በጎንደር‬ ጭልጋና አካባቢው በተለይም በጮንጮቅ በሀወሓት ታጣቂዎችና በገበሬዎች መካከል የተከፈተው ጦርነት ደም ባፋሰሰሁኔታ በርትቶ ቀጥሏል፡፡

በጮንጮቅ እየተካሄደ በሚገኘው ከባድ ውጊያ አረጋዊያን ሴቶችና ህፃናት የዕልቂቱ ሰለባ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ የህወሓት ታጣቂዎች በጮንጮቅና አካባቢው የሚኖሩ ገበሬዎችን የእህል ክምሮችና መኖሪያ ቤቶችን በእሳት አጋይተዋል፡፡
በጮንጮቅ እየተካሄደ የሚገኘውን ህዝባዊ ትግል የህወሓት/ብአዴን ሰዎች አማራና ቅማንት በሚል አቅጣጫ በማስቀየር በውሸት ህዝቡን ጎራ ለይቶ እርስበርሱ ተሰላልፎ እንዲጨራረስ ለማድረግ እየተጉ ነው፡፡
ከጎንደር መተማ የሚያደርሰው አውራ ጎዳና በመዘጋቱ ምክንያት እንደ አማራጭ የተያዘው ከጎንደር በሁመራ መስመር በኩል በስናር አልፎ መተማ የሚያስገባው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከሳምንታት በፊት በኦሮምያ የፈነዳው የህዝብ ቁጣ ማዕበል አድማሱን እያሰፋ የህወሓትን አገዛዝ እስከ አንገቱ ድረስ አጥልቆታል፡፡ ህወሓትም በምላሹ ወደ ህዝቡ መተኮሱን ገፍቶበት እስካሁን ከ30 በላይ ንፁሃን ሰዎች ህፃናትን ጨምሮ መጨፍጨፋቸው ተረጋግጧል፡፡

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: