የአዲስ አበባ ባሕር ዳር መንገድ ተምጫ ወንዝ ላይ ተዘጋ።

መንገዱ የተዘጋው ከደብረ ማርቆስ ወደ ፍኖተ ሰላም አቅጣጫ ይጓዝ የነበረ ከባድ የጭነት መኪና መንገዱን በመሳቱ ነው፡፡ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ የለም፡፡

መኪናው ወደ ተምጫ ወንዝ ለመግባት ለጥቂት የተረፈ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት
አላደረሰም፡፡
ነገር ግን መንገዱ በመዘጋቱ ተሸከርካሪዎች ለመተላለፍ መቸገራቸውንና ከዛሬ ማለዳ አንስቶ እስካሁን ድረስ መንገዱ አለመከፈቱን በቦታው የሚገኙ ሰዎች አረጋግጠውልና፡፡
በቦታው ጥቂት የትራፊክ ፖሊስ ቢኖርም ያለውን መጨናነቅ ለመቅረፍ በቂ አለመሆናቸውም
ተገልፆልናል፡፡
መንገዱ ባለመከፈቱ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ሰዎችን በእግር ድልድዩን በማሻገር
እየተቀያየሩ ወደ የመጡበት እየተመለሱ ነው፡፡
መለስተኛ መኪኖች በተምጫ ወንዝ ውስጥ እየገቡ እያለፉ ነው፡፡ አሁን ላይ ግን በአካባቢው ከባድ ዝናብ እየመጣ ስለሆነ ወንዙ ከሞላ ገብተው ለመሻገር እንደሚቸገሩ መንገደኞች ስጋታቸውን እየገለፁ ሲሆን መንገዱን ለመክፈት ከባድ መኪናውን የሚያነሳ ክሬን እንደሚጠበቅ ለመረዳት ችለናል፡፡

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የአዲስ አበባ ባሕር ዳር መንገድ ተምጫ ወንዝ ላይ ተዘጋ።

  1. Muleta says:

    ወሬኛ።
    መንገድ፡መዝጋት፡በጀግናው፡በላይ፡ዘለቀ፡ ጊዜ፡ ቀረ።

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: