የከሸፈው የዳጋ እስጢፋኖስ ምዝበራ የወያኔ እጅ አለበት ተባለ

የከሸፈው የዳጋ እስጢፋኖስ አንድነት የወንዶች ገዳም የቅርስ ምዝበራና ዘረፉ የመንግስት እጅ እንዳለበት ታማኝ ምንጮች ገልፀዋል። ከ8ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ዘራፊወች በተጨማሪ 4 የስለላ እና ደህንነት ቢሮ አባላት 2ቱ የገዳማውያን አስኬማ ለብሰው ተመሳስለው 2ቱ እንደ ጎብኝ ሁነው ቀድመው በመግባት ነገሮችን ለማስተካከል እንዲችሉ ቢደረግም በእግዚአብሔር የረቀቀ ሀይል እንዲጋለጡ አድርጎ ገዳሙ ከመዘረፍ አደጋ እንዲድን አድርጓል።እግዚአብሔር ይመስገን !
ከ 1ወር በፊት ባቀረብኩት መረጃ ለንደነዚህ አይነት ወንጀሎች ይረዱት ዘንድ ወያኔ በባህርዳር ባለባጃጆችን እና ባለጀልባወችን በማህበር አደራጅቶ ለደህንነት ስራ እና በነሱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሚንቀሳቀሱ በፊት የፖሊስ አባል የነበሩ አሁን ደሞዛቸው ሳይጓደል ባጃጅ ና ጀልባ ተገዝቶ ተሰጥቷቸው የሚሰሩ ልጆች እንዳሉ ገልጨ ነበር።አሁንም በዳጋ ለከሸፈው የስርቆት እና የቅርስ ምዝበራ ወንጀል የእነዚህ ባለጀልባውች እና ባለባጃጆች እጅ አለበት ።በቀጣይም እንደምንጮቻችን ገለፃ ብዙ የታቀዱ የቅርስ ዝርፊያወች እንዳሉ እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ተከትሎ በጎንደር የታሰበ ዝርፊያ እንዳለ ፥ህዝቡም ነቅቶ ነገሮችን መመርመር እንዳለበት አፅዕኖት ስጥቶ ተናግረዋል ።
ታሪካዊ ቅርሶቻችንን ከወያኔ እና ከውጭ ዘራፊወች እንጠብቅ መልዕክቴ ነው።
@እንቅዩጳዝዩን

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: