“ለፍ/ቤት ያዘጋጀነው የፅሁፍ ምላሽ በማረሚያ ቤት ታገደብን” – ተከሳሾች

“ለፍ/ቤት የሚያቀርቡትን ፅሁፍ ማረሚያ ቤት ሳንሱር ማድረግ አይችልም” – ፍ/ቤት
በሽብር ክስ ይግባኝ የተጠየቀባቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ በአቃቤ ህግ ለቀረበብን የሰነድ ማስረጃ ያዘጋጀነው የፅሁፍ ምላሽ በማረሚያ ቤት ታገደብን ሲሉ ለፍ/ቤት አመለከቱ፡፡  ከእስር የተለቀቁት አቶ ሃብታሙ አያሌው ምላሻቸውን በፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ በሽብር የተከሰሱት አምስቱ አመራሮች በፍ/ቤት ከክስ ነፃ መሆናቸው ቢወሰንም፤ ከእስር ሳይለቀቁ መቆየታቸው ሲያወዛግብ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ አቃቤ ህግ፣ በይግባኝ ክሱን ቢገፋበትም፣ ተከሳሾቹ ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በመስጠቱ ነው ውዝግቡ የተቋጨው፡፡ በዚህም አቶ ሃብታሙ አያሌውና መምህር አብርሃም ሰለሞን ከእስር ወጥተዋል፡፡አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሸዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ግን፤ ቀደም ሲል ፍ/ቤት የወሰነባቸውን የዲሲፕሊን ቅጣት አልጨረሱም ተብለው በእስር እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ አቃቤ ህግ ላቀረበባቸው የሰነድ ማስረጃ የፅሁፍ ምላሽ ቢያዘጋጁም በማረሚያ ቤት እንደታገደባቸው የገለፁትም እነዚሁ ሦስት ተከሳሾች ናቸው፡፡ አቃቤ ህግ ያቀረበው የሰነድ ማስረጃ፣ ከብሔራዊ ደህንነት ተቋም የተገኘ
ነው ተብሏል፡፡  ፍ/ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካዮችን አስጠርቶ ጉዳዩን ካጣራ በኋላ፤ ታራሚዎች ለፍርድ ቤቱ የሚያቀርቡትን ፅሁፍ ማገድም ሆነ ሳንሱር ማድረግ እንደማይቻል ገልጿል፡፡ የተከሳሾችን የጽሑፍ
ምላሽ በማየት ውሳኔ መስጠት የሚችለው ፍ/ቤቱ እንጂ ማረሚያ ቤቱ አይደለም በማለትም፤ ተከሳሾቹ ያዘጋጁትን ፅሁፍ ለየካቲት 22  ይዘው እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

11035502_771235849624393_3401706099381023667_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: