ሕግ አስከባሪው ፖሊስ እሴቷን አስገድዶ ለመድፈር ሲሞክር ድርጊቱን የተመለከተ ለምን ሳትፈልግ በግድ ብሎ በመጠየቁ “ህግ አስከባሪዎቹ ፖሊሶች ”ረሽነውት ሄዱ

በትላንትናው ዕለት በ 3/7/2008
በጨርቆስ ክፍለከተማ ቀበሌ 13 ነዋሪ የሆነው ወጣት ሽመልስ በፌዴራል ፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት ህይወቱ ማለፉን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።

በተለምዶ ………በሚባለው አካባቢ ሁለት የፌዴራል ፖሊሶች ወደ ስፍራው በማምራት ከአንዲት ግለሰብ ጋር ፀብ ይጀምራሉ። መንስዔውም፣ አንደኛው የፌዴራል ፖሊስ ግለሰቧን “ከእኔ ጋር ካላደርሽ”ብሎ በማስገደዱ ነበር። በስፍራው የነበረው ወጣት ሽመልስ
“ፍቃደኛ ካልሆነች ለምን አትተዋትም?” በማለት ለማገላገል ሲሞክር ፣ ፖሊሶቹም ” ምን አገባህ ?” በሚል በያዙት ዱላ ቀጥቅጠው ጥለውት እንደሄዱ ምንጮች ገልፀውልናል።

ወጣት ሽመልስ በወደቀበት ስፍራ ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ደብድበው መሄዳቸውን እንጅ መግደላቸውን ያላወቁት የፌዴራል ፖሊሶቹ በማግስቱ ሽመልስን ለማሰር ወደ አካባቢው የመጡ ሲሆን፣ ነዋሪውም በእልህና በቁጭት እንዳባረራቸው ለማወቅ ችለናል።

የወጣት ሽመልስ ጨርቆስ የቀብር ሥነስርዓት በዛሬው ዕለት መፈፀሙንም አረጋግጠናል።

 
Aseged Tamene
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: