የትግራይ ኣስተዳደር በ30 ሚልዮን ብር የሙስና ክስ ሊቀረበበት ነው።

የውሃና ኢነርጂ ምኒስቴር ለትግራይ ክልል መስተዳድር የ30 ሚልዮን ብር ሙስና ክስ ሊያቀርብበት ዝግጅቱ ማጠናቀቁ ታውቋል።

የ30 ሚልዮን ብር ክሱ በራያ ለመስኖ ስራ እንዲውል ተብሎ በፌደራል የውሃና ኢነርጂ ምኒስቴር በጀት ተይዞ የነበረ ሲሆን ምንም ሳይሰራበት የተዘረፈ ብር ነው።

ምኒስቴሩ በጀቱ የውሃ ጉድጓድ ተቆፍረው ገበሬዎች ለተለያየ የመስኖ ስራዎች የሚያገለገሉባቸው ፕላስቲክ ቱቦላሪዎች ከውጭ እንዲገዛ የታቀደ ሲሆን በወቅቱ የትግራይ ክልል የውሃና መኣድን ቢሮ ሃላፊ የነበረው ኣቶ ጌታቸው የተባለ የኣቶ ፀጋይ በርሀ የእህታቸው ልጅ ጥራት የጎደለው እቃ ካስገባና ከጥቅም ውጭ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ብሩ ይዞ ጃፓን ኣገር መግባቱ የሚታወቅ ነው።

ብሩ በመዘረፉ ምክንያት የመስኖ ስራው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የሆነ ሲሆን ብሩ ዘርፎ ጃፓን የገባው የኣቶ ፀጋይ በርሀ የእህት ልጅ የሆነው ኣቶ ጌታቸው በቁጥጥር ስር ለማስገባትም ምንም ዓይነት ሙከራ ኣልተደረገም።

ምኒስቴሩ ኣሁን በትግራይ ክልል መስተዳድር እየመሰረተው ያለው ክስ 30 ሚልዮን ብሩ ሙስና ዙርያ የወቅቱ የትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪዎች እጅ ኣላቸው የሚል ነው።የትግራይ ክልል በፌደራልና በክልል መንግስት የሚበጀት በሚልዮን የሚገመት ብር በሃላፊዎች እየተዘረፉ ፕሮጀክቶች ተጀምረው ሳይጠናቀቁ በቁም የሚቀሩባት ክልል ናት በኣሁኑ ወቅት ህወሓትና ሙስና፣ ሙስናና ህወሓት ተነጣጥለው የማይታዩ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፆች መሆናቸው ተረጋግጠዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: