፋል የእኛ የእምነት አባቶች በብርትኳኑ ዛፍ ይመሰላሉ ሰዎች ናቸውና እንደሾኩ በብዙ የማያስጠጋ ችግር በዙራያቸው እንዳለ እናያለን ያንን አልፈን እንደ አባትነታቸው ተጠግተን በጉያቸው የያዙትን የከርስቶስን መስቀል እንሳለማለን፡፡ምህረትን, መዳንን, የምናገኝበት ሥርዓት አልጋባልጋ እንዳይደለ መእምኑ ጠንቅቆ ያውቃል፡ ለመሆኑ አንተ በመዳፈር በእግዜሃቤሔር ሥራ ገብተህ የተሣዳቤነትህን እልህ ለማብረድ ሥትጮህ ለካ ማንም ተነሥቶ ከቄስ እስከ ፖትርያርክ መተቸት መሳደብ ይችላል በማለት የአንተ ቢጤ ተሳዳቤ እንደምታመርት አውቀህው ይሆን? ልጂ አባቱን, ታናሺ ታላቁን,እንዲሰድብ ለህብረተሰቡ ስርዓተአልበኝነትን እየጋበዝክ መሆኑን ላሳስብህ እወዳለው ለዚህም ድፍረትህ እና ለተደጋገመ ጦርነት ጫሪነትህ ያባቶችን ሥርአት የሚጠብቅ አምላክ ይቀጣሃል ፡፡
  በዲያስፓራ ያሉትን ጠንካራ ቤ/ክን ከእናት ቤ/ክ ወጥታችዋል ተብለው ቢወቀሱ እና መእምኑ ቢያዝንም በጠንካራ የደብሩ አባቶቺ የበሰለ ችሎታ የመበረ ፖትርያርኩን ክብርና ፍቅር ባማይነካ መልኩ ጭራሺ በሙሉ አከብሮት የተፈጠረውን ስህትት በማረም መእምኑን በሚገርም ሁኔታ አጽናንተውታል፡
  ሥራቸው የሰውነት ብቻ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በደብሩ አባቶች ላይ አድሮ የሠራው ታላቅ ሥራ የታየበት መሆኑን ልነግርህ ይገባል ይህ ነው፡ ኦርቶዶክሳዊነት፡ ይህን የመስለ የአባቶች ችሎታ የያዘች ቤ/ክ ዛሬ ባንተ አንድ ተራ ተሳዳቤ ስትተች አያሳዝንም፡፡እነዚህ አባቶች ሊሳሳቱ ሊያጠፉ ይችሉ ይሆናል ሥጋ ለባሾች ናቸውና,,,,,, አንድ ነገር እንድትገነዘብ ልንገርህ,,,ክርስቶስ ድንቅ ሥራውን የሚሥራባቸው እነዚሁን አባቶች እንጂ አንተን እና ቢጤዎችህን እንደማይሆን እወቅ፡ የተከሰተው ችግር አዲስ ነገር ሆኖ አይደለም ቤ/ክኗ ከጥንት ጀምሮ ችግሮቿን እያስተናገደች ኖራለች ወደፊትም በደረጃ ትኖራለች በሥራትና በአሏት ውስጠ ደንብ ከጸሎት ጋር ይታረማል እንጂ በአነተ ጦርነት ማወጂ እና አጉል ድፍረት የሚመጣ አዲስ ነገር የለም፡፡
  የምትችል አይመስለኝም ከቻልክ ከመገነጣጠል አንድነትን አስተምር ፡ጦርነትን ከማወጅ በፀሎት መፍቴዎችን ለማምጣት የስላምና የፍቅር ሥራን መሥራት እንጅ የማይገባህን ሥራ ከመሥራት ተቆጠብ ፡ የሚቀጣህ ሰው ባይኖር ይችን አገርና ቤ/ክ የሚጠብቅ እግዜሃብሔር ያስተካክልሃል፡፡ግብረገብ የጎደለህ ስለሆንክ ዛሬ ከገለጥካት ቤ/ክ እና ከደፈርካቸው አባቶች እግር ስር ተቀምጠህ እራሥህን ጠንቅቀህ እንድታውቅ ተማር፡፡
  ዳንኤል,,,በዚህ 25 ዓመታት ውስጥ ለሥንቱ ሥም አወጣህላሃቸው ስንቱን ከደከሙበት ገፈተርካቸው ስንቱን አስገፈተርካቸው ፡፡ይንሁሉ ስትወነጂል እግዜሃብሔር ቢታገስህ ዛሬ ይህው ከካህናት እስከ እጬጌ መንበሩ ደረስክ ፡፡ ይህንን ታላቅ ሹመት ለኤትዮጵያ ሰጥቶ ከግብጽ ባርነት ያወጣን አምላክ የእጂህን ይሰጥሃል እና አባቶችን ከመሳደብ ትውልድን ወደርግማን ከመጎትት፡ ታቀብ፡፡
  ክርስትና ፈተና የበዛበት የእድሚ ልክ ረዢም ጉዞ ነው ባለንበት ፀንተን ችግሩን በአግባቡ እየቀረፋን የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡፡
  ይህ ቅጥ ያጣ ተሣዳቢነትህን የብዙ ሕዝቦች መመኪያ በሆነችው አንዲት ቤ/ክ ላይ ምታ ነጋሬት ክተት ሰራዌት በማለት ጦርነት አታውጂ፡ ዳንኤል ክብረት,,,,እኛ በአንድት ቤ/ክ ጥላ ስር እንዳለን ነበር የሚመስለን አነተ ግን እንዳይደለን ነገርከን,,,ተጠንቀቁ እኛም ቤት እሳት አለ አልከን በል እንግዴ,,,መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ,,,በዝች ቤ/ክ እና በደፈርካቸው አባቶችቤት ዙራም መንፈስ ቅዱስ አለና ረጋ ብለህ አስብበት፡፡ አባቶቻችን ደግነታቸ ው የዋህነታቸው, ታጋሽነታቸው, ሲያስተምሩን ,ገድላቱን አዋልዱን, ገዳማቱን እየጠቃቀሱ አባትነትን በተምላ ፍቅራቸው ከስማይ መነበሩ መንፈስቅዱስን በማምጣት የሚያስባርኩን እንጅ አንተን የመሰለ ልቡ በአወኩ ባይነት የታበየ የመጸሃፈ ቅድስን ቁጥሩን እንጅ ፈቅሩ የማይታይብህን የገደል ማሚቱ ጪሁት ከዝህ በላይ የትም እንደማያደርስህን ብትገነዘብ መልካም የመስለኛል፡፡ይህ ትውልድ አባቶችን የሚወድ የሚያከብር, በጥሩ ሥነምግባር ከወላጆቹ ተመክሮ ያደገ እንጂ እንዳንተ በደነደነ ልብ ሹመተ እግዜሃብሔር ያላቸውን አባቶች የሚዳፈር የሚሳደብ ትውልድ እንደማይሆን በኤትዮጵያዊነቴ እመሰክራለው ለምን ብትለኝቶ አባቶችን የሚሰድብ ትውልድ ወልዶያሳደገ አይኖርምና ፡፡ ወገኖቼ,,ለቤ/ክ ፀሎት ነው የሚያስፈልጋት ለተፈጠረው ችግር መፈቴ መፈለግ ላላግባባው ችግር ሱባዬ ማወጂ እንጂ የሆነውን ካልሆነው አቀላቅሎ አንድ ተራ በዳቆን ሥም የሚጠራ ,,,በአወኲ ባይ ትምክት ከካህናት እስከ መበረ ፓትሬያርክ ድረስ በመሳደብና በማሳነሥ አገላለጽ በህብረተሰብ ድህረ ገጽ ላይ በማውጣት ይእች አገርን ከማንነት ጋር ቀርጻ ለዛሬይ ያበቃችንን፡ እናት ቤ/ክን ማዋረድ ትልቅ ወንጀል ነው,,,,ዳንኤል ተቆርቋሬና ህግ ጠፍቶ በሰውሰውኛ ባትቀጣም ለእምነቱና ለቤቱ እንዲሁም እራሱ ወርዶ ለቅዱሣን ተገልጦ ይችን ሕገ እግዚሃቤር,,,,,,,,,,,,,,,,,,, እምነት ለኤትዮጵያዊያን የመሰረተ መዳሃኔዓለም ክርስቶሰ ልቦናህን እንዲመረምረው ደረጃህን ጠብቀህ በጸሎትና በትእግስት የድርሻህን ሥራ በአግባቡ እንድትወጣ እንዲያስታግስህ የጦርነት ዘመቻ ያወጅክባት ሥራሃተ ቤ/ክ እና ከሴጣን እና ከአፍዝ አደንግዝ ጋር ያመሳሰልካቸው ብጽዋን አባቶች ጸሎት ይታደግህ፡፡ አባቶችን የሚሳደብ ትውልድ አትመስርት ያንተን ፈለግ ተከትሎ በተለያዮ ድህረ ገጾች ላይ ከሥእለ አድኖ እስከ ተለያዩ ፅኡፍች አግባብ በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ ናቸው በተለይ የአንተን የመርገም ጩህት ፁኡፍ እየቆራረጡ ሳይፈሩ በድፍረት ያለቦታው በማስገባት የሚተቹ ወጣቶች በዚህ ጌዜ እየበዙ መጥተዋል ለምን ቢባል ለነሡ ዳንኤል ክብረት ከቄስ ከመሎክሴ ከፓትያርክም ባላይነውና እባክህን ትውልዱን ወደእርግማን አትምራው፡ ለጥፋት አንተው ትበቃለህ፡ታረም

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: