የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ተንቀሳቅሳችኋል በሚል 13 ገለሰቦች ከአርባ ምንጭ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄን ለመሳተፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርጋችኋል የተባሉ 13 ሰዎች የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ከአራት ወር በፊት ከአርባ ምንጭ ከተማ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉት እነዚሁ ተከሳሾች የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ እንደሆነ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ክሱን ሰዎች ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው አቃቤ ህግ ተከሳሾች መቀመጫውን በኤርትራ ካደረገው የአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በአባልነት ለመታቀፍና የሽብር ድርጊትን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ በክሱ አቅርቧል። ይሁንና ተከሳሾች ለአራት ወራቶች ያህል ክስ ሳይመሰረባቸው ለምን እንደቆዩ ፖሊስ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩ ታውቋል። ነዋሪነታቸው በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የሆነ ኣነዚሁ ተከሳሾች በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ምርመራዎች ሲካሄድባቸው መቆየትን ከሃገር ቤት ከተገነው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ከተከሳሾች መካከል በጋሞጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ የሆኑት አቶ ሉሉ መሰለ የሚገኙበት ሲሆን፣ ክሱን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ለቀጣዩ ወር አጋማሽ ተለዋጭ ቀጠሮን ሰጥቷል።

d2256-amharademocraticmovementforce-ethiopia2

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: