የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸው ተነገረ

)

በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲያደርግ የቆየው ጥረት ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤውን እንደጻፉ በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቢቆይም የተፈለገው ውጤት ሊገኝ አለመቻሉን ሬፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ ድርጅት በድረ-ገጹ አስፍሯል። የጥረቱን አለመሳካት ተከትሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለን ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን ጋዜጣው የሃገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢምባሲ ተወካዮች በቋሚነት እንደሚጎበኙ በተደጋጋሚ ማረጋገጫን ቢሰጡም የተገኘ ውጤት አለመኖሩን ጋዜጣው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘን መረጃ ዋቢ በማድረግ በዘገባው አስነብቧል። የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ያደረገው ጥረት ውጤት አለማስገኘቱን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ካሜሩን ሪፖርት ሲያቀርብ መቆየቱም ታውቋል። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን የሚያደርጉት ዲቪድ ካሜሩን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በማንሳት ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ውይይትን ያካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት አስቀድሞ የሃገሪቱ ከፍተኛ የኢሚግሬሽንና የደህንነት ሃላፊዎች ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በጻፉት ደብዳቤም ሁለቱ ሃገራት ካላቸው የጠበቀ ግንኙነት አንጻር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ዙሪያ ሲደረገ የቆየው ውይይት ፍሬ አለማፍራቱ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ዴቪድ ካሜሩን ይህንን ጉዳይ ከአቶ አንዳጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ሲለዋወጡ መቆየታቸውንም ለመረዳት ተችሏል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: