የቀድሞው የትህዴን ሊቀ መንበር ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ከድቶ ለህወሓት እጁን ሲሰጥ ያስከተላቸው በርካታ ታጋዮች ወደ ኤርትራ በረሃ ተመልሰው በመምጣት አርበኞች ግንቦት 7ን እየተቀላቀሉ ነው፡፡

የቀድሞው የትህዴን ሊቀ መንበር ሞላ አስገዶም አራት ድርጅቶች ጥምረት መስርተው የጋራ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ዝግጅታቸውን በጀመሩበት በ2008 ዓ.ም መባቻ ነበር ከኤርትራ ከድቶ በሱዳን አልፎ ኢትዮጵያ በመግባት እጁን ለህወሓት የሰጠው፡፡ ሞላ አስከትሏቸው የሄደው የትህዴን ታጋዮች “ወደ ጦርነት ልትሄዱ ነው” በሚል እንደሸወዳቸውና ትጥቃቸውን በዘዴ አስፈትቶ ለጠላት አሳልፎ እንደሰጣቸው ይናገራሉ፡፡

ሞላ አወናብዶ ይዟቸው የከዳው ታጋዮች በአዳማ ከተማ “የተሃድሶ ትምህርት” በሚል ስም የውሸት ዲስኩር ለ1 ወር የተደረገላቸው ሲሆን ለመቋቋሚያ የሚሆን አስፈላጊ የሆነ ማንኛውም ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና በመረጡት የስራ መስክ እንዲሰማሩ እንደሚመቻችላቸው አገዛዙ ቃል ከገባላቸው በኋላ ወደየትውልድ መንደራቸው ተሸኝተዋል፡፡ ነገር ግን ከቃል ያለፈ ምንም ነገር አልተደረገላቸውም:: በመሆኑም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል፡፡

ታጋዮቹ ወደ ህበረተሰቡ ተቀላቅለው መኖር ሲጀምሩ በገሃድ የተመለከቱት ነባራዊ ሁኔታ በአዳማ ከተደረገላቸው “ኢትዮጵያ አድጋለች ተመንድጋለች… ፍትህ እኩልነትና ዴሞክራሲ ሰፍኖባታል…” የሚል ዲስኩር ጋር ፈጽሞ እንደተቃረነባቸው ይገልፃሉ፡፡

ታጋዮቹ በትንሹ ከ4 እስከ 9 ዓመታት ከትህዴን ጋር በበረሃ ሲታገሉ የቆዩ ሲሆን አገር ቤት ያለው ጭቆና እና ድህነት እንኳን ሊሻሻል ብሶበት ስለጠበቃቸው እንዲሁም ሞላ አስገዶም “ጦርነት አለ” በሚል አወናብዶ ለጠላት አሳልፎ ስለሰጣቸው በቁጭት እንደገና ተመልሰው ወደ ኤርትራ በረሃ በመውጣት አርበኞች ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ችለዋል፡፡

Hagere Natkbre's photo.

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የቀድሞው የትህዴን ሊቀ መንበር ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ከድቶ ለህወሓት እጁን ሲሰጥ ያስከተላቸው በርካታ ታጋዮች ወደ ኤርትራ በረሃ ተመልሰው በመምጣት አርበኞች ግንቦት 7ን እየተቀላቀሉ ነው፡፡

  1. Pingback: የቀድሞው የትህዴን ሊቀ መንበር ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ከድቶ ለህወሓት እጁን ሲሰጥ ያስከተላቸው በርካታ ታጋዮች ወደ ኤርትራ በረሃ ተመልሰው በመምጣት አር

Leave a comment