በጎንደር የሽማግሌ ኮሚቴዎች የተዘጋጀው ይህ ለየት ያለና የደመቀ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ብሄርነት ጥያቄ በመግባባት ተጠናቋል

ቁጥሩ በግምት ከሰባት መቶ በላይ የሚሆን የጎንደርና አካባቢው ህዝብ በስብሰባው የተገኘ ሲሆን የላንድ ማርክ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ አልበቃ ብሎ ሰዎች ከውጭ ሆነው የታደሙበት ነበር
በስብሰባው የሃይማኖት አባቶች፣የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የወልቃይት የማነት ጥያቄ ኮሚዌዎች እንዲሁም ቁጥሩ የበዛ ወጣት የጎንደር እና አካባቢው ተወላጅ የስብሰባው ተካፋይ ነበር።
በቅርቡ በፀገዴ እና ሁመራ በህውሃት አስተባባሪነት “ወልቃይት የትግሬ ነው። ጥያቄ በሚያነሱ አንዳንድ ፀረ ልማቶች ላይ እርምጃ ይወሰድልን….” የመሳሰሉ መፎክሮችን ይዘው መውጣታቸው በተለይም ድምፁ ታፍኖ ቁጭ ያለውን የወልቃይት ህዝብ ስሜት አስቆጥቷል። ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ የኮሚቴው አባል እንዳሉት “የሆነው ሁነን የተፈጠርነውም አማራ ነው” በማለት ታዳሚውን አስጨብጭበዋል።የተላለፉ ውሳኔዎች
1. በአጭር ቀን ውስጥ ሌላ ስብሰባ በትልቅ አዳራሽ እንዲካሄድ ለዚህም እንዲረዳ ህዝቡ እንዲያውቀው ማስታወቂያዎጭን በየቦታው መለጠፍ
2. በተለያዩ የጎንደር በአጠቃላይ የአማራ አካባቢዎች ተመሳሳይ ስብሰባዎችን ለማድረግ እቅድ ተይዟል።
3. እንዳስፈላጊነቱ ሰላማዊ ሰልፍ የመጥራት
4.የጎንደር ከተማ ተወላጆችን በኮሚቴው ውስጥ ማካተት ዋና ዋናዎቹ ናቸው
አንድ ከዳባት የመጡ መምህር አባት እንዳሉት ከ 25 አመት በፊት የወልቃይትና አካባቢው ሁመራን ጨምሮ አስተዳደራቸው ዳባት ነበር ያሉ ሲሆን አያይዘውም ይህ የማንነት ጥያቄ የወልቃይት ብቻ ሳይሆን የዳባትም ነው ብለዋል። በተጨማሪም ኮሚቴው ዳባት መጥቶ እንዲያወያየን ሲሉ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ኮሚቴውም ጥያቄያቸውን ተቀብሏል።
ከታዳሚው ከተደረጉ ንግግሮች በጥቂቱ
“አሸሸ ገዳሜ እየተባለ በሚዘፈንበት አገር አሸንድየን ምን አመጣው? አትደባልቁብን።”

“በደም የገዛነው መሬት ነው የምትሉት የታገልነው ለነፃነት እንጂ አገር ለመሸጥ አይደለም”
“እስካሁን ብቻችንን ታግለናል አሁን ግን ጥያቄው የአማራ ህዝብ ሁሉ ሁኑዋል በዚህም ኮርተናል ጥያቄው ተጠናክሮ ይቀጥላል።”

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to በጎንደር የሽማግሌ ኮሚቴዎች የተዘጋጀው ይህ ለየት ያለና የደመቀ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ብሄርነት ጥያቄ በመግባባት ተጠናቋል

  1. Bezabih says:

    If you are going to protest, do it now when the TPLF is in a tense condition both from inside and outside. This is a very critical issue. When they are exploiting this fertile land, our people are are starved. The solution is only from this proud people

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: