በደብረ ብርሃን ከተማ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር ተጋጭተው የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 08 ልዩ ስሙ አዲስ አምባ አካባቢ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር ተጋጭተው የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳር ፖሊስ በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተበባሪ ዋና ኢንስፔክተር ረጋሳ ኤዶሳ እንደተናገሩት የሰሌዳ ቁጥር አማ ኮድ 3 07902 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከከሚሴ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ እያለ ከደ/ብርሃን ወደ ቀይጥ ሲጓዝ ከነበረ ኢቲ 72320 ሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር በግምት ከጠዋጡ 3፡10 ገደማ ተጋጭተው የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በደ/ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላት የነበረች የአንዲት መንገደኛም ህይወት ደግሞ በተጨማሪ አልፏል፡፡
አደጋው የ15 ሰዎች ህይወት ያለፈበትና ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ነበር፡፡ የአደጋው መስኤ የህዝብ ማመላለሻው ሚኒባስ ከፊቱ የነበሩትን ሁለት ተሸከርካሪዎችን ደርቦ ያለመስመሩ ለማለፍ ባደረገው ሙከራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ዘግናኝ አደጋ የተከሰተው ከአሽከርካሪዎች የጥንቃቄ ጉድለት ስለሆነ በቀጣይም ሌላ ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ለሚያጓጉዙት ሰው ህይወት ትልቅ ዋጋ ሰጥተው በጥንቃቄና በኃላፊንት ስሜት ማሽከርክር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር ረጋሳ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደርም በደረሰው ዘግናኝ የመኪና አደጋ በእጅጉ ያዘነ ሲሆን በአደጋው ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: