የኢትዮጵያ ህዝብ ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲነሳ ጄኔራል ከማል ገልቹ ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት ዜና:- ህብር ራዲዮ ከላስቬጋስ እንደዘገበው፤ የመገንጠል ሀሳቡን ከፕሮግራሙ ያወጣው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ በአሁኑ ወቅት የግንባሩ ዋነኛ ዓላማ በተባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ወያኔን በማንበርከክ ለህዝቡ ጥያቄ እንዲገዛ ማድረግ መሆኑን በድጋሚ በማረጋገጥ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈልና ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
.
እንደ ህብር ዘገባ፤ ጄኔራል ከማል ይህን ጥሪ ያቀረቡት፤ እሳቸው የሚመሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በቅርቡ የመገንጠል ፕሮግራሙን በመተውና የኢትዮጵያ ህልውናን በመቀበል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለመታገል መነሳቱን አስመልክቶ ለተሰነዘሩባቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።
.
ጀነራል ከማል በዚሁ ምላሻቸው፤ የነፃነት ትግሉን ወደፊት ለመግፋት ያስችላል ያሉትን የኦነግ ዓላማን አብራርተዋል። ኦነግ ፤ለትግል እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን ነገሮች ማስተካከሉን የገለፁት ጄኔራል ከማል ህዝቡ ይህን መንገድ ተከትሎ ማንንም ሳይጠብቅ ራሱን ነፃ እንዲያወጣም በአጽንኦት አሣስበዋል።
.
የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ በስልጣን ላይ ያለውን የግፍ ስርዓት እንዲያስወግድ ከተፈለገ ፤የተቃውሞ ትግሉን የሚመሩ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ወገኖች መተባበር እንዳለባቸውም ጀነራሉ ሳይጠቁሙ አላለፉም።
.
«ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ከተንበረከከ በኋላስ- ምን አይነት መንግስት ይመሰረታል?» በሚለው አብይ ጥያቄ ዙሪያ የድርጅታቸውን አቋም ሲገልጹም፦ ኦነግ ከሌሎች ጋር በመሆን ምን አይነት አገር መመስረት እንዳለበት እንደሚነጋገርና ግንባሩ ለህዝቡ የሚያቀርበውን አማራጭ እንደሌሎቹ ድርጅቶች ሁሉ ለህዝቡ አቅርቦ በህዝቡ ውሳኔ የወደፊት እጣውን እንደሚወሰን አመልክተዋል።
.
ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ የአቶ መለስ አስተዳደርን አውግዘው ከመከላከያ ሰራዊቱ የተለዩት ምርጫ 97ን ተከትሎ ወያነ ሰራዊቱን ሽፋን በማድረግ በህዝቡ ላይ የወሰደውን ህገ-ወጥ ግድያ በመቃወም ቢሆንም፤ እ.ኤ.አ ከ2001 ጀምሮ በህቡዕ በኦነግ አመራር ውስጥ ተሳትፎ እንደነበራቸው ገልፀዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: